አቶ መላኩን ጨምሮ 10 የሚሆኑ የጉምሩክ ሃላፊዎች በቀረበባቸው አንደኛ ክስ እንዲከላከሉ ተወሰነ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ሃላፊ የነበሩትን አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 10 ሃላፊዎች በቀረበባቸው አንደኛ ክስ እንዲከላከሉ ተወሰነ። ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በባለስልጣኖቹ ላይ ብይኑን ይሰጣል ተብሎ በተጠየቁበት ወቅት በስፍራው ያለው ድምፅ ችሎቱ ለመሰየም አያስችልም በሚል ቀጠሮውን ለሁለት ጊዜ አራዝሞ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ችሎቱን ወደ ቃሊቲ ሲያዞር አስቀድሞ ሁኔታዎችን ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን መድረሱን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል አዲስ የተከሰተው የድርቅ አደጋ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑንና ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 1.7 ሚሊዮን አካባቢ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ድርቁ እያደረሰ ባለው ጉዳት ከመኖሪያ ቀያቸው የሚፈናቀሉ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ወደ 168 ሺ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሊ ክልል ጉዳት እያደረሰ ያለው ይኸው የድርቅ አደጋ ስጋት እያሳደረ መምጣቱን ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ረሃብ መከሰቱ የተባበሩት መንግስታት ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) በደቡብ ሱዳን ሁለት ግዛቶች ረሃብ መከሰቱን እና የ100ሺ ሰዎች ህይወት አደጋ ውስጥ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ይፋ አደረገ። በደቡብ ሱዳን ለሶስት ተከታታይ አመታት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት እንዲሁም በቅርቡ በሃገሪቱ የተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለረሃብ መከሰት አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። አቅም ያገኙ ደቡብ ሱዳናውያን ረሃቡን በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ በመሰደድ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ደቡብ ...

Read More »

በዝርፊያ ወንጀል የሚጠረጠሩ የቀድሞ የልማት ባንክና የንግድ ባንክ ባለስልጣናት ከአገር መኮብለላቸው ታወቀ

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአብዛኛው የቀድሞ የህወሃት የጦር መኮንኖችና አባላት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንክ እንዲበደሩ በማድረግ በጋምቤላ ሰፋፊ መሬቶችን እንዲገዙ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸው የሚነገርላቸው የልማት ባንክ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረን ጨምሮ ሌሎች የልማት ባንክ እና የንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች ከአገር መውጣታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ድርጊቱ ግለሰቦቹንና ከእነሱ ጀርባ ያሉትን ባለስልጣናት ሆን ...

Read More »

ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች የአዲስ አበባ ፋርማሲዎችን አጥለቅልቀዋል

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መገኛ ምንጫቸው በትክክል የማይታወቁና በኮንትሮባንድ ጭምር እንደሚገቡ የሚነገርላቸው የተለያዩ መድሃኒቶች በአዲስአበባ በሚገኙ በአንዳንድ ሕጋዊ መድሃኒት መሸጫ ፋርማሲዎች፣ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች እየተቸበቸቡ ነው፡፡ መድሃኒቶቹ በተለያዩ መጠቅለያዎች ተጀቡነው ድንበር አቋርጠው የሚገቡ መሆናቸውን፣ ከመንግሥት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በአንዳንድ ምግባረ ብልሹ ሠራተኞች እየተመዘበሩ በፌስታልና በመሳሰሉ ጥንቃቄ በጎደላቸው መያዣዎች ወደፋርማሲዎቹ እንደሚሸጋገሩ ፍንጭ መኖሩን ከጤና ቢሮው ...

Read More »

በአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ምክንያት 100 ሺህ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ አለመምጣታቸው ተዘገበ

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት የተለያዩ አገራት ማንኛውንም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የጉዞ እቀባ መጣላቸውን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቁጥራቸው ከ100 ሺህ በላይ አገር ጎብኚ ቱሪስቶች መቅረታቸውን የጁሚያ ትራቭል ጥናትን በመጥቀስ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ከሁለት ዓመት በፊት 900 ሺህ ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ...

Read More »

የአሜሪካ የምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲያቆም ጠየቁ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ  መብት ጥሰቶች ዕርምጃ እንድትወስድ ለሃገሪቱ ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብን ያቀረቡ የምክር ቤት አባላት፣ የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲያቆም ጠየቁ። በዚህ በአሜሪካ የኒውጀርሲና የኮሎራዶ ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላት የሆኑት ሚስተር ክሪስ ስሚዝ እና ማይክ ኮፍማን ገዢው የኢህአዴግ መንግስት ተቃዋሚ አካላትን ለማጥፋት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እየፈጸመ ...

Read More »

ግልገል ጊቤ ሶስተኛው የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት የቱርካና ሃይቅ ላይ የውሃ መበከልን ሊያስከተል ይችላል ሲል የኬንያ መንግስት ቅሬታን አቀረበ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) የኬንያ መንግስት በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት የጀመረው ግልገል ጊቤ ሶስተኛው የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት በአካባቢው በሚገኘው የቱርካና ሃይቅ ላይ የውሃ መበከልን ሊያስከተል ይችላል ሲል ቅሬታን አቀረበ። የሃገሪቱ የአካባቢ ሚኒስትር የሆኑት ጁዲ ዋኩንጉ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑት የተፈጥቶ ሃብቶች ጥቅም ላይ በሚውሉ ጊዜ አለም አቀፍ ህጎችን መሰረት ያደረገ ስምምነት ግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት መግለጻቸውን ዲይሊ ኔሽን ...

Read More »

በዚምባብዌ ፍርድ ቤት ከቀረቡት 56 ኢትዮጵያውያን 8ቱ ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገቡ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) በህገወጥ መንገድ ወደ ዚምባቢዌ ገብታችኋል ተብለው ለእስር ከተዳረጉ 56 ኢትዮጵያውያን መካከል 8ቱ ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን የዚምባብዌ ባለስልጣናት አርብ ገለጹ። ስደተኛ ኢትዮጵውያኑ የተመሰረተባቸውን ክስ ለመስማት በማታቤላንድ ግዛት ስር በምትገኘው የግዋንዳ ከተማ ቢገኙም ሳምንት በችሎቱ ፊት ራሳቸውን ስተው እንደወደቁና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዚምባብዌ ፖሊስ ለመገኛኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ በፍርድ ቤቱ በተገኙ ...

Read More »

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ባለፉት 15 አመታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ባለፉት 15 አመታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ሃገሪቱ ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አንድ ተቋም በጉዳዩ ዙሪያ ያካሄደውን ጥናት ዋቢ በማድረግ አርብ ይፋ አደረገ። እንደፈረጆቹ አቆጣጠር እስከ 2015 አም ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ዜጎች ቁጥር 2.1 ሚሊዮን ሲሆን፣ ከዚሁ ቁጥር መካከል 222ሺ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ፒው (PEW) የተሰኘ የምርምር ...

Read More »