በምስራቅ ጉጂ ዞን የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ሚድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶና አካባቢው የወርቅ ማእድን ማውጣት ስራውን ለተጨማሪ 10 አመታት እንዲቀጥል የፈቃድ እድሳት ማግኘቱን ተከትሎ በሻኪሶና አካባቢው የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በለገንደቢ፣ አዶላና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝቡ እስከ እኩለቀን ድረስ ተቃውሞውን ሲያሰማ የዋለ ሲሆን፣ ከሰዓት በሁዋላ የንግድ ድርጅቶችን በመዝጋት ተቃውሞውን እየገለጸ ነው። ትናንት ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በእስር ላይ የሚገኘው እውቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ የሚጠይቅ የፌስ ቡክ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል። የአቶ አንድርጋቸው የትግል አጋሮች፣ ስለ ጓዳቸው የሚያስታወሱትን በማጻፍ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደግሞ እሱ ከጻፋቸው ጽሁፎች ሃሳቦችን በመውሰድ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ እየጣሩ ነው። በራሳቸው ተነሳሽነት የፌስቡክ ዘመቻውን ...
Read More »በአዲ ዳዕሮ ህዝቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጉ ተሰማ
በአዲ ዳዕሮ ህዝቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጉ ተሰማ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት በሚከሰቱ ከአድዋ ውሃ በቦቲ እየተወሰደ እንዲከፋፈል ተደርጓል። የከተማዋ ነዋሪዎች በቦቴ ከሚመጣው ውሃ ለመቅዳት ረጃጀም ወረፋዎችን መጠበቅ ግድ ብሏቸዋል። ከአድዋ የሚጫነውም ውሃ አልፎ አልፎ እንጅ በየጊዜው እንደማይመጣ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በተመሳሳይ ዜና በሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውሃ ከተቋረጠ ከሳምንት በላይ መሆኑንና ...
Read More »በሐዋይ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በሐዋይ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተቀሰቀሰ። የኪላዊያ እሳተ ጎሞራ ፍንዳታን ተከትሎም 2 ሺ የሚጠጉ ሰዎች በአስቸኳይ ከቀያቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። ትልቅ ስፋት አለው በተባለው ደሴት የተከሰተው እሳተ ጎመራ ፍንጣቂ ወደ ዛፎችና መንገዶች ላይ መወርወር መጀመሩ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል። የኪላዊያ እሳተ ጎመራ በአለም ላይ ከሚገኙትና በማንኛውም ሰአት ሊፈነዱ ይችላሉ ተብለው ከሚጠበቁት እሳተ ጎመራዎች አንዱ ነው። ዛሬ ላይ በሃዋይ ...
Read More »በባህርዳር ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ ጨዋታዎች ተሰረዙ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) የጸጥታ ስጋት በሚል ሰበብ በባህርዳር ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ ጨዋታዎች ተሰረዙ፡፡ ሚያዝያ 26 /2010 ባህርዳር ከነማ ከኮምቦልቻ ከነማ እንዲሁም አውሥኮድ እግር ኳስ ክለብ ከሰበታ ከነማ ክለብ ጋር ዛሬ የነበረው ጨዋታ ተሰርዟል። ውድድሩን ለመመልከት ሜዳ የገቡ ተመልካቾች ጨዋታው በመቋረጡ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባቸው የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእግር ኳስ ተመልካቾች ትኬት ቆርጠው ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን በመጠባበቅ ...
Read More »የባህርዳር ሁለገብ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ ርክክብ ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በባህርዳር የተገነባው ሁለገብ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ የአማራ ክልል መንግስት ከሜድሮክ ኢትዮጵያ ጋር የርክክብ ስነስርአት ፈጸመ። በ7 መቶ ሚሊየን ብር ተገንብቶ በ5 አመት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የባህርዳር ሁለገብ ስታዲየም የጣራና የወንበር ተከላ ሳይጠናቀቅ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርክክብ ፈጽሟል። በ2002 የተጀመረውና 8 አመታትን ያስቆጠረው የስታዲየሙ ግንባታ 4 መቶ ሚሊየን ብር ወጪ ከተደረገበት በኋላ በጅምር መቅረቱ ታውቋል። ሜድሮክ ኢትዮጵያ ስታዲየሙን ባለማጠናቀቁ ...
Read More »በሕወሃትና በዋልድባ መነኮሳቱ መካከል ያለው ውዝግብ 40 አመታትን አስቆጥሯል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በቅርቡ ከወህኒ የተለቀቁት የዋልድባ መነኮሳት በሕወሃትና በመነኮሳቱ መካከል ያለው ውዝግብ 40 አመታትን ያስቆጠረ መሆኑን ይፋ አደረጉ። ሕወሃት ጫካ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ በገዳሙ ሰላዮቹን ማሰማራቱን ይናገራሉ። መነኮሳቱ አባ ገብረኢየሱስና አባ ገብረስላሴ በገዳሙ መጸለይ ወንጀል ሆኖ በመከላከያ ሰራዊቱ መደብደባቸውን ተናግረዋል። ከታሰርን በኋላም ራሳችንን እስክንስት ተደብድበናል ያሉት የዋልድባ መነኮሳት በድብደባው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ...
Read More »በድሬዳዋ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በድሬዳዋ የሶማሌ ክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌን በመቃወም ሰልፍ ተደረገ። ዛሬ ከጁማአ ስግደት በኋላ በተደረገው ተቃውሞ የአብዲ ዒሌ አስተዳደር ከስልጣን እንዲወርድ ተጠይቋል። የሶማሌ ክልልን በሰፊው ያዳረሰው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህን ወቅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ሃላፊ በአብዲ ዒሌ በተላኩ ሰዎች ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። አብዲ ዒሌ የገጠማቸውን ተቃውሞ ለመቀልበስ ያዘጋጁት የድጋፍ ሰልፍም እንዳልተሳካ የደረሰን ...
Read More »የገዛህኝ ነብሮ ግድያ ሆን ተብሎ የታቀደ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) የኢትዮጵያውያን የመብት ተሟጋች ገዛህኝ ገብረመስቀል ነብሮ ግድያ ሆን ተብሎ የታቀደ መሆኑን አንድ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ገለጸ። ሳምንታዊው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ሜይል ኤንድ ዘጋርዲያን በዛሬው እትሙ ግድያው ከዘረፋ ጋር ያልተያያዘ መሆኑን የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጥር ሚያዚያ 21/2018 ከቀትር በኋላ 11 ሰአት ላይ በቀን ብርሃን፣ሕዝብ በሚተራመስበት ጎዳና ያምፔራ በተባለ ምግብ ቤት ደጃፍ ነበር ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያውያን ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በደቡብ አፍሪካ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሰባት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተሰማ። ከጆሀንስበርግ በ60 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ፓልም ሪች ወይም ቶኮዛ በሚባል አካባቢ ከትላንት ወዲያ ጀምሮ እስከዛሬ ጠዋት ድረስ 7 ኢትዮጵያውያን የተገደሉት በተደራጁ ዘራፊዎች በተወሰደ ርምጃ መሆኑ ታውቋል። 5ቱ የተገደሉት ትላንት ምሽት መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በቦታው ደርሶ ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል። የሟቾቹ ኢትዮጵያውያንን አስክሬን ወደ ...
Read More »