(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በቤንሻንጉል ክልል ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ 108 ሲቪሎች እና ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ ። የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን ዛሬ አዋሳ ላይ እንደተናገሩት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 20 ፖሊሶች እና 88 ሲቪሎች ታስረዋል። ግጭቱን የፈጠሩት ለውጡን ያልተቀበሉ እና ሥልጣን የሚፈልጉ ናቸው ብለዋል። ባለፈው ሰኔ የቤንሻንጉል ክልል ዋና ከተማ በሆነችው አሶሳ በተከሰተው ግጭት 14 ያህል ሰዎች ሲገደሉ ...
Read More »በደቡብ ክልል በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በደቡብ ክልል የም ወረዳ በተፈጠረ ግጭት በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በወረዳው ዋና ከተማ ሳጃ ግጭቱ የተከሰተው የመልካም አስተዳደር ችግር በመነሳቱ ነው ተብሏል። በእምነት ሰበብም በርካታ ሰዎች ሲገደሉ ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ የሚወስደው መንገድ በግጭት ምክንያት ተዘግቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በደቡብ ክልል የም ወረዳ ሳጃ ከተማ ከሐምሌ 4 ጀምሮ ...
Read More »የኪነጥበብ ባለሙያው ፍቃዱ ተክለማርያም አረፈ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010)አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ፍቃዱ ተክለማርያም ከዚህ አለም በሞት ተለየ። በገጠመው የኩላሊት ሕመም በ62 አመቱ ሕይወቱ ያለፈው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በሙያው ከፍተኛ አድናቆትና አክብሮት ያገኘ የመድረክ ፈርጥ ነበር። ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 24/2010 ከዚህ አለም በሞት የተለየው የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አስከሬን ዛሬ ከቀትር በኋላ ከነበረበት የጸበል ቦታ አዲስ አበባ ገብቷል። በ1948 አመተ ምህረት በአዲስ አበባ ከተማ የተወልደው የኪነጥበብ ባለሙያው ፍቃዱ ...
Read More »የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርን የማካለሉ ስራ እንዲጀመር ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ ያለውን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ለመፍታት የድንበር ማካለሉ በአስቸኳይ እንዲጀመር ሱዳን ጠየቀች። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ድሬድሪ ሞሐመድ እንደገለጹት በእርሻ ቦታ ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት የሚፈጠረውን የድንበር ግጭት ለመፍታት አስቸኳይ የማካለል ስራ መጀመር ይኖርበታል። በሱዳን ወታደሮችና በኢትዮጵያ ገበሬዎች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰተው ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ድሬድሪ ሞሐመድ በካርቱም ...
Read More »ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት መደረጉ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። አመራሮቹም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በሃገራቸው ጉዳይ ላይ በንቃት እንደሚሳተፉም አመልክተዋል። አክቲቪስት ታማኝ በየነ እንዲሁም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ጅዋር መሃመድ ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱም ዶክተር አብይ አህመድ ገልጸዋል። ለሳምንት ያህል በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ከኢትዮጵያውያን ጋር ሲወያዩ የቆዩትና ዛሬ አዲስ አበባ የተመለሱት ጠቅላይ ...
Read More »ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ አዲስ አበባ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) ብጹእ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ከሩብ ክፍለ ዘመን ስደት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽም ከፍተኛ አቀባበል እንደተዘጋጀላቸውም ታውቋል። ከሩብ ክፍለ ዘመን ስደት በኋላ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን የያዘው አይሮፕላን ዛሬ ከቀትር በኋላ 8 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ...
Read More »በአብዲ ዒሌ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሀምሌ 24/2010)በሶማሌ ክልል በክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ መቀጠሉ ተገለጸ። ላለፉት 3 ወራት በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ አብዲ ዒሌ ስልጣን እንዲለቅ ተጠይቋል። በአውበር ጂጂጋ ዞንና በአፍዴር ዞን ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸው ታውቋል። በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በጋሞጎፋ ሳውላ ባላፈው ሳምንት የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በጣና በለስ የስኳር ...
Read More »አርበኞች ግንቦት ሰባት ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሀምሌ 24/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገባ አስታወቀ። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የንቅናቄው አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት መደረጉን የጠቀሰው ንቅናቄው የተጀመረውን ለውጥ ወደ ግቡ እንዲደርስ ለማድረግ ወደ ሀገር ቤት መግባቱ አማራጭ የሌለው እንደሆነ በማመን ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።
Read More »የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጨረሻ ጉብኝታቸውን በሚኒሶታ አካሄዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሀምሌ 24/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ የመጨረሻ ጉብኝታቸውን በሚኒሶታ አካሄዱ። ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን በሚኒያፖሊስና ሴንት ፖል ከተሞች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የተገናኙት ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን ወደ ጎን አድርገው ለሀገራችን ለውጥ በአንድነት እንዲነሱ ጥሪ አድርገዋል። አቶ ለማ መገርሳም ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሁላችን የምትበቃ በመሆኑ ለእድገቷ በጋራ እንስራ ሲሉ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማምሻውንም በሚኒሶታ ...
Read More »ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 24/2010) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ላደረገው ልኡል እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዋል።እንዲሁም ይህ እርቅ ኣንዲወርድ አስተዋጻኦ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ምስጋናቸውን አቅረበዋል። መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎውን ሁሉ ተመኝተውላታል። ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ ...
Read More »