የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመድበው ገንዘብ ተቸገረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) በኢትዮጵያ ያለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ተባብሶ በመቀጠሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤምባሲዎችና ለቆንስላ ጽህፈት ቤቶች የሚመድበው ገንዘብ መቸገሩ ታወቀ። ኤምባሲዎቹ እየገጠማቸው ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ በየሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በኢንቨስትመንት ማበረታቻና በቤት መስሪያ ቦታ እያግባቡ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ቤት እንዲልኩ ታዘዋል። ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት የውጭ ምንዛሪ እየታየ ለኤምባሲዎቹ የበጀት ጉድለቱ እንደሚሸፈንላቸውም ተመልክቷል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ...

Read More »

በመቄት ከተማ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) በሰሜን ወሎ መቄት ከተማ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ከወልዲያ ወደ ደቡብ ጎንደር የሚወስደው መንገድም ተዘግቷል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ መነሳቱም ታውቋል። በሰሜን ወሎ በተለያዩ አካባቢዎች ውጥረት መቀጠሉ ታውቋል። መቄት ከወልዲያ ወደ ደቡብ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ ከሚገኙ ከተሞች አንዷ ናት። በተለያዩ ጊዜያት በተነሱ ተቃውሞዎች መቄት ስሟ ሳይጠቀስ አያልፍም። ሰሞኑንም ሰሜን ወሎን ካዳረሰው ተቃውሞ ጋር ተነስታለች። የመቄት ነዋሪዎች የወልዲያውን ጭፍጨፋ ፣ ...

Read More »

የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ተበተነ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ተበተነ። የክለቡ ተጫዋቾች የተበተኑት በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል። የወልዲያ ክለብ ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ከተማዋን ለቀው ሄደዋል ተብሏል። በሰሜን ወሎ የተለያዩ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ ነው የቀጠለው። የአካባቢውን ከተሞች በፍጥነት ያዳረሰው ተቃውሞ የሕይወትና የንብረት ጉዳት አስከትሏል። ሕወሃት ከመሃል ሀገር ወደ ትግራይ ሸቀጦችንና ወታደራዊ ቁሶችን የሚያሻግርበት መንገድም አገዛዙን በሚቃወሙ የሰሜን ...

Read More »

የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ያህል መድረሱ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ያህል መድረሱን አለም አቀፍ ሪፖርቶች አመለከቱ። ስደተኞቹ በ4 መቶ ጣቢያዎች መስፈራቸውን ሪፖርቱን ያቀረቡት ተቋማት ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ በቂ እርዳታ እየተደረገላቸው አለመሆኑንም በሪፖርቱ ተመልክቷል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተበራከተው ግጭት ምክንያት ተዘንግተዋል። በቀደሙ ሪፖርቶች 7 መቶ ሺ ሕዝብ መፈናቀሉ ሲነገር ነው የቆየው። ...

Read More »

በወልዲያ ተቃውሞ ዳግም ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) የወልዲያው ተቃውሞ ዳግም ተቀሰቀሰ። መሀል ወልዲያ ዛሬ ጠዋት ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ሲደረግና የመንግስት ተቋማት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ከቀትር በኋላ በቤት ውስጥ የመቀመጥ የስራ ማቆም አድማ የተመታ ሲሆን ወልዲያ ሁሉ ነገር ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆኖ እንደዋለም ታዉቋል። ህዝባዊ አመጹ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪ መገደላቸውም ታውቋል። በሲሪንቃ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። መንገዶች ተዘግተዋል። የትራንስፖርት አገልግሎት ...

Read More »

የአቶ ካሳ ተክለብርሃን የቴሌ ኮንፈረስ ውይይት በሕዝብ ተቃውሞ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በሕወሃት አገዛዝ በቅርቡ በአሜሪካ የኢሕአዴግ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ ካሳ ተክለብርሃን በቴሌ ኮንፈረስ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት በሕዝብ ተቃውሞ ተቋረጠ። በአሜሪካ ከ11 ከተሞች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ተመርጠው ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር በስልክ ኮንፈረንስ ለመወያየት ታቅዶ ራሳቸውን ካስተዋወቁ በኋላ በጥያቄና መልስ ጊዜው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። አቶ ካሳ ስለህዳሴና ልማት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለውጠናል ሲሉ የስልክ ውይይት ተሳታፊዎቹ ግን መጀመሪያ ሕዝብን መግደል ...

Read More »

በአዲስ አበባ መንደሮች ሊፈርሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በአዲስ አበባ አምስት ነባር መንደሮች ሊፈርሱ ነው። ነባሮቹን መንደሮች ለማፍረስ ደግሞ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲህ አይነቱ ስትራቴጂ የሕወሃት አገዛዝ አብሮ የኖረውን ሕዝብ በመበታተን ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለማስፈር በየጊዜው የሚነድፈው እኩይ እቅድ ነው ሲሉ እቅዱን አውግዘዋል። ሕብረተሰቡም እንዲህ አይነቱን እኩይ ተግባር በጋራ በመሆን ማስቆም ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በቅርቡ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ...

Read More »

ዶክተር መረራ ጉዲና ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010)   በቅርቡ ከወህኒ የወጡት ዶክተር መረራ ጉዲና በአምቦና በጊንጪ ከተሞች ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው። በተለይ በአምቦ ስታዲየም በተካሄደው የአቀባበል ስለስርአት በመቶ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ እንደታደመም ለማወቅ ተችሏል። ወደ አምቦ ባደረጉት ጉዞ በሌሎች የምዕራብ ሸዋ ከተሞች በተለይም በጊንጪ ከፍተኛ አቀባበል የጠበቃቸውና በአምቦ ስታዲየም የጀግና አቀባበል የተደረገላቸው ዶክተር መረራ ጉዲና ለሕዝቡ በተለይም ለወጣቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ትግሉ እንደሚቀጥል ቃል የገቡት ዶክተር ...

Read More »

በአንድ ሆስፒታል በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ 37 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በደቡብ ኮሪያ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ የ37 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ቆሰሉ። ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ የሆስፒታሉ ባለቤትና ስራ አስኪያጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከሕሙማኑ በተጨማሪ የሕክምና ባለሙያዎችም በአደጋው ሕይወታቸው አልፏል። ከደቡብ ኮሪያ ርዕሰ መዲና ሴኡል በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሚሪያንግ ከተማ በሚገኘው ሲአንግ ሆስፒታል ትላንት ምሽት የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ ባይታወቅም ...

Read More »

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ለእስረኛ የተመደበውን ብር መከፋፈላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) ከማረሚያ ቤት ለሚለቀቁ ታሳሪዎች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎች የተመደበውን 78 ሺ ያህል ብር የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሀላፊዎች እንደተከፋፈሉት ከማረሚያ ቤት የተገኘው መረጃ አመለከተ። በፌደራል ደረጃ ይፈታሉ ተብሎ ስማቸው ከተዘረዘረው 115 እስረኞች ውስጥ አሁንም ማረሚያ ቤት የሚገኙት ታሳሪዎች ቁጥር ስድስት መድረሱ ታውቋል። ከሳምንታት በፊት ክሳቸው ተቋርጦ ይለቀቃሉ ከተባሉት የፌደራል እስረኞች መካከል 115 ያህሉ ተለቀዋል ቢባልም የተወሰኑት እስካሁን በእስር ላይ ...

Read More »