በዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ላይ የሚደረገው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ አሚን ጁዲ ጥሪ አቀረቡ።

ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አክቲቪስት አሚን ጁዲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኅብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአፍሪካ ህብረት ዶክተር ቴዎድሮስን ደገፈው፤ አልደገፈው ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም ጤና ድርጅት ስም ስልጣን እንዲይዝ የሚፈልጉት፤ ከጀርባ እሱን ተጠቅመው በአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ማድረግ የሚፈልጉ የመድሃኒትኩባንያዎችና አገሮች ናቸው ሲሉ አቶ አሚን ተናግረዋል።
“እሱን የመሰለ በሕዝብ እልቂት የሚቀልድ ዓሣ ነባሪ ለዚህ ቦታ መታጨት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ውርደት ነው። “ ያሉት የቀድሞው የኦነግ አመራር፤ ሰውዬውን የአፍሪካ ህብረትደገፈው አልደገፈው ሕብረቱ የአምባገነኖች ስብስብ መሆኑን ስለምናውቅ ተቃውሟችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል”ብለዋል።
ነገሩ ከብቃትና ከሙያ አንጻር ብቻ የሚታይ አይደለም ያሉት አቶ አሚን፤“የህወኃቱን ቁንጮ ዶከተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን እዚያ ቦታ ማስቀመጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጸመው ኢሰብ ዓዊነትና ጭቆና ማረጋገጫ እስደመስጠት ነው “ብለዋል።
ዶክተሩ ለዓለም የጤና ዳይሬክተርነት የሚያደርጉትን ውድድር ለመቃወም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የፊታችን ግንቦት 22 ቀን በስዊዘርላንድ ጄኔሻ የመንግስታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰልፍ መጠራቱ ይታወቃል።