ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ጥረት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 28 ፥ 2008) የሱዳን መንግስት የሃገሪቱን ግዛት በመጠቀም በሊቢያና ግብፅ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ጥረት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገለጸ። ባለፈው ወር ብቻ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ከ300 በላይ ስደተኞች ሱዳንን ከሊቢያ በሚያዋስናት የሃገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኮማንደር የሆኑት ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ለሱዳን ትሪቢዮን ጋዜጣ አስታውቀዋል። የስደተኞቹ ቁጥር መበራከትን ተከትሎ የሱዳን መንግስት ...

Read More »

መንግስት ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ በመመደብ ስኳርን ከህንድ ማስገባት ጀመረ

ኢሳት (ሰኔ 28 ፥ 2008) ለሃገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ገበያ ስኳርን ያቀርባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩ የስኳር ፋብሪካዎች ወደስራ አለመባታቸውን ተከትሎ መንግስት ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ በመመደብ ስኳርን ከህንድ ማስገባት ጀመረ። አራት የስኳር ኮርፖሬሽኖች ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ተመድቦላቸው ከሶስት አመት በፊት ስራ ይጀምራሉ ቢባሉም ፋብሪካዎቹ ግንባታቸው ገና አለመጠናቀቁ ታውቋል። ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና ስራቸው በመስተጓጎሉ ለኪሳራ ተዳርገዋል ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት አብዛኛውን ወታደራዊ ግዥ የሚፈጸመው  ከቻይና ኩባንያዎች ጋር መሆኑን ሰነዶች አመለከቱ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት የደረሱት ወታደራዊ የመሳሪያ ግዢን የሚያመላክቱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፣ መከላከያ ሰራዊት አብዛኛውን ግዢ የሚፈጽመውም ሆነ የእድሳት ስምምነትና እና የግንባታ ስራ የሚሰራው ከቻይናው North Industies Corporation ወይም በአጭሩ NORINCO ኩባንያ ጋር ነው። መከላከያ ከዚህ ኩባንያ ጋር በፈረንጆች አቆጣጠር እስከ 2013 ድረስ 440 ሚሊዮን 158 ሺ 409 አሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ...

Read More »

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች በወታደሮች ሲዋከቡ ዋሉ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፋብሪካው ሰራተኞች ለጂንካ ልማት በሚል ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው እየተቆረጠ መከፈሉን ሲቃወሙ የሰነበቱ ሲሆን ዛሬ ከ200 በላይ ወታደሮች ወደ ፋብሪካው በመግባት ሰራተኞችን ሲያስጨንቁ ውለዋል። ከደርጃ 1-13 የሚገኙ ሰራተኞች  በአንድ ድምጽ “አንከፍልም” በማለት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ተከትሎ በብሄር እየለዩ ለማጋጨት ሙከራ ሲደረግ መሰንበቱን ሰራተኞች ገልጸዋል። የአማራ ተወላጆች  “ልማት አደናቃፊ እና የድሮ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ቤት መከራየት አለመቻላቸውን ተናገሩ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክረምት መጠለያ አልባ የሆኑት የቀድሞ የሃና ማርያም አካባቢ ነዋሪዎች፣ ቤት ለመከራዬት እንኳን ስንጠይቅ፣ አከራዮቹ “ ‘እንዳታከራዩዋቸው’ የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል”  በሚል ቤታቸውን ሊያከራዩን ፈቃደኞች አልሆኑም ሲሉ ብሶታቸውን ገልጸዋል። ገዢው መንግስት ወጣቶችን እያደነ ማሰሩን መቀጠሉን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በእስር እና በግድያ መበቀሉ አንሶ አሁን ደግሞ ቤት እንዳንከራይ በመከልከል የበቀል ጅራፉን እያሳረፈብን ...

Read More »

ሶስት የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ መኪና ተገጭተው ህይወታቸው አለፈ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሟች ተማሪዎች በባጃጅ መኪና ሲጓዙ እንደነበር የገለጹት ተማሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ መኪና የተደሳፈሩበትን ባጃጅ መኪና ገጭቶ እንደገደላቸው  ታውቋል። አንደኛው ተማሪ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ መሞቱንና አስከሬኑ ወላጆቹ ወደሚገኙበት አዳማ ተልኳል። ሁለቱ ተማሪዎች በዚህ አመት የሚመረቁ ነበሩ። ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ይሁን ድንገተና አደጋ ለማወቅ አልተቻለም።

Read More »

ሱዳን ሊቢያ ድንበር አቅራቢያ 300 ስደተኞችን ያዘች

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን 300 ስደተኞችን መያዝዋን ሱዳን አስታወቀች። ስደተኞቹ የሳህራ በርሃን አቋርጠው ወደ ሊቢያ በመግባት በባሕር ወደ አውሮፓ ለማቅናት ሲጓዙ እንደነበር የሱዳን ልዩ ጦር የጸጥታ ሹም ጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ገልጸዋል። በሰሜናዊ ሱዳን አል ሸቨርሊት ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ አብዛሃኞቹ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን መሆናቸውንም አስታውቀዋል።። የሱዳን መንግስት ...

Read More »

ፍርድ ቤቱ የአቶ ሃብታሙ አያሌውን ጉዳይ ሳያየው ቀረ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህመም በመሰቃዬት ላይ ባለው  የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ ጠ/ፍርድ የጣለበት ከአገር ውጭ የመጓዝ እገዳ ይነሳለታል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አልተሟላም በሚል ውሳኔውን ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል። የአቶ ሃብታሙ ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው የፍርድ ቤቱን መልስ እንደሰማች ራሱዋን ስታ በመውደቋ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።

Read More »

የኢትዮጵያ ጦር የጋላድ ከተማን ለቆ ወጣ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታጠቁ የአልሸባብ ወታደሮች በማእከላዊ ሶማሊያ በጋለድቡ ክልል ውስጥ የምትገኘውን የጋላድ ከተማን ድጋሜ በቁጥጥር ስር አድርገዋል። በስፍራው በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ስም የነበሩት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸው ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ወታደሮች መሸሻቸውን ተከትሎ እኩለ ቀን ላይ የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎችና የከተማዋ ...

Read More »

የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ ከተካሄደው ዘመቻ ጋር በተገናኘ ከ200 በላይ ነዋሪዎች ለእስር ተዳረጉ

ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ዙሪያ “ህገወጥ” የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ ተካሄዶ በነበረው ዘመቻ ጋር በተገናኘ ከ200 በላይ ነዋሪዎች ለእስር ተዳረጉ። የመኖሪያ ቤታቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመፍረስ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች በጅምላ የእስራትና ድብደባ ድርጊት ሲፈጽሙ መሰንበታቸው ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቤት ማፍረሱን ድርጊት ለማስተባበር በተሰማራበት በዚሁ ዘመቻ ባለፉት ...

Read More »