በኢትዮጵያ የሚገኙ መንግስት እየመራቸው ያሉ የመገናኛ ብዙሃን በመረጃ እጥረት ተመተዋል

ነሃሴ  ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ፤ የአማራ ና የኦሮምያ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች  በየአካባቢው በተነሳው ህዝባዊ አመፅ የተነሳ  ጋዜጠኞቻቸው እንደልብ መጓጓዝ ባለመቻላቸው ምክንያት በመረጃ እጦት ምክንያት ጣቢያዎች  ዜናቸውን በሰአቱ ለመሸፈን አልተቻላቸውም፡፡

ከየወረዳዎች ይደርሱ የነበሩት የልማት ዜናዎች  እና የተለመዱት ስበሰባዎች በመቆማቸው ምክንያት፣  የአየር ስዓታቸውን በተገቢ ሁኔታ መሸፈን አልቻሉም፡፡

በአሁኑ ስዓት ዘገባዎችን በመንግስት ካድሬዎች  እየተመሩ  ቀበሌ ሂደው እንደሚቀርፁ ለኢሳት የተናገሩት ጋዜጠኞች፣ ህዝቡ በምንም ዓይነት መልኩ አስተያየቱንም ሆነ ድምፁን ለመንግስት ሚዲያዎች መስጠት አይፈልግም ብለዋል።