የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ አወጣ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሳምንት በፊት የጀመረው ስብሰባ አለመጠናቀቁን በማስመልከት ግንባሩ መግለጫ አወጣ። በአባል ድርጅቶች ውስጥ አለመተማመንና መጠራጠር እንደነበርም መግለጫው ዘርዝሯል። አዘቅት ውስጥም ገብተናል ሲልም ያክላል። በአጠቃላይ ጉዳይ የተጀመረውና የቀድሞ አመራሮችን ያሳተፈው ግምገማ አሁንም መቀጠሉን በፓርቲና በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተለቀቀው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ያስረዳል። “እስካሁን በተደረገው ጥልቅ ግምገማ ከስኬት ጎዳና እያራቁን የሚገኙት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል አለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ሁኔታ ስጋት ውስጥ እንደከተተው አስታወቀ። ትላንት በህብረቱ ቃል አቀባይ የተላለፈው መልዕክት ላይ እንደተገለጸው የአውሮፓ ሀገራት ህብረት በኢትዮጵያ ያለው ብሄርን መሰረት ያደረገው አለመረጋጋት አሳሳቢ ሆኖበታል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎችና በዩኒቨርስቲዎች የሚታየው የሰላም መደፍረስ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ህብረቱ ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች መሀል የተፈጠረው ግጭት የማያባራ ሆኖ መቀጠል በከፍተኛ ሁኔታ አሳስቦኛል ብሏል የአውሮፓ ...

Read More »

በኦሮሚያ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው  

(ኢሳት ዲሲ–ታሕሳስ 12/2010) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ታወቀ። በሀረርጌ የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በመቱ ለአራተኛ ቀን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጂማና በቄሌም ወለጋም ተመሳሳይ የተቃውሞ ትዕይንት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። በወለጋ በአንዳንድ ቦታዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላትና ደጋፊዎች የትምህርት አገልግሎትን ጨምሮ ብድርና እርዳታ እንደተከለከሉ ተገልጿል። ህዝባዊ ተቃውሞና ግድያ ተለይቶት በማያውቀው ሀረርጌ ዛሬም ጠንከር ያለ ...

Read More »

የኦሕዴድና ብአዴን የፓርላማ አባላት ስብሰባ አንሳተፍም አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010)  በኢትዮጵያ ፓርላማ የኦሕዴድና ብአዴን አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ካልሰጧቸው በመደበኛ ስብሰባዎች አንሳተፍም አሉ። የኦሕዴድና የብአዴን የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ሀገሪቱን ስጋት ላይ በጣላት ብሄር ተኮር ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ላይ አቶ ሃይለማርያም ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ አቅርበዋል። አባላቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በተወከሉባቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት ካካሄዱ በኋላ ነው። በኢትዮጵያ ያለው ...

Read More »

በኢራቅ እስከ 11 ሺ የሚደርሱ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በኢራቅ በአይሲስ ተይዛ የነበረችውን ሞሱል ለማስለቀቅ በተደረገ ፍልሚያ እስከ 11 ሺ የሚደርሱ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ይህ አሃዝ ከዚህ በፊት ሲነገር ከነበረው በ10 እጥፍ እንደሚልቅም ታውቋል። በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር በኢራቅ ወታደራዊ ሃይል በአይሲስ ተይዛ የነበረችውን ሞሱልን ለማስለቀቅ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ጥቃት ከ9ሺ እስከ 11ሺ ንጹሃን ሰዎች ማለቃቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ...

Read More »

ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የኛ አጋር አይሆንም አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የአሜሪካ አጋር መሆን አይገባውም ሲሉ ተናገሩ። ኮፍማን ይህንን ያሉት በአሜሪካ የኮሎራዶ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ዴንቨር ባለፈው ቅዳሜ ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውን ረቂቅ ህግ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ነበር። ኢትዮጵያና አሜሪካ በጋራ የሚያደርጉት የጸረ ሽብር እንቅስቃሴ አደጋ ላይ ይወድቃል በሚል ማስፈራሪያ ህጉ እንዲጨናገፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ...

Read More »

የሱዳን ጦር የሀገራችንን ድንበር መጣሱ አለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታሕሳስ 11/2010) የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የሱዳን ጦር የሀገራችንን ድንበር በመጣስ በቅርቡ የፈጸመው ወረራ አለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ሲል ለፕሬዝዳንት አልበሽር በጻፈው ደብዳቤ አሳሰበ። የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣም ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ይህን መሰል ደብዳቤ ሲጽፍ የመጀመሪያው አይደለም። የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተላልፎ ተሰቷል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ጉዳዩ ያሳሰበው ...

Read More »

የትግራይ ተወላጆች ማህበር የሀዘን መግለጫ አወጣ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/ 2010) ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በርካታ ዜጎች ሲገደሉ ድምጹን ያላሰማውና በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ማህበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተገደሉ ዜጎች የሀዘን መግለጫ ማውጣቱ ተሰማ። በርካታ ኢትዮጵያውያን በመከላከያ ሰራዊት፣ በፊደራል ፖሊስና በልዩ ሃይል ፓሊስ ሲገደሉ ድምጹን ያላሰማው ማህበር አሁን ላይ አለሁ ማለቱ በብዙዎች ዘንድ እንዲተች አድርጎታል። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ማህበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ...

Read More »

ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በሐገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ሁለት ፓርቲዎችና በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚዎች ስብሰባ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገለጹ። ሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም መኢአድና ሸንጎ በዋሽንግተን ዲሲ በሳምንቱ መጨረሻ ባካሄዱት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ሁለቱ የሀገር ቤት ድርጅቶችና ሸንጎ በሚል አጭር መጠሪያ የሚታወቀው በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ስብሰባ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በአደረጃጀት፣በፋይናንስ፣በአቅም ግንባታ፣አለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ...

Read More »

ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ዛሬ ተቃውሞ መካሄዱ ተገለጸ። በዱከም የቻይና የኢንዱስትሪ ዞን መመስረትን በመቃወም ሰልፍ ተካሄዷል። መቱ ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ተደርጎባታል። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ግጭት መፈጠሩም ታውቋል። በድሬዳው ዩኒቨርስቲ ዛሬ ግጭት መፈጠሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ባለፈው ሰኞ በርካታ ተማሪዎች የተጎዱበት ግጭት ከተከሰተ በኋላ ዩኒቨርስቲው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም ዛሬም በተማሪዎች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በኢሉባቡር መቱ ለ3ኛ ቀን ...

Read More »