ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ77 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ከ10 የስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካዎች መካከል አንዱንም ማጠናቀቅ ያልቻለው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለአባይ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን ለመስራት ኮንትራት ቢወስድም፣ ሰራውን መስራት ባለመቻሉ የውጭ ኮንትራክተር ቀጥሮ እያሰራ ነው። የውጭ ኩባንያዎች በአማካሪ ስም ቢቀጠሩም ዋናውን ስራ የሚሰሩት እነሱ ናቸው። አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ አዳማ ጋርመንት ...
Read More »በዛንቢያ 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተፈረደባቸው
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሊዋንጉዋ ማጀስትሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በትናንትናው እለት በዋለው ችሎት በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛንቢያ ገብተዋል ባላቸው 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ የአገሪቱን የሕገወጥ ስደተኞች ሕግ አንቀጽን በመጥቀስ እያንዳንዳቸው ስደተኞች 1 ሽህ 500 የዛንቢያ ክዋቻ እንዲከፍሉ ወይም የሶስት ወራት ጽኑ እስራት ይታሰሩ ዘንድ የፍርድ ብያኔውን ሰጥቷል። በሕገወጥ መንገድ ወደ ...
Read More »16 ኢትዮጵያውያንን አይሲስ ገደለ በሚል የተሰራጨውን ያልተረጋገጠ ዜና ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ሃዘኑን ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) አይሲስ የተባለው አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን 16 ኢትዮጵያውያንን ገደለ በሚል የተሰራጨው ዜና አልተረጋገጠም። ኢሳት ባደረገው ማጣራት የዜና ቀዳሚ ምንጭ የሆነው የኢራኑ ፕሬስ ቲቪ ያሰራጨውን ዜና ከድረ-ገጹ አንስቷል። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ይህንኑ ምንጭ በመጥቀስ ሃዘኑን መግለጹን ለመረዳት ተችሏል። በተለያዩ ድረገጾችና በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው ይኸው ኢትዮጵያውያን ተገደሉ የሚለው ዜና፣ ከአመት በፊት የነበረውን ሁኔታ የሚያስታውስ እንጂ አዲስ ...
Read More »በህወሃት ጄኔራሎች የሚመራት ሜቴክ በመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ መምጣቱን ታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) የህወሃት ታይ በነበሩት በእነ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው የመሰረታዊ ብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ከውጭ ሃገር በሚገቡ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በሞኖፖል እንዲያዝ በመደረጉ በመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ መምጣቱ ተገለጸ። መለዋወጫዎቹን ቶሎ ባለማቅረቡም ፋብሪካዎች ተበላሽተው ያለስራ ብዙ ጊዜያት ለመቆየት እንደሚገደዱ፣ ዕቃው ሲገኝም በውድ ዋጋ እንደሚቀርብላቸው ተመልክቷል። ይህንን ያጋለጡት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎች መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል። ...
Read More »በደራሽ ጎርፍ 120ሺ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የጣለውን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው ደራሽ ጎርፍ፣ ከ120 ሺ በላይ ሰዎች እንደተፈናቀሉና፣ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱት ደግሞ በዚሁ ጎርፍ ተፅዕኖ እንደደረሰባቸው፣ የኢትዮጵያ መንግስትና የሰብዓዊ ድርጅቶች ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ገለጸ። የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM)ን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ባለፈው ወር ብቻ በስድስት ወረዳዎች በከባድ ደራሽ ጎርፍ የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 119,711 ሲሆን፣ ሌሎች የእርዳታ ...
Read More »ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ዘር እንዲቀርብላቸው (FAO) ተማጸነ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የሚዘሩት ዘር ለሌላቸው ገበሬዎች ዘር እንዲቀርብላቸው የዕርዳታ ተቋማትን ተማፀነ። ድርጅቱ በድርቅ የተጠቁ ገበሬዎች ለዘር የሚሆን እህል ካላገኙ ለከፍተኛ ረሃብና የምግብ አቅርቦት ችግር እንደሚጋለጡም አስጠንቅቋል። በረሃብ ለተጠቁ ገበሬዎች ዘር ለማከፋፈል በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 10 ሚሊዮን ዶላር መገኘት እንዳለበትና ይህ ካልሆነ ግን የተጠቂ ቤተሰቦች ህይወታቸውን በረሃብ ምክንያት ሊያጡ ይችላሉ ሲሉ ...
Read More »ለምግብ እጥረት የተጋለጡ የህጻናትና በእርግዝና ላይ እናቶች ቁጥር በእጥፍ ሊያድግ እንደሚችል ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ በመካከለኛ ደረጃ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ የህጻናትና በእርግዝና ላይ እናቶች ቁጥር በእጥፍ ሊያድግ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በመካከለኛ ደረጃ የተፈረጁ ህጻናትና እናቶች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን አካባቢ ቢሆንም ይህ ቁጥር በቅርቡ ወደ 2.5 ሚሊዮን ሊያሻቅብ እንደሚችል ትንበያ መኖሩን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። በሃገሪቱ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ዙሪያ ወቅታዊ ዝርዝር ሪፖርትን ያቀረበው ...
Read More »አንድ የዱባይ ኩባንያ የሶማሊላንድ ወደብን ከሶማሊ ላንድ ጋር በጋራ ለማልማት ስምምነት ፈጸመ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት የጎረቤት ሶማሊላንድ ወደብን ለመጠቀም ድርድር እያካሄደ ባለበት ወቅት መቀመጫውን በዱባይ ያደረገ አንድ ኩባንያ ወደቡን ከሶማሊላንድ ጋር በጋራ ለማልማት ስምምነት ፈጸመ። የጅቡትን ወደብ እያስተዳደረ የሚገኘውና ዲፒ ወርልድ (DPWorld) የሚል መጠሪያ ያለው ኩባንያ የሶማሊላንድ ወደብን ለማስተዳደር ስምምነት መፈጸሙን ለኢትዮጵያ አማራጭን የሚያሳጣ አካሄድ እንደሆነም በጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት አስታውቀዋል። መንግስት ከጅቡቲ ወደብ በየጊዜው የሚደረግበትን የአገልግሎት ክፍያ ...
Read More »በአርባምንጭ አካባቢ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን ወሰደ
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት 7 ለኢሳት በላከው ወታደራዊ መግለጫ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ውስጥ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው አንድ ቡድን ከሚያዝያ 29 ቀን እስከ ግንቦት 1 ቀን ባደረገው የመረረ ፍልሚያ ከሃያ በላይ የጠላት ወታደሮችን ገድሎ ከሃምሳ ያላነሱትን ማቁሰሉንና በጦርነቱም ከአርበኞች ግንቦት 7 ወገንም መስዋዕትነት ተከፍሎአል ብሎአል። “በወጣት አርበኞቻችን ጀግንነት፣ ...
Read More »በሃረሪ ክልል በኦህዴድና በሃብሊ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው፣ ክልሉን በሚያስተዳድሩት በኦህዴድና በሃረር ብሄራዊ ሊግ ፓርቲዎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በሃረር ከተማ ዙሪያ ከተገኑበት ቤቶች ጋር የተያያዘ ነው። የክልሉ መንግስት ከ2003 ዓም በሁዋላ በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን ቤቶች ለማፍረስ እንቅስቃሴ ቢጀምርም፣ከህዝቡ በደረሰበት ተቃውሞ ምክንያት ያሰበው ሳይሳከለት ቀርቷል። በአፍራሽ ግብረሃይልና በፖሊስ የተጋዘው ቤት የማፍረስ እንቅስቃሴ ሊሳካ አለመቻሉን ተከትሎ የምስራቅ እዝ ...
Read More »