በጎንደር የከተራ በአል እጅግ በተቀዛቀዘ ስሜት ተከበረ

ጥር ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አብዛኛው የጎንደር ህዝብ በአካባቢው የሚፈጸመውን ከፍተኛ የመብት ጥሰት በመቃወም የዘንድሮው የከተራ በአል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቀዘቀዘ ስሜት መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።ከዚህ በፊት የነበሩት ስርዓቶች በአብዛኛው የቀሩ ሲሆን፣ ታቦታቱ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ፖሊሶችና በተወሰኑ ምዕመናን ታጅበው እንዲወጡ ተደርጓል። በገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ጫና የበአሉ ስነሰርዓት እንዲከበር ቢደረግም፣ ወጣቶች በቡድን በመሆን የተቃውሞ ድምጾችን ሲያሰሙ እንደነበር ...

Read More »

በጎራጌ ዞን አርሶአደሮች  ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ  እንዲከፍሉ ተገደዱ

ጥር ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን የአካባቢው ነዋሪዎችን በመጥቀስ  እንደዘገበው አርሶአደሮቹ ለመሬት ግብር በሚፍሉበት ወቅት 100 ብር ተጨማሪ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍሉ ተገደዋል። አዲሱ የተጣለው መመሪያ በእጅጉ እንዳበሳጫቸው አርሶአደሮች ተናግረዋል። በአመት 400 ብር የመሬት ግብር ይከፍሉ የነበሩ አርሶአደሮች አሁን 500 ብር ከዚህም በላይ የሚከፍሉትም በተመሳሳይ እየታሰበ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው።

Read More »

የባለስልጣናት ጥቅማጥቅሞች ዝርዝር

ጥር ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከስልጣን የሚለቁ የገዢው ፓርቲ ሹመኖች ቀድሞ ያገኙት ስለነበረው ጥቅም በፊት የነበረው አዋጅ መሻሻሉን በተመለከተ ትናንት በዜና ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወሳል። አዋጁን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች ደርሰውናል ገዢው ፓርቲ ከስልጣን የሚሰናበቱ ባለስልጣናትን ጥቅማጥቅሞች ለማስከበር ቀደም ብሎ አዋጅ ቁጥር 653/2001ን አውጥቶ ላለፉት 7 ዓመታት ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። ይሁን እንጅ አዋጅ ለማሻሻል በሚል  ጥር 9፣ ...

Read More »

የአጋዚ ጦር አባላት መከላከያን በብዛት እየለቀቁ ነው

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገዛዙ ወደ ሶማሊያና ሱዳን በሰላም አስከባሪ ስም በሚልካቸው ወታደሮች ላይ የማእረግ ማጭበርበር እየፈጸመ ገንዘብ እንደሚያገኝ የአጋዚ የህግ ክፍል ኤክስፐርት አስታውቋል። የአጋዚ ኮማንዶ እና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ የህግ ሰነድ እና ዝግጅት ኤክስፐርት የነበረው ሃምሳ አለቃ ወደ ሶማሊያ ሰላም አስከባሪ አባል ሆኖ ሲሄድ ሻለቃ ተብሎ የተሰየመው ሃምሳ አለቃ ኃ/ሚካኤል በእውቀቱ ጋሻዬ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የጥምቀት በአል አከባበር ከመቼውም ጊዜ በላይ የተቀዛቀዘ ይሆናል ተባለ

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የሰሜን ጎንደር ወኪል እንደዘገበው፣ ከዚህ በፊት የጥምቀትን በአል ለማክበር ይደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በዚህ አመት አልተደረጉም። የሃይማኖት አባቶች የሆኑት የአቡነ አብርሃ እና አባ ቀለመወርቅ መታሰር እንዲሁም በዞኑ የሚፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ የሃይማኖት አባቶች በአሉን በተቀዛቀዘ ስሜት ለማክበር እንዲወስኑ አድርጓቸዋል። የወረዳው ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት ህዝቡ ቢያምንበትም ባያምንበትም በአሉ እንዲከበር የሚል ትእዝዛ ...

Read More »

ከኃላፊነት የሚነሱ ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንትን ጥቅማጥቅም ለማሻሻል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ  ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት ሰባት ዓመታት የሀገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለለስልጣናት፣ የፓርላማ አባላትና ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችና መብቶችን በአዋጅ ቁጥር 653/2001 አማካይነት ሲያገኙ የቆዩ ቢሆንም፣  ዛሬ ማክሰኞ፣ ጥር 9 ቀን 2009 ዓም ለፓርላማው የቀረበው አዋጅ በተለይም የሚኒስትሮች፣ የሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የምክትል ሚኒስትሮች የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት(የተሸከርካሪ) ...

Read More »

በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ መንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ባደረጉት ሪፖርት በድርቅ ለተጎዱ 5 ሚሊዮን 600 ሺ ኢትዮጵያውያን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚሆን 948 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል። አብዛኛው ገንዘብ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ዜጎች የሚውል ነው። ከዚህ ውስጥ የኢህአዴግ መንግስት 47 ሚሊዮን ዶላር ...

Read More »

በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ባለፈው ሳምንት የደረሰውን የቦምብ አደጋ ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ተገለጸ

(ጥር 9 ፥ 2009) ሰሞኑን በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የደረሰን የቦምብ አደጋ ተከትሎ በሁለቱ ከተሞች ውጥረት መንገሱን የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ገለጸ። የጥምቀት በአል አከባበርን አስመልክቶ በሁለቱ ከተሞች ተጨማሪ ጥቃት ሊደርስ ይችላል ሲል ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱንም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎቹ ባሰራጨው የጉዞ ጥንቃቄ መረጃ አመልክቷል። ይሁንና ፖሊስ ሊደርስ ይቻላል ስላለው ተጨማሪ ጥቃት የሰጠው ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ በሁለቱ ከተሞች ...

Read More »

ድርቅ በተከሰተባቸው ክልሎች 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ

(ጥር 9 ፥ 2009) አዲስ የድርቅ አደጋ በተከሰቱባቸው አራት ክልሎች ወደ 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች በድርቁ ሳቢያ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በአፋር ኦሮሚያ፣ ደቡብና የሶማሊ ክልሎች ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል። ይህንኑ የድርቅ አደጋ መባባስ ተከትሎ 23ሺ 764 ቤተሰቦች ከመኖሪ8ያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለአስቸኳይ ...

Read More »

ባለፈው የፈርንጆች አመት በሶማሊያ በተሰማሩ የኬንያ ወታደሮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 173 ወታደሮች መገደላቸው ተገለጸ

(ጥር 9 ፥ 2009) ኬንያ ባለፈው አመት በሶማሊያ በሚገኘው አንድ የጦር ማዘዣ ጣቢያዋ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 173 ወታደሮቿን ማጣቷን ይፋ አደረገች። ሃገሪቱ በአልሸባብ ታጣቂ ሃይል የደረሰባትን ጉዳት ለመገናኛ ብዙሃን ግልጽ ከማድረግ ተቆጥባ ብትቆይም የኬንያ ወታደራዊ ባለስልጣናት በጥቃቱ 173 ወታደሮች መሞታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳወቃቸውን ዘስታንዳርድ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። በሶማሌ ኤል አዴ ተብሎ በሚጠራው የኬንያ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ጥቃቱ ...

Read More »