ሕወሃት በስብሰባ ተጠምዷል ተባለ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በስብሰባ መወጠሩ ተሰማ። ሕወሃት በአቶ አባይ ወልዱና ወይዘሮ አዜብ መስፍን ምትክ አቶ ጌታቸው ረዳንና ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን እንዲሳተፉ ማድረጉ ታውቋል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የውጭ ሀገር ጉዟቸው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰርዟል።                                   በማያቋርጥ ስብሰባ የተጠመደው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሀገራዊ፣ወቅታዊና ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመወሰን በጠቅላይ ...

Read More »

የገደንቢ ወርቅ ማምረቻ የሚያደርሰው ማህበራዊ ቀውስ መባባሱ ተገለጸ

  (ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያመጣው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ቢቢሲ ገለጸ። ኩባንያው ወርቁን ለማጽዳት የሚጠቀምበት “ሳናይድ”የተባለው ኬሚካል የልብ፣የአእምሮና የነርቭ ህመሞችን እንደሚያስከትል ሙያተኞቹ ገልጸዋል። ሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያመጣው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። የሚዲያ ተቋሙ በአካባቢው በአካል በመገኘት የሻኪሶ ነዋሪዎች፣የጤና ባለሙያዎች፣የወረዳው ...

Read More »

በኢየሩሳሌም ጉዳይ በተነሳው ብጥብጥ አንድ ሰው ተገደለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ስለመሆኗ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ አንድ ሰው ሲገደል 200 ያህል ቆሰሉ። በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክ እንዲሁም በእስራኤልና ጋዛ ድንበር ላይ ከፍተኛ ግጭት ተከስቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ነች አሜሪካም ኤምባሲዋን ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ታዞራለች ማለታቸው ግጭት እንደገና እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል። በፍልስጤም በመሀሙድ አባስ የሚመራው የፋታህ ፓርቲ ...

Read More »

ሕሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) በኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሕሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ባለማግኘታቸው ችግር ላይ እየወደቁ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ። መድሃኒት አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻላቸው በተለይ የልብና የስኳር ህሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ለማግኘት ተቸግረዋል። ቢቢሲ በአዲስ አበባ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ህሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ማግኘት ባለመቻላቸው ችግር ላይ እየወደቁ መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም የስኳርና የልብ ህሙማን እለት እለት መድሃኒት የሚፈልጉ ቢሆንም በየመድሃኒት ቤቶቹ ዞረው ማግኘት አልቻሉም። ...

Read More »

በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥ አንዱን ብሔር ማግለልና ሌላውን ማወደስ ይታያል ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥ አንዱን ብሔር ማግለልና ሌላውን ማወደስ እንደሚታይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የቀድሞ ተማሪዎች የሚሰባሰቡት በፖለቲካና በርዕዮተ አለም አመለከታተቸው ነበር ብለዋል። በአፋር ክልል የሕወሃት አገዛዝ ኣያከበረ ያለውን “የብሔረሰቦች ቀን” በማስመልከት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ እየተየ ያለውን ተቃውሞና አመጽ በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አቶ ሃይለማርያም በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ ብሄር ተኮር ...

Read More »

የህወሃት አገዛዝ ሕዝቡን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እያመራው ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) የህወሃት አገዛዝ ትዕግስተኛውንና በፈሪሃ እግዚአብሔር በተመሠረተ ጨዋነት ላይ የሚኖረውን ሕዝባችንን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እንዲያመራ እየገፋፋው ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ። “ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም ”በሚል ርዕስ መግለጫ ያወጣው ቅዱስ ሲኖዶስ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ፖለቲካ አገርን ለመምራት መሞክር በዘመኑ ያለመኖርን ያህል ይቆጠራል በዓለም መድረክ ፊትም ...

Read More »

አርዱፍ የህወሃትን ሰራዊት መቶ መለሰ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት የአርዱፍን ይዞታ ሰብሮ ለመግባት ያደረገው ሙከራ መክሸፉንና ተመቶ መመለሱን የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ አስታወቀ። መብታችን እስኪከበር በሕወሃትና በመልዕክተኛው የአፋር ልዩ ፖሊስ ሃይል ላይ የጀመርነው ውጊያ ይቀጥላል ሲልም አስታውቋል። የውጭ ሀገር ዜጎችና ጎብኚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አርዱፍ አስጠንቅቋል። የብሔር ብሄረሰቦች በአል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በሚል በአርዱፍ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ከአርዱፍ ተዋጊዎች ...

Read More »

የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሊያደረግ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የሕወሃት አገዛዝ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሊያደርግ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ውድድሩ እንዲቆም የተፈለገው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይና በአማራ ክልል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለም በወሎ ወልዲያ ግጭት በተካሄደ ማግስት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የነቀምት ከነማ ክለብ ተጫዋቾችና ደጋፊዎችን በደመቀ ስነስርአት ተቀብለዋቸዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በክለቦች መካከል ባሉ ...

Read More »

ሃማስ የአመጽ ጥሪ አስተላለፈ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ነች ሲሉ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ሃማስ የአመጽ ጥሪ ማስተላላፉ ተሰማ። የትራምፕን ውሳኔ ተከትሎም በኢየሩሳሌም፣በራማላህና በቤተልሄም ተቃውሞ ተቀስቅሷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢየሩሳሌም እውቅና መስጠታቸውና በቴላቪቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም ለማዛወር መወሰናቸው ከሀገራት መሪዎችና ከእስልምናው አለም ውግዘትን አስከትሏል። እስራኤላውያንም ሆኑ ፍልስጤማውያን ኢየሩሳሌም በመዲናነት ትገባናለች ብለው ያምናሉ::ይህም ለዘመናት አጨቃጫቂ ጉዳይ ሆኖ ...

Read More »

አባ ገብረኢየሱስ በእስር ቤት ሲደበደቡ አደሩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የዋልድባው መነኩሴ አባ ገብረኢየሱስ ዛሬ ለሊቱን በእስር ቤት ሲደበደቡ አድረው ወደ ጭለማ ቤት መወርወራቸው ተሰማ። በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለምንም ብይን በጭለማ ቤት ታስሮ የሚገኘው አስቻለው ደሴ አባ ገብረየሱስ ስብርብር እንዲሉ ተደርገው ከተደበደቡ በኋላ በሱ ጭለማ ክፍል መጣላቸውን መስክሯል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑን ...

Read More »