(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በዘመናዊ የወላይትኛ ሙዚቃው ከፍተኛ ዕውቅናን ያገኘው ኮይሻ ሴታ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ማረፉን ለማወቅ ተችሏል። የወላይትኛን ሙዚቃ በዘመናዊ መልክ በመጫወት ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ 2 አልበሞችን ለአድማጮቹ አድርሷል። የወላይትኛ ሙዚቃን ቀድሞ በማቀንቀን ለዛሬው የወላይትኛ ሙዚቃ የተሻለ መሆን ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከተም ይነገርለታል። በ1980ዎቹ አጋማሽ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ስማቸው ...
Read More »አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ መበተኑ ተገለጸ። ባለፈው ቅዳሜ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ብሉሚንግተን ከተማ የተጠራውን ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ባሰሙት ተቃውሞ ተቋርጧል። በተለይም የሶማሌ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስብሰባ አዳራሽ በመግባት እንዲቋረጥ ማደረጋቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከስብሰባ አዳራሹ በጓሮ በኩል እንዲሸሹ መደረጉንም ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ያለፈው ...
Read More »በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ተባባሰ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መባባሱ ተገለጸ። በጤፍ፣ በበርበሬ፣ በዘይት፣ በስኳር፣በቲማቲምና በተለያዩ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ኢሳት ወደ ተለያዩ ከተሞች በመደወል ካሰባሰበው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በከተሞች እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረው መሆኑም ታውቋል። መንግስት የኑሮ ውድነቱን ነጋዴዎችን ተጠያቂ በማድረግ እንደሚቀጣቸው ሲያስጠነቅቅ ነጋዴዎች ደግሞ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በመግለጽ የመንግስትን ወቀሳ ያጣጥላሉ። በሌላ በኩል በዚህ ...
Read More »ኦዴግ ከሕወሃት መንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ከመንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ። ቀጣዩን ድርድር በአዲስ አበባ ለማካሄድ የኦዴግ መሪዎች ሰሞኑን አዲስ አበባ እንደሚገቡም ተገልጿል። በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ድርድሩን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ከመንግስት ከተላኩ ሁለት ልኡካን ጋር መወያየቱን ገልጿል። የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ እንዳመለከተው ከመንግስት ልኡካን ጋር ድርድሩ የተካሄደው ባለፈው አርብና ቅዳሜ ነበር። ውይይቱ የተካሄደበት ስፍራ ...
Read More »በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ በስቅላት የተገደለችውን የ24 አመቷ ወጣት ሞት ለማስተባበል እየተሞከረ ነው
በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ በስቅላት የተገደለችውን የ24 አመቷ ወጣት ሞት ለማስተባበል እየተሞከረ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) ዘመዶችሽ እኔን ሊከሱ ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል በሚል ምክንያት በኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ በአቶ አብዲ ኢሌ ወታደሮች በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ ባለፈው ሃሙስ በስቅላት የተገደለችው የ24 አመቷ ወጣት ታሲር ኦማር ፎድን ግድያ ለማስተባበል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ወጣቷ ...
Read More »በአርበኞች ግንቦት7 የተከሰሱት በፍርድ ቤት ውስጥ መፈክር አሰሙ
በአርበኞች ግንቦት7 የተከሰሱት በፍርድ ቤት ውስጥ መፈክር አሰሙ (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ በአርበኞች ግንቦት 7 ተከሰው ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ መፈክር አሰምተዋል። የህሊና እስረኞች “ የነፃነት ታጋዮች እንጅ አሸባሪዎች አይደለንም፣ እንደ ማዕከላዊ እስር ቤት ቂሊንጦም ይዘጋ፣ ግፍ ይብቃ፣ ስቃይ ይብቃ” ብለዋል። በእነ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ጋር ተወያየሁ አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ከአቡነ ማትያስ ጋር በእርቅ ጉዳይ ላይ መነጋገርቸውን አስታወቁ። በውጭ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ሰላም በሚወርድበት ሁኔታ ላይ ከፓትሪያርኩ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። ዶክተር አብይ አሕመድ የደርግ ባለስልጣናት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ጭምር ይቅርታ አድርገንላቸው በሃገራቸው መኖር ይኖርባቸዋል ማለታቸውም ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይህንን የተናገሩት ...
Read More »ሃዋሳ በከፍተኛ የውሃ ችግር ተጠቅታለች ተባለ
ሃዋሳ በከፍተኛ የውሃ ችግር ተጠቅታለች ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የአዋሳ ህዝብ ንጹህ ውሃ ያገኛል ብሎ መናገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። በ15 ቀናት ውስጥ ለአንድ ወይም ለ2 ቀናት ለተወሰኑ ሰዓታት ውሃ ካገኙ በሁዋላ መልሶ እንደሚሄድባቸው የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ሰሞኑን ደግሞ ሴቶች የወንዝ ውሃ ፍለጋ ከ3 እስከ 4 ኪሎ ሜትር እየተጓዙ ነው። በአህያ ጭነው ውሃ ከሚያመጡ ...
Read More »አሜሪካ በኢራን ባለሃብቶችና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010) አሜሪካ በኢራን ባለሃብቶችና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች። ይህን ተከትሎም ኢራን ስምምነቱ በዚህ መልኩ የሚፈርስ ከሆነ ዩራኒየም የማበልጸጌን ስራ ለመጀመር ተዘጋጅቻለሁ ስትል ምላሿን ሰታለች። በሌላ በኩል እስራኤል ኢራን በሶሪያ ባላት የጦር ሰፈር ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱ ተሰምቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ2015ቱን የኢራንና የሃያላኑ ሃገራትን የዩራኒየም ማበልጸግ ስምምነት ማፍረስን ተከትሎ የተለያዩ ውዝግቦች በመነሳት ላይ ናቸው። ...
Read More »ስታራቴክስ ኢንተርናሽናል ወርቅ ፈላጊና አምራች ኩባንያ ፈቃድ ተሰረዘ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010) ስታራቴክስ ኢንተርናሽናል የተባለው ወርቅ ፈላጊና አምራች ኩባንያ ፈቃድ መሰረዙን ኩባንያው ይፋ አደረገ። በኢትዮጵያ አፋር አካባቢ ወርቅ በመፈለግና በማውጣት ሲንቀሳቀስ የቆየው ታኒ ስታራቴክስ ፈቃዱ እንዲታደስ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ መሰረዙን ኩባንያው አስታውቋል። በሻኪሶ ዞን የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሜድሮክ ንብረት የሆነው የለገደንቢ ወርቅ አምራች ኩባንያ ፈቃድም መታገዱ ይታወሳል። ኩባንያው ትላንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ...
Read More »