(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 17/2010)በአፍሪካ አህጉር አክራሪነት እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነው የየሀገራቱ መንግስታት ጭቆና መሆኑን አንድ ጥናት ይፋ አደረገ። ባለፉት 6 ወራት ብቻ አክራሪ ሃይሎቹ በአፍሪካ ምድር በወሰዱት ርምጃ 33 ሺህ ሰዎች ሲያልቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ደግሞ መፈናቀላቸው ተመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት የጥናት ቡድን በአክራሪ ሃይሎቹ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 500 ያህል ጽንፈኛ ግለሰቦችን ጭምር በማነጋገር ባደረገው ጥናት የመንግስታት የጭቆናና አፈና ድርጊት ግለሰቦች አክራሪ ቡድኖችን እንዲቀላቀሉ ...
Read More »የአሰሪና ሰራተኛ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሰራተኞችን መብት ያፍናል ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 17/2010)የአሰሪና ሰራተኛ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሰራተኞችን መብት እንደሚያፍን ተገለጸ። አዋጁ የመንግስት ሰራተኞችን የመደራጀት መብት የሚከለክልም ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በጽህፈት ቤቱ ጥቅምት 13 2010 በረቂቅ አዋጁ ላይ የሰጠውን የተቃውሞ መግለጫና የቀጣይ ርምጃዎች ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ሰራተኞች እስከ ስራ ማቆም አድማ የሚሄድ ዝግጁነት እያደረጉ መሆኑን የተለያዩ ፋብሪካዎች የሰራተኛ ማህበራት አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉና የሰራተኛ ማህበራቱ ኮንፌዴሬሽን ...
Read More »አንድ ፈረንሳዊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ዘመቻ ከፈተ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 17/2010)ፈረንሳዊው ፍራንሷ ጂራርድ ዘመቻ ማካሄጃ መረብ በመክፈት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የያዙትን ሃልፊነት እንዲለቁ በአለም አቀፍ ደረጃ ዘመቻ ጀመረ። ዘመቻውን በተለያዩ አለም የሚገኙ ነዋሪዎችና ኢትዮጵያውያን እየደገፉት መሆኑም ታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ዘመቻ የተከፈተባቸው የዚምባቡዌውን ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለአለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን ተከትሎ ነው። በቅርቡ የዚምባቡዌውን ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለአለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ...
Read More »በጊንጪ ዛሬ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃት ተፈጸመ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 17/2010)በጊንጪ ዛሬ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃት ተፈጸመ። በጥቃቱ ሁለቱ መገደላቸው ታውቋል። የአምቦው ግድያ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች አዲስ ተቃውሞ ቀስቅሷል። በአምቦ ትላንት የተገደሉ ሰዎች የቀብር ስነስርዓትም ተፈጽሟል። በኢሉባቡር ጎሮ የህወሀት አባል በሆኑ ሁለት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት የጦር መሳሪያዎች መገኙቱንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ የውጭ ድጋፍ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህወሀት መንግስት በመጨረሻው ሰዓቱ ...
Read More »በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010) በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ። በርካታ ቁጥር ባለው የጸጥታ ሃይል ታጅቦ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው እጩ ደጋፊዎች በሚገኙበት የምርጫ አካባቢዎች ግጭት ተከስቶ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ታውቋል። በርካታ ሰዎችም ተጎድተዋል። እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ምርጫው በሰላም የተካሄደ ቢሆንም የተቃዋሚ እጩው ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በሚበዙባቸው አራት የምርጫ አውራጃዎች ግን ግጭት ተከስቷል። ራይላ ኦዲንጋ ከዛሬው ...
Read More »ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቁ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010)የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዚምባቡዌውን ሮበርት ሙጋቤን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርገው የሾሙበት ድርጊት እንዲመረመርና ጉዳዩ ሙስና ሆኖ ከተገኘ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቁ። ቻይና ስፍራውን እንዲያገኙ ለተጫወተችው ሚና የተሰጠ ምላሽ ይሆን ወይ የሚሉ መላምቶች መንጸባረቃቸውንም በዋሽንግተን ፖስት ላይ ጥቅምት 25/2017 የቀረበው ጽሁፍ አመልክቷል። ለ18 አመታት የሲ ኤን ኤን ዘጋቢና ተንታኝ የነበረችውና በአሁኑ ወቅትም በዋሽንግተን ፖስት፣በቺካጎ ትሪቡንና መሰል ...
Read More »የአቶ በረከት ስምኦንና አባዱላ ገመዳ ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ በሕዝቡ ዘንድ ግርታን ፈጥሯል ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010) የአቶ በረከት ስምኦንና አባዱላ ገመዳ ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ያልተለመደ በመሆኑ በሕዝቡ ዘንድ ግርታን ፈጥሯል ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም በፓርላማ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ እንዳሉት አቶ በረከት ከመንግስት ስልጣን ቢለቁም ትግል ትተዋል ማለት ባለመሆኑ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል ብለዋል። የአቶ አባዱላ ከመንግስት ስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ግን ገና ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ነው የገለጹት። አቶ ሃይለማርያም በሀገሪቱ ወቅታዊ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን መንግስት በሚዲያ ስራ እየተመራ ነው አለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መንግስታቸው በሚዲያ ስራ እየተመራ መሆኑን ገለጹ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃና ዜና የሚሰማው ከአዲስ አበባ ሳይሆን ከዋሽንግተን ዲሲ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርአይ አስገዶም የመንግስት ቃል አቀባዩን ዶክተር ነገሬ ሌንጮን በተቹበት በዚህ መግለጫ የውጭ መገናኛ ብዙሃንን ተጠቅመው ስርአቱን የማብጠልጠልና ግጭቶችን የማባባስ ስራ ከሚዲያዎቹ በስተጀርባ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል። ትልቁ ችግር ከሚዲያው በስተጀርባ ...
Read More »በኢሉባቡር መቱ ከተማ ከአንድ የህወሀት አባል መኖሪያ ቤት በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተገኙ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010) በኢሉባቡር መቱ ከተማ ከአንድ የህወሀት አባል መኖሪያ ቤት በርካታ የጦር መሳሪያዎችና የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች ተገኙ። በከተማዋ ለረጅም ጊዜ ነዋሪ በሆኑትና በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አባልነታቸው የሚታወቁት ግለሰብ በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ፍተሻ ዘጠኝ ቦምቦችን ጨምሮ ክላሽ መሳሪያዎች፣ የጦር ሜዳ መነጽር፣ ለቅስቀሳ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችና የተለያዩ ዶክመንቶች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል በኢሉባቡር በደሌና ጮራ በህወሀት መንግስት አቀናባሪነት የተፈጸመው ...
Read More »በአምቦ በተነሳው ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010) በአምቦ በተነሳው ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ። የአምቦ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት እንደተናገሩት ግን በአጋዚ ኃይል የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 10 ነው። ስኳር የጫኑ ተሳቢ ተሽከርካሪዎችን በማገት ወዳስቀረው የአምቦ ከተማ ህዝብ ዛሬ ጠዋት የመከላከያ ሰራዊቱንና የፌደራል ፖሊስ ሃይል ያሰማራው መንግስት በትንሹ 20 ሰዎችን ማቁሰሉንም መረጃዎች ያመለክታሉ። አምቦ ከቀትር በኋላ ሙሉ በሙሉ በሰራዊት ...
Read More »