ኢሳት (መጋቢት 11 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው አደጋ በቆሻሻ ክምር የተቀበሩ ሰዎችን ሙሉ ለሙሉ ለማግኘት ወራትን ሊፈጅ እንደሚችል የነብስ አድን ሰራተኞች አስታወቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍለጋን የማካሄዱ ዘመቻው ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል ቢልም፣ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ድረስ ከ80 የሚበልጡ ሰዎች አለመገኘታቸውን ገልጸዋል። የነብስ አድን ሰራተኞች በበኩላቸው በቆሻሻ ክምሩ ያልተገኙ ሰዎችን ሙሉ ለሙሉ ፈልጎ ...
Read More »የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትላቸው ከሃገር ኮበለሉ
ኢሳት (መጋቢት 11 ፥ 2009) የበርካታ ሚሊዮን ብር ብክነት ሪፖርት የቀረበባቸው የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከሃገር መኮብለላቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ሁለቱ ባለስልጣናት ከሃገር የኮበለሉት ስራቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የ16 ሚሊዮን 863 ሺ 33 ብር ከደምብ ውጭ ህገወጥ የመድሃኒት ግዢ ፈጽመዋል በሚል በፓርላማ ሪፖርት የቀረበባቸው ዋናው ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ...
Read More »ለስኳር ፕሮጄክቶች ግንባታና ማስፋፊያ ከህንድ የተወሰደው ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር የታሰበውን ውጤት አለማምጣቱ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 11 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ከህንድ ለስኳር ፕሮጄክቶች ግንባታና ማስፋፊያ የወሰደው ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር (ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ) የታሰበውን ውጤት አለማምጣቱ ተገለጸ። ለእነዚሁ ፕሮጄክቶች በአምስት ዙሮች በድምሩ 739 ሚሊዮን ዶላር ብድር መለቀቁንና ባንካቸው ፋይናንስ ያደረጋቸው የስኳር ልማት ፕሮጄክቶች ውጤታማ መሆን እንዳልቻሉ የህንድ የኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ዲባሲህ ማሊክ ለሪፖርተር ጋዜጣ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 ተከታታይ ጥቃቶችን መፈጸሙን ተከትሎ ሰሜን ጎንደር ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት አለ
መጋቢት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት ሰሞኑን በተለያዩ ታጋዮች ስም የተሰነዘሩት ጥቃቶችን ተከትሎ በአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ በመቀጠሉ ወታደሮች ታጋዮችን ጠቁሙ በማለት ህዝቡን እያስጨነቁት ነው። ቆላ ድባ በመስተዳድሩ ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ሚሊሺያውና ወታደሮች እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ዛሬም ከተማው ተወጥሮ ማወሉን የአካባቢው ምንጮቻችን ገለጸዋል። በጭልጋ ወረዳ አቦ ከተባለው ቦታ ላይ ትናንት ከምሽቱ 12:30 ላይ ታጋዮች ...
Read More »የብአዴን ባለስልጣናት ኢሳት በሚያውጣቸው መረጃዎች ዙሪያ ክርክሮችን አካሄዱ
መጋቢት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ብአዴንን አስመልክቶ የሚያወጣቸው መረጃዎች የብአዴንን ባለስልጣናት እርስ በርስ እያወዛገባቸው ነው።በአንዳንድ አመራሮች መካከል አለመተማመኑ እየሰፋ ሂዷል። የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከክልሉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋር ያደረጉት ስብሰባ የድምጽ ቅጂ ፣ በፌደራል ደረጃ በሚጠበቅ ተቋምና ከፍተኛ የኤሌክቶሪንክስ ፍተሻ በተደረገበት ሁኔታ እንዴት በኢሳት ሊወጣ ቻለ የሚል ጥያቄ ተነስቶ ባለስልጣኖቹ የተወዛገቡ ሰሆን፣ የኮሚኒኬሽን ሃላፊው አቶ ንጉሱ ...
Read More »በዝዋይ የሚታየው ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንደቀጠለ ነው
መጋቢት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዝዋይ ሃይቅ ሼር በሚባለው የሆላንድ አበባ እርሻ በሚለቀው አደገኛ ኬሚካል የተነሳ፣ ህዝቡ ከሃይቁ ተጣርቶ የሚመጣውን ውሃ መጠቀም ካቆመ ሳምንታት ቢቆጠሩም፣ የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት መፍትሄ ሊሰጡት አልቻሉም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለስልጣናት ህዝቡ ከሃይቁ የሚመጣውን የቧንቧ ውሃ እንዳይጠቀም ቢከለክሉም፣ አማራጭ መፍትሄ ግን አላስቀመጡም። የከተማው ህዝብ ከከተማው ውጭ በመኪና እየተጫነ የሚመጣለትን ውሃ እየገዛ ለመጠቀም ተገዷል። ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መንግስት ከጋምቤላ የተወሰዱ ህጻናት ካለ ለማስመለስ እንሞክራለን አለ
መጋቢት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ የሙርሌ ጎሳ አባላት በጋምቤላ ክልል ጥቃት መፈጸማቸውን ቢያምንም፣ ተወሰዱ ስለተባሉ ህጻናትና ተገደሉ ስለተባሉ ሰዎች ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወደ ጁባ በማምራት ከመንግስት ጋር መነጋገራቸውን የገለጸው ራዲዩ ታማዙጂ፣ የቦማ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋምቤላ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ለጁባ መንግስት ቢያስታውቁም አሃዙ ላይ ማረጋገጫ አልሰጡም። የደቡብ ሱዳን መንግስት በሙርሌ ጎሳ አባላት በኩል ...
Read More »የኢትዮጵያ የግብርና ዕድገት ወደ 2.5 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሲመዘገብ የቆየው ሰባት በመቶ የግብርና እድገት በሃገሪቱ ተከስቶ ባለው የድርቅ ምክንያት ወደ 2.5 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ አራት ክልሎች አዲስ ተከስቶ ባለው ድርቅ ዙሪያ ሃሙስ ለፓርላማ ሪፖርትን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ድርቁ በግብርና እድገቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አብራርተዋል። በአፋር ኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ከወራት በፊት በአዲስ መልክ ...
Read More »ኢትዮጵያ ለተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ፈቃድ እንድትሰጥ ጥያቄ ቀረበ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ተደርጎ በሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ተደርጓል ያለውን ማሻሻያ ተከትሎ ሃገሪቱ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ፈቃድ እንድትሰጥ ተጠየቀ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የአዋጁ መውጣትን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ተፈጽሟል ባለው ግድያና የጅምላ እስራት ላይ ምርመራ ለማካሄድ ጥያቄን አቅርቦ እንደነበር አውስቷል። ለአዋጁ ...
Read More »የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የአገሪቱ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳሰበ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ጉብኘትን እያደረጉ ያሉት የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በሃገሪቱ ቆይታቸው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የብሪታኒያ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳሰበ። ሪፕሪቭ የተሰኘውና የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅቱ, ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባለፈው አመት ስልጣን በተረከቡ ጊዜ ለሃገሪቱ ዜጎች መብት መከበር የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ የቦሪስ ጆንሰንን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው ...
Read More »