በአዲስ አበባ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተከሰተ

ኢሳት (የካቲት 3 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተ ከፍተኛ የውሃ ዕጥረት አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለምግብ ማብሰያነት የወንዝ ውሃ እስከመጠቀም መድረሳቸው ተገለጸ። ሆቴሎችም በተከሰተው ከፍተኛ የውሃ እትረት እንግዶችን በተገቢው ላምስተናገድ መቸገራቸውም ተመልክቷል። የውሃ ዕጥረቱ ለውሃ ወለድ በሽታዎች መንስዔ ሆኗል። በከተማዋ በጉለሌና የካ ክፍለ ከተሞች ብቻ የውሃ አቅርቦ ከተቋረጠ ከሁለት ወር በላይ መቆጠሩንና ነዋሪዎችን ለጤና ችግሮችና ለማህበራዊ ቀውሶች መዳረጋቸውን ከሃገር ቤት ...

Read More »

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰባት አገር ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ያወጡት መመሪያ በፌዴራል ፍ/ቤት ውድቅ ተደረገ

ኢሳት (የካቲት 3 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰባት ሃገራት ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ያወጡት መመሪያ በሃገሪቱ የፌዴራል ይግባኝ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ተደረገ። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ በሲያትል ዋሽንግተ የተሰየመው የፌዴራል ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቱ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ያወጡት አጨቃጫቂ መመሪያ የሃገሪቱን ህገመንግስት የሚጻረር ነው ሲል ሃሳቡ ውድቅ እንዲሆን ውሳኔ መሰጠቱ ይታወሳል። ይሁንና የፕሬዚደንት ትራምፕ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ...

Read More »

እንደ ኦሮምያና አማራ ሁሉ የደቡብ ክልል የመንግስት ሰራተኞችም በጥልቅ ተሃድሶ ስም የቀረበውን ሪፖርት ተቃወሙ

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ በዞኑ የሚገኙ ሰራተኞች ጥልቅ ተሃድሶ ለማድረግ በሚል ከሰኞ ጥር 29 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ አዳራሽ እያደረጉት ባለው ስብሰባ ላይ ፣ ለውይይት መነሻ ሆኖ የቀረበውን ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል። የውውይት መነሻ ጽሁፉ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ከቀድሞ ስርአቶች ጋር ሲነጻጻር የተሻለ ድል ...

Read More »

በሚዳ ወረሞ የቅስቀሳ ወረቀቶች ተበትነው ማደራቸውን ተከትሎ ወጣቶች ታሰሩ

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ሬማ ንኡስ ወረዳ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚያሳስቡ በራሪ ወረቀቶች ተብትነዋል። ይህንን ተከትሎ ወጣት አብዩ ሰኢድና ወጣት ግርማ ፈሊ በፖሊሶች ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን ግርማ ማምሻውን መፈታቱ ታውቋል። ወረቀቱ ከወረዳ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ለተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣ የሚቀሰቅስ ቢሆንም፣ “በጎንደር የፈሰሰው የህዝብ ደም በከንቱ ...

Read More »

በጅቡቲ መስመር ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የሚያመላልሱ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች እንደተናገሩት ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በአዋሽ 7 ኬላ ላይ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሃደ በመሆኑ በስራቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በአሁኑ ሰአት መኪኖች ከ3 እስከ 5 ኪሜትሮች የሚደርስ ሰልፍ ሰርተው ለመፈተሽ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ፣ ፍተሻው ከዚህ ቀደም ከነበረው የተጠነከረ ነው ይላሉ። ...

Read More »

ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከባንክ አክሲዮን ለማስወጣት የተወሰደው እርምጃ በግል ባንኮች ላይ ስጋት አሳደረ፡፡

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ የኢትዮጵያዊያን ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በባንኮችና የመድን ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች ውስጥ ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲመልሱ ባዘዘው መሠረት በተለይ አንዳንድ ባንኮች የካፒታል አጣብቂኝ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ፡፡ ባለሙያዎቹ እንደሚሉት አንዳንድ ባንኮች በርካታ ቁጥር ያላቸው ...

Read More »

የጃማይካ ተወላጆች ዜግነት የሚያገኙበት ህጋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኢትዮጵያና ጃማይካ ምክክር መጀመራቸው ተነገረ

ዜና (የካቲት 2 ፥ 2009) ኢትዮጵያና ጃማይካ በኢትዮጵያ የሚገኙ የጃማይካ ተወላጆች ዜግነት የሚያገኙበት ህጋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከር መጀመራቸውን የጃማይካ መገኛኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። በጃማይካ ጉብኝትን እያደረጉ የሚገኙት በአሜሪካ፣ ጃማይካና፣ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ሃገራት የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ግርማ ብሩ ኢትዮጵያና ጃማይካ በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን እንዳስታወቁ ጃማይካ ኦብሰርቨር የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። ወደ 500 የሚጠጉ የጃማይካ ተወላጆች በኢትዮጵያ በተለይ ...

Read More »

የበልግ ዝናብ ባለመጀመሩ ምክንያት የድርቅ መባባስ ስጋት መኖሩን ተመድ ገለጸ

ዜና (የካቲት 2 ፥ 2009) በደቡብ እና ደቡባዊ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተያዘው ወር መጣል የነበረበት የበልግ ዝናብ ባለመጀመሩ ምክንያት የድርቅ መባባስ ስጋት መኖሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በበኩሉ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ከተጋለጡ 5.6 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 2.5 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆኑት በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። ካለፈው ሃምሌ ወር ጀመሮ በአራት ክልሎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በኦሮሚያ ክልል ...

Read More »

የቀድሞ የሶማሊያ ጠ/ሚኒስትር አብዱላሂ ሞሃመድ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ

ዜና (የካቲት 2 ፥ 2009) የቀድሞ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ሞሃመድ የሃገሪቱ አዲሱ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ። ረቡዕ ከፍተኛ ጥበቃ በተደረገበት ሁኔታ ሞቃዲሾ በሚገኝ የአየር ማረፊያ በተካሄደው በዚሁ የፓርላማ አባላት ድምፅ የመስጠት ሂደት ፕሬዚደንት አብዱላሂ 184 ድምፅ በማግኘት ለድል መብቃታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። 20 የሚሆኑ ተፎካካሪዎች ለውድድር ቀርበው በነበሩት በዚሁ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በስልጣን ላይ የነበሩት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ 97 ድምፅን ብቻ በማግኘታቸው ...

Read More »

የውጭ ምንዛሪ ገቢ በ3 ቢሊዮን ብር መቀነሱ ተነገረ

ዜና (የካቲት 2 ፥ 2009) ባለፉት ስድስት ወራቶች ኢትዮጵያን ከጎበኙ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ በ145 ሚሊዮን ዶላር (በ3 ቢሊዮን ብር) አካባቢ መቀነሱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሃሙስ አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል ለአንድ አመት ያህል የዘለቀውና በሃምሌ ወር 2008 አም በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በቱሪዝም ገቢው እንዲቀንስ አስተዋጽዖ ማድረጉን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። በሃገሪቱ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሲባል በትቅምት ...

Read More »