ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) በመገንባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ላለፉት አራት አመታት ሲወዛገቡ የቆዩት ግብፅ፣ ኢትዮጵያና፣ ሱዳን፣ ልዩነቶቻቸን በማጥበብ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ። በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚወዛገቡት ግብፅና ኢትዮጵያ ግብጽ ባቀረበችው የትብብር ሰነድ ላይ ስምምነታቸውን መግለጻቸውን የግብፅና የሱዳን መገናኛ ብዙሃን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋቢ በማድረግ ትናንት ዕሁድ ዘግበዋል። በግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በመርህ ደረጃ የተስማሙበትን ጉዳይ አስመልክቶ የሱዳን ...
Read More »በአዲስ አበባ መጽሃፍ አዟሪዎች እየታሰሩ ነው ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች መጽሃፍ በማዞር የሚተዳደሩትን ዜጎች እያሰሩ እንደሚገኙ ተገለጸ። መጽሃፍት አዟሪዎቹ “ኅብረተሰቡን ለአመፅ የሚገፋፉና ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ መጻሕፍት በማዘዋወርና በመሸጥ” በሚል ክስ እንደተወነጀሉ በአገር ውስጥ የሚታተሙ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር የዋሉት መጽሃፍት አዟሪዎች በተለይም በአዲስ አበባ በተለያዩ እርስ ቤቶች ታስረው የሚገኙ ሲሆኑ፣ እስካሁን ድረስ ለተጠረጠሩበት ...
Read More »በአማራ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደሌሎች አካባቢዎችም እየተስፋፋ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘው ሳምንት ወደ አዳዲስ አካባቢዎች መዛመቱን ተከትሎ፣ የአገዛዙ ሃላፊዎች በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንደገቡና ህዝባዊ ተቃውሞንም በሃይል ለመጨፍለቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ እንደሆነ ተነገረ። ህዝባዊ ተቃውሞ በተለይም በሰሜን በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ...
Read More »በአማራ ክልል የሚካሄዱ ህዝባዊ አመጾች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ነሃሴ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር የተጀመረውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ወታደሮች ለችግረኛ ወጣቶች እርዳታ ለማሰባሰብ በሞከሩ ወጣቶች ላይ በወሰዱት እርምጃ ህዝቡ በመቆጣት ከተቃውሞውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጽ ውሎአል። ከባህርዳር በ15 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ መሸንቲ ከተማ ደግሞ 2 አበባ እርሻዎችና የተለያዩ መኪኖች ተቃጥለዋል። አካባቢው ለትራንስፖርት ዝግ ሆኗል። ከባህርዳር በ30 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ...
Read More »በአማራ ክልል ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) ባለፉት ሳምንታት በአማራ ክልል በሚገኙ በተለያዩ ከተሞች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሳምንቱ መገባደጃ በአዊ፣ በምዕራብ ጎጃምና፣ በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ትናንት እሁድና ዛሬ ሰኞች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ። ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እየተደረገ ባለው የነጻነት ትግል፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በእንጅባራ (ኮሶበር)፣ በቲሊሊ፥ በአዴት፣ በቻግኒ፣ መራዊ፣ መሸንቲና በመሳሰሉ ከተሞች ትናንት እሁድና ዛሬ ሰኞ የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ...
Read More »የውሃ አጠቃቀም ችግር በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 18 ፥ 2008) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚታየው የውሃ አያያዝ ችግር በህዝቡ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተገለጸ። በውሃ አያያዝ ችግር የሚከሰተው ድርቅና ጎርፍ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ሄለን ፓርከት የተባሉ የወተር ኤይድ የስትራቴጂ ባለሙያ በሮይተርስ ድረገጽ ላይ ባወጡት ጥናታዊ ጽሁፍ ገልጸዋል። በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በመከሰቱ ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን አዝመራ እንደወደመባቸው ...
Read More »በአብድራፊ ከተማ በትግራይ ልዩ ሃይል አባላትና በነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውጥጥ እየተካሄደ ነው
ነሃሴ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአብድራፊ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ባለሀብቱ አቶ ታያቸው በአብድራፊና አብርሃ ጅራ መሃል ኮረደም ቴሌ በሚባል ቦታ ላይ በትግራይ ክልል ልዩ አባላት መደገላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮአል። በፓትሮል መኪና የመጡ ወታደሮች አቶ ታያቸውን ከመኪና አውርደው ከደሉዋቸው በሁዋላ፣ ተመሳሳይ ተልእኮ ይዘው በመምጣት አቶ በርጃለው የተባሉ የልዩ ሃይል አባልን ገድለዋቸው አምልጠዋል። በእርምጃው የተበሳጨው ...
Read More »በአማራ ክልል በቡሬ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ
ነሃሴ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ፣ ጅጋና ማንኩሳ ከተሞች ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄድ ከቆዩ በሁዋላ፣ ተቃውሞው ወደ አጎራባች ከተሞች በመሸጋገር ዛሬ አርብ በቡሬና ቋሪት ከተሞች ተቀጣጥሎ ህዝቡ ከወታደሮች ጋር ሲፋለም ውሎአል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በቡሬ ሲሆን አንድ ሰው ሲገደል ከሶስት አላነሱ ቆስለዋል። አንዳንድ ወገኖች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 2 ነው ይላሉ። ...
Read More »በአዘዞ የሚገኙ ወታደሮች ግድያውን በእነሱ ስም የሚፈጽሙት የህወሃት ልዩ ሃይል አባላት ናቸው አሉ
ነሃሴ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወታደሮቹ እንደሚሉት የኦሮሞ፣ አማራ እንዲሁም የደቡብ ክልል ወታደራዊ አዛዦች በሰሜን ጎንደር በሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አመራር መስጠት አቁመዋል። 3 ወታደራዊ አዛዦችን የገደሉ ከ70 ያላነሱ የሰራዊት አባላት አለመመለሳቸውንም የ24ኛ ው ክ/ጦር አባላት ተናግረዋል። ወታደሮች በህዝብ ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወሰዱም ምክራቸውን ለግሰዋል ሰሞኑን በርካታ የጦር መሳሪያዎች በወለቃ፣ እና በገነት ተራራ አካባቢዎች ወድቀው ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚገኙ መንግስት እየመራቸው ያሉ የመገናኛ ብዙሃን በመረጃ እጥረት ተመተዋል
ነሃሴ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ፤ የአማራ ና የኦሮምያ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች በየአካባቢው በተነሳው ህዝባዊ አመፅ የተነሳ ጋዜጠኞቻቸው እንደልብ መጓጓዝ ባለመቻላቸው ምክንያት በመረጃ እጦት ምክንያት ጣቢያዎች ዜናቸውን በሰአቱ ለመሸፈን አልተቻላቸውም፡፡ ከየወረዳዎች ይደርሱ የነበሩት የልማት ዜናዎች እና የተለመዱት ስበሰባዎች በመቆማቸው ምክንያት፣ የአየር ስዓታቸውን በተገቢ ሁኔታ መሸፈን አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ስዓት ዘገባዎችን በመንግስት ...
Read More »