ዶክተር ዓቢይና የለውጥ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም በሚያደርጉት ትግል አብረናቸው መሆናችንን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምላሽ ሰጠ።

ዶክተር ዓቢይና የለውጥ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም በሚያደርጉት ትግል አብረናቸው መሆናችንን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምላሽ ሰጠ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) “የሰለጠነ ፓለቲካ” የምንመርጠው፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው” በሚል ርዕስ አርበኞች ግንቦት ሰባት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ለምክር ቤት ያቀረቡትን የሥራ ዘገባ እና ከምክር ቤቱ አባላት ...

Read More »

በአሜሪካ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሚከተለውን የውጪ ፖሊሲ ተከትሎ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ። ፕሮ ፐብሊሺያ የተባለ የዜና ማሰራጫ ከቤተሰቦቻቸው ሲለያዩ ሕጻናቱ የሚያሰሙትን የሰቆቃ ድምጽ ቀርጾ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተቃውሞ ማየሉ ተሰምቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገወጥ በሚሏቸው ስደተኞች ላይ ያላቸው ፖሊሲ ርህራሄ የሌለው ነው በማለት በብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ ሲገጥመው ...

Read More »

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ይሰራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ሕዝብን የሚያገለገል ተቋም እንደሚሆን አዲሱ የተቋሙ ዋና ዳየሬክተር ገለጹ። በቅርቡ በጠቅላይ ሚንስትር አብየ እህመድ የተሾሙት የቀድሞው የአየር ሐይል አዣዥ ጄኔራል አደም መሀመድ እንደገለጹት ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ በመደራጀት ማሻሻያ ይደረግበታል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ትናንት ለፓርላማው ባደረጉት ገለጻ ደሕንነትና መከላከያው የፖለቲካ ወገንተኞችና የአፈና መሳሪያ ሆነው መቆየታቸውን መናገራቸው ይታወሳል። ...

Read More »

የብሄራዊ ባንክ ገዢው ከሥልጣን ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010)የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከሥልጣን ተነሱ በምትካቸው የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ተሹመዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ተመልክቷል። አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ሹመቱ ያልተጠበቀ እና ከሙያው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለሌላቸው የተሰጠ ሲሉ ተችተዋል። ከ10 ዓመታት በላይ በብሄራዊ  ባንክ ገዢነት የቆዩትና አሁን ከሃላፊነት የተነሱት  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ...

Read More »

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በአርጎባ ማህበረሰብ ተወላጆችና በፈንታሌ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩ የከረዩ ማህበረሰቦች መካከል ከመሬት ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ። ትናንት በነበረው ግጭት ቢያንስ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 7 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ...

Read More »

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰሞኑን በሲዳማ እና በወላይታ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዛሬ በጉታራ አዳራሽ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎችን ባወያዩበት ወቅት ፣ ህዝቡ ግጭቱን ያስነሱት የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ናቸው ብሎአል። ህዝቡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከስብሰባ አዳራሽ እንዲወጡ ቢጠየቁም እርሳቸው ግን ስብሰባውን ...

Read More »

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ተዘጋጀ

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ተዘጋጀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍና ለማበረታታት የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ይደረጋል። አስተባባሪዎቹ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰልፉ አላማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸውን ጅምር የማሻሻያ ሀሳቦች ለመደገፍ፣ለማመስገንና ይበልጥ ለማበረታታት ነው። ከዚህ በተረፈ ሰልፉ የማንንም ፓርቲ አጀንዳ አያስተናግድም ብለዋል ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ጉደታ ገላልቻ። በሀገሪቱ ህገ ...

Read More »

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግልጽነት የተሞባለትና በብዙዎች የተወደሱበትን የመጀመሪያ ሪፖርት አቀረቡ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግልጽነት የተሞባለትና በብዙዎች የተወደሱበትን የመጀመሪያ ሪፖርት አቀረቡ (ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን፣ ትንተናዎቻቸውና ገልጽነታቸው ንግግሩን በስሜት ያዳምጡ በነበሩ የማህበራዊ ሚዲያ ታዳሚዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል። ዶ/ር አብይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሁለት ጠ/ሚኒስትሮች ያደርጉ እንደነበረው ከፓርላማ ወንበራቸው ላይ ሆነው ሳይሆን፣ ሚኒስትሮችና የመምሪያ ሃላፊዎች መልስ ሲሰጡ ...

Read More »

በለኩ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደረሰ

በለኩ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደረሰ (ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ ከሃዋሳ 25 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ለኩ ከተማ ፣ የአብይ አህመድን አስተዳደር ያልተቀበሉ የደቡብ ክልል መሪዎች እንዳስነሱት በሚነገረው ግጭት በርካታ ጥፋት ደርሷል። የሲዳማ ወጣቶችን በማደራጀት በሌሎች ብሄሮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው የተደረገ ሲሆን፣ በርካታ የንግድ ቤቶች ወድመዋል። የአካባቢው የፖሊስ ሃይል ድርጊቱን በዝምታ መመልከቱን የአካባቢው ተወላጆች በጽኑ ...

Read More »

በኬንያ 8 የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናት ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) በኬንያ 8 የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናት አልሻባብ ጥቃት መገደላቸው ተሰማ። ባለስልጣናቱ የተገደሉት በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ይጓዙበት የነበረው ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደው ቦምብ በመፈንዳቱ ነው። ጥቃቱን የፈጸመው በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የአልሻባብ ቡድን በተደጋጋሚ ኬንያ ወደ ሶማሊያ የላከችውን የሰላም አስከባሪ ሃይል እንድታስወጣ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን ሮይተርስ በዘገባው አስፍሯል። ይህን ተከትሎም ተከታታይ ጥቃቶችን ሲፈጽም መቆየቱንም ዘገባው አመልክቷል። የኬንያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ቻርለስ ...

Read More »