የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም ያግዛል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያካሂዱት ውይይት ጥላቻና መከፋፈልን በማስወገድ ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም እንደሚያግዝ የጉብኝቱ የአቀባበል ኮሜቴ ገለጸ። በዋሽንግተን ዲሲ የአቀባበል ኮሜቴ ሰብሳቢዎች በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ ላይ ይሄ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት የችግሩ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት እድሉ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 28/2010 በዋሽንግተን ኮንቬንሽን ...

Read More »

የምህረት አዋጁ ጸደቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010)የምህረት አዋጁ ጸደቀ። የምህረት አዋጁ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና የሚፈለጉ እንዲሁም የተፈረደባቸውን ሰዎች ጭምር ነጻ የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል። ፓርላማው በአስቸኳይ ስብሰባው ያጸደቀው የምህረት አዋጁ ከግንቦት 30/2010 በፊት በወንጀል የሚፈለጉና የተፈረደባቸው እንዲሁም የተከሰሱ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። የምህረት አዋጁ የኮበለሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ነጻ የሚያደርግ ይሆናል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ ...

Read More »

ባለስልጣናት ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስኪያጅ መሾማቸው ተነገረ። ከሁለቱ መስሪያቤቶች የተነሱት የቀድሞ የስራ ሃላፊዎች ደግሞ በሌላ ቦታ ተመድበዋል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የአዲስ አበባ መንገዶች ባልስልጣናት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ናቸው። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ...

Read More »

የኤርትራ መንግስት ድንበር ላይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን እንዲነሳ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ12/2010) የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ አጎራባች ድንበር ለይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን ከአካባቢው እንዲነሱ ማድረጉን ሮይተርስ ዘገበ ። በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሰፈረው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እንዲነሳ የተደረገው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተወሰደውን የእርቅ እርምጃ መነሻ በማድረግ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮጵያ ከግጭቱ ወዲህ የመጀመሪያ የተባሉትን አምባሳደር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአስመራ መመደቧ ታውቋል ።  

Read More »

የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን ችግር በንግግር ለመፍታት ከአዲስ አበባ የተወከሉት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል። ልዑካኑ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በቤተመንግስት ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያይተዋል። ከአዲስ አበባ የመጡት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ማለዳ ዋሽንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ የሚገኙ አባቶችና ምዕመናን ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዚህ ሳምንት የሚጀመረው የእርቅ ሒደት ...

Read More »

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010) ለእረፍት ተበትኖ የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተነገረ። ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባውን በነገው እለት የሚያካሂደው በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ለነበሩ ሰዎች ምሕረት ለመስጠት በሚቀርብ ረቂቅቅ አዋጅ ላይ ለመምከር ነው ተብሏል። ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ረቂቅ አዋጅ እና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ፓርላማው በነገው ውሎው የህግና ፍትህ ...

Read More »

ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ማስወጣት ጀመረች

ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ማስወጣት ጀመረች ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )ሬውተርስ እንደዘገበው ኤርትራ ጦሯን ከድንበር ማስወጣት የጀመረችው የቀረበውን የእርቅ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ፍላጎት ለማሳየት ነው። ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መንገድ ጦሯን ከድንበር ለማስወጣት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ውሳኔ እየጠበቁ መሆናቸውን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል። ኤርትራ ጦሯን ማስወጣቷ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁልፍ እርምጃ ...

Read More »

የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ

የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )በሳውላ ዶ/ር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ ህዝቡ ያቀረባቸው የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዲሟሉለት ጠይቋል። የአስተዳደር ወሰን ፣ የሹመት እንዲሁም መንገድን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ጥያቄያቸውን መንግስት እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ጥያቄ አቀርበዋል። ህዝቡ ለውጡን ለሚመሩት የኢህአዴግ መሪዎች እና ለተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ያለውን ድጋፍም የተለያዩ ፎቶዎችን በመያዝ ድጋፉን ገልጿል።

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ።

የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እዬልኝ ሙሉ ዓለም እንደገለጹት የኮሚሽኑ ተግባር ሀብትን መመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፣ ሹመኛው ወይም ሠራተኛው ያስመዘገበው ሀብት ትክክል ነው? ወይስ አይደለም?የሚለው መረጋገጥ ጭምር እንደሆነ በመጥቀስ፤ መዝግቦ እና ማጣራት አድርጎ ያረጋጠውን ሀብት ለሕዝቡ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ባጋጠማት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ በረዥም ጊዜ ክፍያ ነዳጅ ለማስገባት ሳኡዲ አረቢያን ጠየቀች።

ኢትዮጵያ ባጋጠማት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ በረዥም ጊዜ ክፍያ ነዳጅ ለማስገባት ሳኡዲ አረቢያን ጠየቀች። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ረቡዕ ሀገራቸው ካጋጠማት የምንዛሬ እጥረት አንጻር በ12 ወራት ተከፍሎ በሚያልቅ እዳ የነዳጅ ዘይት እንድትሸጥላቸው ለሳኡዲ አረቢያ ጥያቄ እንዳቀረቡ መናገራቸውን፤ ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ብሄት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በበኩላቸው ...

Read More »