ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ካናቢስ”የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ወደ ለንደን ለማስገባት ስትሞክር የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት የ33 ወር እስራት ተፈረደባት። እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ፤በዋሽንግተን የኢትዮጵያኤምባሲ ውስጥ የምትሠራው አመለወርቅ ወንድማገኝ የተባለች ዲፕሎማት፤ የዲፕሎማቲክ ከለላዋን በመጠቀም 56 ኪሎ ግራም የሚመዝንካናቢስ- በሄትሮን አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ለንደን ለማስገባትስትሞክር ነው የተያዘችው። ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረውና በምዕራብ ለንደን የሚገኘው የአይስወርዝ ክራውን ...
Read More »መንግስት አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት መኖራቸውን በምስል አቅርቦ ማሳየት እንዳለበት ኢሳት አሳሰበ::
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መንግስት አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት መኖራቸውን የድምጽ ወይም የቪዲዮ ምስል አቅርቦ ማሳየት እንዳለበት ኢሳት አሳሰበ:: የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢዲቶሪያል ቦርድ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ዛሬ አቶ በረከት ስምኦን ኢሳት ላቀረበው ዜና የሰጡትን መልስ በማስመልከት ነው። አቶ በረከት ሪፖርተርና ሰንደቅ ለተባሉት ጋዜጦች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢሳትን ዜና በማስተባበል መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ በረከት ኢሳትን ...
Read More »ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመታዊ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ገለጸ።
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሃምሌ 22 እስከ ሃምሌ 24 ቀን 2004 ዓም ድርስ ባካሄደው የንቅናቄው አመታዊ ስብሰባ በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በስፋት በመነጋገር በአስቸኳይ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ባላቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላለፉት 21 አመታት የተገበራቸው የዘረኝነት ፖሊሲዎች ...
Read More »የፍትህ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ማእከላዊ ምርመራ ቀርቦ ቃሉን ሰጠ::
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ጋዜጠኛ ተመስገን በፌስ ቡክ ገጹ ባሰፈረው ማስታወሻ፦ በዛሬው ዕለት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተጠርቶ፦” ፍትህ ሚኒስቴር ክስ ስላቀረበብህ ቃልህን ስጥ”መባሉን ገልጿል። ከቀናት በፊት የታገደቸው ጋዜጣ ትለቀቅና ለንባብ ትውላለች ብሎ ሢያስብ፣ እሱ እና ባልደረቦቹ ባልነበሩበትና ባልተከራከሩበት ችሎት ቀርባ ‹‹ትወረስ›› የሚል ወሳኔ እንደተላለፈባት ተመስገን አስታውሷል። “ ካዛስ ምን ይሆናል?የተወረሰችውን ጋዜጣ መንግስት ሸጦ ገቢውን ይወስዳልን? ...
Read More »መንግስት የግል ትምህርት ቤቶችን መውረሱን አመነ::
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ የሚገኙ ከ102 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች መወረሳቸውን መንግስት አምኖአል። ኢሳት ከወራት በፊት፣ ራሳቸውን ማስተዳዳር የሚችሉ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት እንደዞሩ ዘገባ በሰራበት ወቅት፣ መንግስት ዜናውን ሲያስተባብል ነበር። ይሁን እንጅ የአዲስ አበባ መስተዳዳር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከ102 በላይ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት መዞራቸውን ገልጧል። መንግስት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የዘረጋውን የአንድ ...
Read More »የአለማቀፍ ግጭት ተንታኝ ቡድን ባለስልጣናት አቶ መለስ ዜናዊ አርፈዋል ይላሉ::
ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአለማቀፍ ግጭት ተንታኝ ቡድን ባለስልጣናት አቶ መለስ ዜናዊ አርፈዋል ይላሉ: ድርጅቱ በበኩሉ ዜናውን አስተባብሎአል ኢሳት የአለማቀፍ ግጭት ተንታኝ ቡድን በእንግሊዝኛው አጣራር አይ ሲ ጂ የውስጥ ጥናትና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን በመጥቀስ አቶ መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ተቋሙ በዛሬው እለት ማስተባበያ ያወጣ ሲሆን፣ በማስተባበያውም ፣ ተቋም የአቶ መለስ ዜናዊን የጤና ...
Read More »የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከመንግስት የድርድር ጥያቄ እንደቀረበለት ገለጠ::
ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጡት፣ ግንባሩ እስካሁን ድረስ ከመንግስት ጋር ድርድር ያላደረገ ቢሆንም፣ በኬንያ መንግስት በኩል የንግግር ጥያቄ እንደቀረበለት ተናግረዋል። የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ድርድሩ በገለልተኛ አገር መካሄድ እንዳለበት፣ አለማቀፍ ኮሚኒቲው ድርድሩን እንዲመራ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን አቶ ሀሰን ገልጠዋል:: ከብዙ ጊዜ ውይይት በሁዋላ ከመንግስት የቀረበውን ...
Read More »በሲዳማ ባህል አዳራሽ የተሰበሰቡ ሰዎች አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ተቃወሙ::
ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በጥንቃቄ የመረጣቸው የሲዳማ ተወላጆች በዛሬው እለት በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተሰብስበው የክልሉ መንግስት ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ህዝቡ እንዲጠይቅ አደርገዋል። 12 ጥያቄዎች ለባለስልጣናት የቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ” የሲዳማን ጥያቄ አሁን ለማቅረብ እንደማይቻል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሽሎአቸው ወደ ስራ ሲመለሱ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል። በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ፣ ...
Read More »ሀብታሞችና የኢህአዴግ አባላት ጭንቀት ውስጥ ናቸው::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ተሻሽሎ ከዛሬ ነገ ወደ አገር ይመለሳሉ በማለት ተስፋ አድርገው የነበሩት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም የኢህአዴግ አባላትና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ነው የኢሳት የመንግስት የውስጥ ምንጮች የሚናገሩት። ባለሀብቶች በየጊዜው ከባለስልጣናት መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ የገለጡት ምንጫችን ፣ ...
Read More »ከ20 ሺ በላይ ሰዎች የሞያሌን ግጭት በመሸሽ ኬንያ ገቡ::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ ቀይ መስቀልን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በተነሳው ግጭት 18 ሰዎች ተገድለው 12 ደግሞ ቆስለዋል። ኢሳት ትናንት ከአካካቢው ሰዎች እና ከተለያዩ ድርጅቶች ባሰባሰበው መረጃ 20 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የፌደራል ፖሊስ አባል መሆኑን፣ 7 የክልል ፖሊሶች መቁሰላቸውን ዘግቦ ነበር። ዛሬ በደረሰን ዘገባ ደግሞ የሟቾች ቁጥር 30 ደርሷል። ከ20 ...
Read More »