በሚዳ ወረሞ የቅስቀሳ ወረቀቶች ተበትነው ማደራቸውን ተከትሎ ወጣቶች ታሰሩ

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ሬማ ንኡስ ወረዳ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚያሳስቡ በራሪ ወረቀቶች ተብትነዋል።
ይህንን ተከትሎ ወጣት አብዩ ሰኢድና ወጣት ግርማ ፈሊ በፖሊሶች ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን ግርማ ማምሻውን መፈታቱ ታውቋል።
ወረቀቱ ከወረዳ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ለተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣ የሚቀሰቅስ ቢሆንም፣ “በጎንደር የፈሰሰው የህዝብ ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተካተውበታል።