ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ አለም አቀፍ ሃገራትና አበዳሪ አካላት የሚያገኘው የብድርና የእርዳታ ፍሰት እየቀነሰ መምጣቱ ጉዳዩን የሚከታተለው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ረቡዕ አስታወቀ። በተለይ ያደጉ አገሮች በራሳቸው ችግር ምክንያት ሲያደርጉ የቆዩትን የፋይናንስ ድጋፍ እያቋረጡ መሆኑን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አዳም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል። የብድርና የእርዳታ ፍሰቱ መቀነስ ከአጠቃላይ ወጪ አንጻር ተጽዕኖ ይኖረዋል ያሉት ሃላፊው ...
Read More »ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪን ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። በቅርቡ መንግስትና ድርጅቱ ባወጡት የተረጂዎች ቁጥር መረጃ 5.6 ሚሊዮን አካባቢ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተረጂዎች በ2.2 ሚሊዮን በማደግ 7.8 ሚሊዮን መድረሱ ይፋ ተደርጓል። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪ እየሰጠ ያለው ምላሽ አነስተኛ መሆንና በድርቁ በተጎዱ አካባቢዎች በበልግ ወቅት ...
Read More »የማላዊ መንግስትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማላዊ አየር መንገድን በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት ተቃውሞ ቀረበበት
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ መንግስት ጋር የማላዊን አየር መንገድ በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት በማላዊ የፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞ ቀረበበት። በሃገሪቱ ፓርላማ ተሰሚ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የፓርላማ አባሏ ጁሊያን ሉንጉዚ የሃገራቸው መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያደረገው ስምምነት ማላዊን የሚጠቅም አይደለም በማለት ውሉ መጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ...
Read More »አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ድንገተኛ ህምም ማክሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ላለፉት 23 አመታት በዚህ በአሜሪካ በስደት ይኖሩ የነበሩት አቶ ፈቃደ የኢህአዴግን ስልጣን መያዝ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተባረሩ 42 መምህራን አንዱ እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። በዚህ በአሜሪካ በነበሩበት ረጅም ጊዚያቶች አቶ ፈቀደ ...
Read More »የአዲስ አበባ ሕዝብ በገዥው ፓርቲ የበቀል እርምጃ እየተማረረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት የአርሶ አደሮችን መሬት ነጠቃ ከተቋረጠ ወዲህ ገዥው ሕወሃት/ኢህአዴግ ፊቱን ወደ ዋና ከተማዋ መልሷል የሚሉት ነዋሪዎች፤ በልማት ስም ነባር ይዞታያላቸውን የከተማ ነዋሪዎች መሬት መንጠቅ ተጧጡፎ መቀጠሉን ይገልጻሉ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ካለፍላጎታቸው ከይዞታቸው እንዲነሱ የተደረጉት ነዋሪዎች መኖሪያውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ በመስተዳድሩ ቃል የተገቡላቸው በሙሉ ተፈጻሚ አይሆኑም። ...
Read More »ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጥምረት መስራት አትራፊ እንዳልሆነ አንድ የማላዊ የፓርላማአባል ገለጹ::
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲና የአገሪቱ ፓርላማ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁሊያን ሉንዛጊ ዛሬ ለአገራቸው ፓርላማ እንዳሳወቁት የማላዊ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በጥምረት መስራቱ አትራፊአያደርገውም ብለዋል። ጁሊያን ሉንዛጊ አያይዘውም የአገራቸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት-አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሥራቱ እንዴት ትርፋማ ሊሆን እንደሚችል ሪፖርትእንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የፓርላማ አባሏ “ትርፋማ ካልሆንን ለምን አብረን ...
Read More »በዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ላይ የሚደረገው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ አሚን ጁዲ ጥሪ አቀረቡ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አክቲቪስት አሚን ጁዲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኅብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአፍሪካ ህብረት ዶክተር ቴዎድሮስን ደገፈው፤ አልደገፈው ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም ጤና ድርጅት ስም ስልጣን እንዲይዝ የሚፈልጉት፤ ከጀርባ እሱን ተጠቅመው በአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ...
Read More »አቡነ ዘካርያስ የተጭበረበሩትን 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ራሳቸው ከፈሉ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቀደም ሲል የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት አስተዳደር የነበሩትና አሁን የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ዘካርያስ፣ በሐሰተኛ ሰነድ ተጭበርብረው ሕንፃበመግዛታቸው የከሰረውን ገንዘብ ከምዕመናን በማሰባሰብ ራሳቸው ፈጸሙ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ዘካርያስ ቀደም ሲል ያስተዳድሩት በነበረ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ደቀ መዛሙርት ማሠልጠኛና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ...
Read More »ሟቹ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን አስጨፋሪ ከጨጓራ ህመም ውጪ ምንም ዐይነት ህመም እንደሌለበት ወላጅ አባቱ ገለጹ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘነበ አባት አቶ በላይ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ልጃቸው ከጨጓራ ህመም ውጪ የልብ ድካምም ሆነ ድንገት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ እንዳልነበረበት ጠቅሰው፤ እስካሁን ድረስ ምን ሆኖ እንደሞተ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በሀዘን ስሜት ተውጠው ተናግረዋል። ቡና ከሃዋሳ ከነማ ጋር ላለው ግጥሚያ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ወደ ሃዋሳ ሲያመራ አብሮ እንደተጓዘ ...
Read More »አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ አቋረጠች
ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ለሙስና የተጋለጠ ነው በማለት ድጋፏን አቋረጠች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴት ለኬንያ መንግስት ባሳወቀው በዚሁ ውሳኔ 12 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ድጋፍ እንዲቋረጥ መደረጉን እንደገለጸ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። በኬንያ የአሜሪካ አምባሳደር ሮበርት ጎዴክ በሃገሪቱ ሙስናና ተጠያቂነት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቀጥታ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ...
Read More »