በጎራጌ ዞን አርሶአደሮች  ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ  እንዲከፍሉ ተገደዱ

ጥር ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-ወኪላችን የአካባቢው ነዋሪዎችን በመጥቀስ  እንደዘገበው አርሶአደሮቹ ለመሬት ግብር በሚፍሉበት ወቅት 100 ብር ተጨማሪ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍሉ ተገደዋል።

አዲሱ የተጣለው መመሪያ በእጅጉ እንዳበሳጫቸው አርሶአደሮች ተናግረዋል።

በአመት 400 ብር የመሬት ግብር ይከፍሉ የነበሩ አርሶአደሮች አሁን 500 ብር ከዚህም በላይ የሚከፍሉትም በተመሳሳይ እየታሰበ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው።