ለወራት በእስር ላይ የነበሩት መምህር አለማየሁ መኮንን ተፈቱ

መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወታደራዊ እዙ ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የቆዩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ምክትል ሊቀመንበር መምህር ዓለማዬሁ መኮንን በ3000 /ሦስት ሺህ) ብር ዋስ ተፈተዋል፡፡
አቶ አለማየሁ ከእርሳቸው ጋር የነበሩት ሌሎች 10 እስረኞች ሲለቀቁ እርሳቸው ብቻ ታስረው እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር።
በሌላ በኩል በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ወልደሃና መጋቢት 6 ቀን 2009 ዓም ከቤቱታቸው በደኅንነት ታፍነው ተወስደዋል።
አቶ ለገሰ ወ/ሃና ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መዛወራቸውን ምንጮች ገልጸዋል።