የብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የስልጣን መልቀቂያ ተቀባይነት አገኘ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010) የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜይቴክ/ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሕዝብና የሃገር ሃብት አባክነው ሳይጠየቁ የስልጣን መልቀቂያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ተነገረ። ሜይቴክ የተለያዩ ግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶችን በጊዜ ባለመፈጸምና ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት በመፈጸም ኢትዮጵያ በቢሊዬኖች የሚቆጠር ብር እንድታጣ ማድረጉን የመንግስት ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ብርጋዴር ጄኔራሉ ከሜቴክ የስራ ሃላፊነታቸው ቢለቁም በመከላከያ የስልጣን ድርሻቸው በሌላ ስራ እንደሚቀጥሉ ምንጮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ...

Read More »

በጉጂ ተወላጆች እና ጌዲዮ ብሔረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010) ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ በጉጂ ተወላጆች እና ጌዲዮ ብሔረሰቦች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ ትናንት ምሽት ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ። ግድያው  እየተካሄደ ያለው  ቡሌ ሆራ ወይንም ሃገረ ማርያም  በተሰኘችው ከተማ ሲሆን በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች  አስክሬን ዛሬ በሆስፒታል እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በዚህም በግጭቱ እስካሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ ደርሷል። ግጭቱ በመስፋት አጎራባች የሆኑ ብሄረሰቦችም እየተቀላቀሉ መሆኑ ...

Read More »

በጉጅና በጌዲዮ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ትናንት ምሽት ብቻ በቡሌ ሆራ ከተማ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

በጉጅና በጌዲዮ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ትናንት ምሽት ብቻ በቡሌ ሆራ ከተማ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) የተለያዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ሰሞኑን በሁለቱ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ትናንት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች በጩቤ ተገድለዋል። በአካባቢው ብቻ እስካሁን የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ20 ይበልጣል። ከ15 በላይ መኪኖች ስደተኞችን ይዘው በከተማው አስተዳደር ተጠልለው የቆዩ ቢሆንም፣ ...

Read More »

በኮሬ እና በጉጂ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው

በኮሬ እና በጉጂ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከሃምሌ 2009 ዓም ጀምሮ በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት አንዴ ከፍ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ እንዳዲስ በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው። ሰሞኑን በተነሳው ግጭት ከሁለቱም ወገን 5 ሰዎች ሲገደሉ 11 ሰዎች ...

Read More »

መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ

መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳቡን በድፍረት በመግለጽ የሚታወቀው መምህር ስዩም ተሾመ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፎ አገዛዙን ተቃውሟል በሚል ለወር ያክል ጊዜ ከታሰረ በሁዋላ ዛሬ ከእስር ቤት ተለቋል። በተመሳሳይ መንገድ የታሰረው የኦሮምያ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደዓም እንዲሁ ከእስር ተለቋል። ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ ...

Read More »

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ካለ ሕግ ማሰርን፣ በግዳጅ ማፈናቀልና ሰቆቃን ማስቆም አልቻሉም ሲል ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ኢስት አፍሪካ አስታወቀ

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ካለ ሕግ ማሰርን፣ በግዳጅ ማፈናቀልና ሰቆቃን ማስቆም አልቻሉም ሲል ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ኢስት አፍሪካ አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ በህወሃት ኢህአዴግ በሚመራው ወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ወ/ሮ አያንቱ ሰኢድ የተባለች የድስት ወር ነፍሰጡር ሴት በምእራብ ሃረርጌ ዞን በቆቦ ከተማ መገደሏን ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ኢስት አፍሪካ ይኮንናል። የአያንቱ እህት በቪኦኤ ሬዲዮ ላይ ...

Read More »

የጣናን ደለል ለማውጣት ታስቦ የተገዛው ማሽን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም

የጣናን ደለል ለማውጣት ታስቦ የተገዛው ማሽን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወደ ጣና ሐይቅ በየዓመቱ የሚገባውን ከሰላሳ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ አፈር ለማስወገድ ታስቦ ከሶስት ዓመት በፊት በሃያ ሚሊዮን ብር የተገዛው የደለል ማውጫ ማሽን ካለ አገልግሎት መቀመጡ ታወቀ፡፡ ወደ ሐይቁ የሚገባውን ግዙፍ ደለል ለማውጣት ታስቦ በ2007 ዓ.ም የተገዛው የደለል ማውጫ ማሽን ያለአገልግሎት በጐርጐራ ወደብ መቀመጡን ...

Read More »

በምዕራብ ጉጂ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው

በምዕራብ ጉጂ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በጉጂና በጌዲዮ ማህበረሰብ መካከል የተነዛውን ወሬ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን በርካታ ዜጎች ሳይገደሉ አልቀረም። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጌዲዮ ዞን፣ ቡሌ ሆራና ሌሎችም አካባባቢዎች እየተሰደዱ ነው። የግጭቱ መንስኤ በውል ባይታወቅም ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች እንደሚሉት በጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ውስጥ ...

Read More »

በርካታ የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል ተኝተዋል

በርካታ የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል ተኝተዋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ተማሪዎች በመኝታ ክፋል በማምራት ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ በመፈጸማቸው በርካታ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሃረማያ ሆስፒታል ተኝተዋል። ተማሪዎቹ የታሰሩ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ወታደሮች “ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ መሰላችሁ?” በማለት ወደ ክፍላቸው እየገቡ እንደቀጠቀጡዋቸው ወኪላችን ገልጿል። ...

Read More »

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ከበዓለ-ሲመታቸው ጀምሮ ያሰሙት ንግግር ለአገራችን ፖለቲካዊ መረጋጋት ተስፋ ሰጪዎች ቢሆንም ሁሉንአቀፍ ለውጥ ለማምጣት አፋኝ ሕጎችን በማንሳት ተግባራዊ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ተናገሩ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ከተመረጡበት ጊዜ ...

Read More »