(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ ከእስር ተፈታ። የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ ከ13 አመታት በፊት በሕዝብ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ በመቃወም ሔሊኮፕተር ይዘው ወደ ጅቡቲ ከጠፉት የበረራ ባለሙያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት አመታት በፊት የታሰረው ሌላው የበረራ ባለሙያ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤም በተመሳሳይ ከወህኒ ቤት ወጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በኤርትራ ወህኒ ቤት ታስረው የነበሩት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህም በቅርቡ መፈታታቸው ታውቋል። ሰኔ ...
Read More »በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የወሰነው አዲስ ነገር የለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተወሰነ ምንም አዲስ ጉዳይ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። ሕዝብ ሳይወያይበት ለምን በአደባባይ ተገለጸ በሚል ሕወሃት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተም ከእንግዲህ የመደበቅ ፖለቲካ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አሰብን ስንሰጥስ ሕዝብን አወያይተናል ወይ በማለት ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ውጥረቱ ሊረግብ በድንበር ላይ ያለውም ሕዝብ እፎይ ሊል ይገባል ብለዋል። የኢትዮ-ኤርትራ ...
Read More »ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሽብር ድርጊት ሲፈጽም ቆይቷል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱ በኢትዮጵያውያን ላይ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። መከላከያና ደህንነቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ እንዲሆን ሕገ መንግስቱ ቢያዝም በተግባር ግን ይህ ሳይፈጸም መቆየቱንም ይፋ አድርገዋል። ግንቦት 7፣ኦነግና ኦብነግ ግዜ ካለፈበት የመሳሪያ ትግል ራሳቸውን አቅበው ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዶክተር ብርሃኑ እኔን ገድለው ወይንም አስገድለው ...
Read More »የኢድ አልፈጥር በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው
የኢድ አልፈጥር በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) 1 ሺህ 439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች በመከበር ላይ ሲሆን ሙስሊም ኢትዮጵያውያውን የተፈናቀሉ እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ዜጎችን እንዲያስቡ የሃይማኖቱ መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያለ ጸጥታ ችግር ተከብሯል። በጅጅጋ በአቶ አብዲ አሌ ትዕዛዝ በከተማው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢድ በአል በአደባባይ ...
Read More »በወላይታ ሶዶ በተደረገው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፋ
በወላይታ ሶዶ በተደረገው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፋ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲዳማ ማህበረሰብ አመታዊ የመን መለወጫ በአልን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የተገደሉ ዜጎችን ድርጊት ለመቃወም ዛሬ በወላይታ ሶዶ በተካሄደው ተቃውሞ እስከ 5 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን በርካታ የመንግስት መስሪያቤቶችና መኪኖች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሶዶ ከተማ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም፣ የዞኑ ባለስልጣናት ፈቃድ ...
Read More »ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ
ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ስምምነትን በተመለከተ ኢህአዴግ በቅርቡ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም እንዲሁን በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር የተወሰዱ ምደባዎችን ለመቃወም የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋል። ለሰለፉ ማካሄጃ ከፍተኛ ገንዘብ የተመደበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ከትግራይ ክልል በህወሃት ወጪ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ምንጮች ...
Read More »300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ
300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽብር ወንጀል ተከሰው ሞት እና የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው 289 እስረኞች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል። ከተፈቱት መካከል በእስር ቤት ውስጥ ጥፍሮቹ ተነቅለውና የተለያዩ የጭካኔ እርምጃዎች የተፈጸሙበት አበበ ካሴና ሌሎችም በአርበኞች ግንቦት7 ስም ታስረው የነበሩት ተለቀዋል። አበበ ካሴ በኢትዮጵያ ህዝብ ጸሎትና ትግል መፈታቱን ገልጾ ...
Read More »ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ
ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የለማ አስተዳደር የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ስራዎችን እየሰራ ነው። አቶ ለማ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ባደረጉ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል። የኦሮምያ ክልል የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በባህርዳር ተገኝተው ከተፈናቀሉት ዜጎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢን ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው ይችላሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን አቶ ተክለውልድ አጥናፉን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው እንደሚችሉ ተዘገበ። በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት ዶክተር ይናገር ደሴን ይሾማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወስኗል። ሆኖም አቶ በቃሉ ዘለቀ ከንግድ ባንክ ...
Read More »300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) በሽብር ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው 300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ። መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት እስረኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ከወህኒ ቤት እንደሚወጡም ተመልክቷል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው እስረኞች በአጠቃላይ 304 ሲሆኑ ፣ከነዚህ ውስጥ ከአስራ አምስቱ በቀር ሁሉም የአሽባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው ናቸው። አበበ ካሴ እና ከለንደን ሄዶ አዲስ አበባ ላይ የታሰረው አበበ ወንድም አገኝ ...
Read More »