መድረክ ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ለመነጋገር ሃሳብ አቀረበ

መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተደረገ ባለው 22 ፓርቲዎች የፖለቲካ ድርድር መድረክ ላይ፣ የመድረኩ ተወካይ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ድርድሩ በኢህአዴግና በመድረክ መካከል ብቻ ሊካሄድ ይገባል ብለዋል። ኢህአዴግ ገዢ ፓርቲ በመሆኑ፣ መድረክ ደግሞ የአገሪቱ ዋነኛ ፓርቲ በመሆኑ ድርድሩ በሁለቱ መካከል ሊሆን ይገባል ሌሎች ፓርቲዎች ግን በተሳፊነት ብቻ መቅረብ አለባቸው ብለዋል። ኢህአዴግ በበኩለ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በፓርላማ ወንበር ...

Read More »

ለወራት በእስር ላይ የነበሩት መምህር አለማየሁ መኮንን ተፈቱ

መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወታደራዊ እዙ ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የቆዩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ምክትል ሊቀመንበር መምህር ዓለማዬሁ መኮንን በ3000 /ሦስት ሺህ) ብር ዋስ ተፈተዋል፡፡ አቶ አለማየሁ ከእርሳቸው ጋር የነበሩት ሌሎች 10 እስረኞች ሲለቀቁ እርሳቸው ብቻ ታስረው እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር። በሌላ በኩል በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ወልደሃና መጋቢት ...

Read More »

በቆሼ በደረሰው አደጋ ሟቾችን በፍጥነት የማውጣት ስራ ባለመሰራቱ አሰከሬን መሽተት ጀምሯል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቆሸ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ፣ ሟቾችን በፍጥነት ለማውጣት ባለመቻሉ የአስከሬኑ ሽታ ከቆሻሻ ሽታው ጋር ተደማምሮ ፍለጋውን አስቸጋሪ አድርጎታል። የኢህአዴግ አገዛዝ ሁለት ስካቫተር እና 3 አምቡላንስ መኪኖችን ብቻ በማቅረቡ፣ ፍለጋው እንዲጓተትና በህይወት የተረፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንዲስተጓጎል እያደረገ ነው የሚል ትችት ከቀረበበት በሁዋላ፣ ትናንት ሁለት ተጨማሪ ስካቫተር መኪኖችን ...

Read More »

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከስልጣናቸው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል

መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ስብሰባ ከመጋቢት 4/2009 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ሃሙስ በሚደረገው ስብሰባ ጉባዔው አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከስልጣን በማንሳት፣ አማራን በመዝለፍና በማዋረድ የሚታወቁትን አቶ አለምነው መኮንንን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ የካቢኔ አባላት ህዝቡን ለማረጋጋት አቶ ገዱ ለ3 ወራት ያክል በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ሃሳብ ያቀረቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ባለው ...

Read More »

ከዋልድባ ገዳም ታፍነው የተወሰዱት አባ ገብረኢየሱስ እስካሁን ያሉበት አድራሻ አልታወቀም

መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጥንታዊው እና ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ስም ውድመት እንዲደርስ መደረጉን በመቃወም ባለባቸው ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ገዳሙን በመወከል ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአካልና በደብዳቤ ያቀረቡት አባ ገብረኢየሱስ በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም። በገዳሙ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ሲሰጡ የነበሩትን የአባ ገብረኢየሱስን በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው ...

Read More »

የታይላንድ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ የተጓጓዘው የአውራሪስ ቀንድ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላትን ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆናቸውን ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) የታይላንድ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ከተጓጓዘውና በሃገሪቱ አለም አቀፍ አውሮፓላን ማረፊያ ማክሰኞ ከተያዘው 21 የአውራሪስ ቀንድ ዝውውር ጋር የተገናኙ አካላት ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸውን አስታወቁ። አምስት ሚሊዮን ዶላር (ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ) ግምት ያለው ይኸው የአውራሪስ ቀንድ በአየር ማረፊያው በጥርጣሬ በተካሄደ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ ዘግቧል። መነሻውን ከኢትዮጵያ ያደረገው ሻንጣ ለመረከብ በአየር ማረፊያው ከቬይትናምና ከካምቦዲያ የተጓዙ ሁለት ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤል ክልል ጥቃት ፈጽመው 28 ሰዎችን ሲገድሉ 43 ህጻናትን ጠልፈው መውሰዳቸው ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) ሰሞኑን ከደቡብ ሱዳን ድንበር በመዝለቅ በጋምቤላ ክልል ጥቃት የፈጸሙ ታጣቂዎች 28 ሰዎች መግደላቸውንና 43 ህጻናትን ዳግም አግተው መውሰዳቸውን መንግስት አረጋገጠ። የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት በፈጸሙት ጥቃት ከ100 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውንና ወደ 125 አካባቢ የሚደርሱ ህጻናት ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል። ይኸው ጥቃት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በድጋሚ መፈጸሙንና በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ኢሳትና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ...

Read More »

በሴት ልጁ ላይ ግርዛት ፈጽሟል የተባለ ኢትዮጵያዊ ከ10 አመት የእስር ቅጣት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) ነዋሪነቱ በዚሁ በአሜሪካ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ በሴት ልጁ ላይ ፈጽሞታል በተባለ ግርዛት ከ10 አመት የእስር ቅጣት በኋላ ሰኞ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ተደረገ። ነዋሪነቱ በጆርጂያ ግዛት የነበረው የ41 አመቱ ካሊድ አህመድ ከ10 አመት በፊት በሁለት አመት ህጻን ልጁ ላይ የፈጸመው ግርዛት በአሜሪካ ታሪክ የተከለከለና ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ እንደነበር ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የፍርድ ቤት ውሳኔን ዋቢ ...

Read More »

በተለምዶ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁፋሮ የሚገኝ አስከሬን መጨመሩን ተከትሎ ሰዎች ወደቦታው እንዳይገቡ ታገዱ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) በአዲስ ከተማ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነውና በተለምዶ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በየዕለቱ በቁፋሮ የሚገኝ አስከሬን መጨመሩን ተከትሎ ሰዎች ወደቦታው እንዳይገቡ ታገዱ። የቤተሰብ አባሎቻቸው የገቡበት ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ቁፋሮን የማካሄዱ ስራ ተጓትቷል በማለት ቅሬታን እያቀረቡ መሆኑን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በዚሁ ድርጊት ቁጣቸውን እየገለጹ የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ ለመጓዝ ቢሞክሩም ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ስፍራዎች ጥቃት ፈጸሙ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ ስፍራዎች ማክሰኞ ምሽት ጥቃት ፈጸሙ። ከአይን ምስክሮችና ከንቅናቄው ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለው በጭልጋ፣ ደንቢያና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀንና በተቀራራቢ ሰዓት በመንግስት ሃይሎችና ተቋማት ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በትግል ላይ እያሉ መስዋዕትነት በከፈሉት ሻለቃ መሳፍን ጥጋቡ ወይንም ገብርዬ እንዲሁም በታጋይ ጎቤ መልኬ እና በአበራ ጎባው ስም የተሰየሙት ወታደራዊ ዘመቻዎች፣ ...

Read More »