ሶስት የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ መኪና ተገጭተው ህይወታቸው አለፈ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሟች ተማሪዎች በባጃጅ መኪና ሲጓዙ እንደነበር የገለጹት ተማሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ መኪና የተደሳፈሩበትን ባጃጅ መኪና ገጭቶ እንደገደላቸው  ታውቋል።

አንደኛው ተማሪ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ መሞቱንና አስከሬኑ ወላጆቹ ወደሚገኙበት አዳማ ተልኳል። ሁለቱ ተማሪዎች በዚህ አመት የሚመረቁ ነበሩ። ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ይሁን ድንገተና አደጋ ለማወቅ አልተቻለም።