መድረክ ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ለመነጋገር ሃሳብ አቀረበ

መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተደረገ ባለው 22 ፓርቲዎች የፖለቲካ ድርድር መድረክ ላይ፣ የመድረኩ ተወካይ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ድርድሩ በኢህአዴግና በመድረክ መካከል ብቻ ሊካሄድ ይገባል ብለዋል። ኢህአዴግ ገዢ ፓርቲ በመሆኑ፣ መድረክ ደግሞ የአገሪቱ ዋነኛ ፓርቲ በመሆኑ ድርድሩ በሁለቱ መካከል ሊሆን ይገባል ሌሎች ፓርቲዎች ግን በተሳፊነት ብቻ መቅረብ አለባቸው ብለዋል።
ኢህአዴግ በበኩለ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በፓርላማ ወንበር ያላቸው በኢህአዴግ ፓርቲ ውስጥ ያልታቀፉ ነገር ግን ክልሎችን የሚያስተዳድሩ ፓርቲዎች እንዲካተቱ ሃሳብ አቅርቧል።
ሌሎቹ 20 ዎቹ ፓርቲዎች ድርድሩ በአገር አቀፍ ደረጃ በተደራጁ ፓርቲዎች መካከል መሆን አለበት የሚል አቋም ይዘዋል።