ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ የአሁኑ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ሰመጉ) ባወጣው 142ኛ ልዩ መግለጫ፣የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም28 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከህግ አግባብ ውጭ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ተደብድበዋል፣ በመደበኛ እስር ቤቶችና ከመደበና እስር ቤቶች ውጭ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፣ የደረሱበትም የማይታወቁ በርካታ ናቸው ብሎአል። ሰመጉ ከህግ ...
Read More »Amsterdam
የደህንነት ሃይሎች የባህርዳርን ጸጥታ መቆጣጠር ተስኖዋቸዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣የጥቃቱን ፈጻሚዎች ማንነት ለማወቅ አለመቻሉ ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ የክልሉን ደህንነት እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመራው የህውሃት ደህንነት ክፍል ጥቃቶችና አፈናዎችን መመከት አለመቻሉን የከተማዋ ነዋሪኦች ለክልሉ ወኪላችን ገልጸውላታል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ የተካሄዱትን ግድያዎችና አፈናዎች መመከት ያልቻለው የደህንነት ኃይሉ፣ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸሙትን ግለሰቦች መያዝ ...
Read More »የጎርፍ አደጋ በረሃብ የተጎዳውን ህዝብ ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ተመድ አስታወቀ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ከ3 ሳምንት በፊት በኦሮምያ በምዕራብ ሃረርጌ በሃዊ ጉዲና ወረዳ እና በአርሲ ዞን ሰሩ እና ጮሌ ወረዳዎች የጣለው ዝናብ በርካታ ዜጎችን አፈናቅሏል። በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በሃዊ ጉዲና ወረዳ 8 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ቆስለዋል። 3 ሺ 179 የቀንድ ከብቶች አልቀዋል። በአርሲ ...
Read More »ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ ታገደ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ማስ ሚዲያ ውስጥ ጋዜጠኛ የሆነውና በድፍረት በሚሰነዝራቸው ትችቶች የሚታወቀው ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ መታገዱንና የመንግስትን ስም በማጥፋት ሊከሰስ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም ከስራ መታገደኑን ወደ መስሪያ ቤት ሲገባ መከልከሉን ኢሳት ለማረጋገጥ ችሎአል። ፍቅርማርያም ጥልቅ ተሃድሶ በሚል በአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለጋዜጠኞች በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ፣ የህወሃትን ...
Read More »በኮሪያ በኢትዮጵያ ኢምባሲ የተጠራዉ የግንቦት 20 በአል ዝግጅት ተቃውሞ ገጠመው
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ3 ቀናት በፊት በአምባሳደር ሽፈራዉ ጃርሶ የሚመራው ኢምባሲ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ዉስጥ በሚገኘው ባለ 5 ኮከብ ሎቴ ሆቴል ያዘጋጀው ዝግጅት በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዳጋጠው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ኢምባሲው የሚስጥር ጥሪ ወረቀት መላኩንና እንግዳ ሆነው የተገኙት የህወሃት አባላት ብቻ መሆናቸውን የሚገለጹት ኢትዮጵያውያን፣ በግብዣው ...
Read More »በጎዴ አንድ የአይር ሃይል ባልደረባ በርካታ መኮንኖችን ገድሎ ራሱን ማጥፋቱ ተሰማ
ግንቦት ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር በምትገኘው ጎዴ ከተማ የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው የጎንደር ተወላጅ ወታደር በርካታ መኮንኖችን ገድሎ በመጨረሻም ራሱን አጥፍቷል። ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው በአየር ሃይል የምህንድስና ትምህርት ተምሮ ጎዴ በእግረኛ ወታደርነት መመደቡን ተከትሎ ነው። ምንጮች እንደገለጹት ፣ ወታደሩ ያለምንም ምክንያት ወደ ጎዴ ተወስዶ በእግረኛ ወታደር ...
Read More »ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በ1 አመት ከስድስት ወር እስር ተቀጣ
ግንቦት ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራውን በአንድ አመት ከስድስት ወር እንዲቀጣ የወሰነበት ሲሆን፣ ጌታቸው የእስሩን ጊዜ የጨረሰ በመሆኑ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ጌታቸው የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 257 ሀ እና መ ን በመተላለፍ ህዝቡን ለአመጽ ...
Read More »በአዳማ ከተማ የመኪና አደጋና የአስተዳደር ችግር ተባብሰው ቀጥሎአል
ግንቦት ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ ውስጥ ያሉት ነባርና አዲስ የትራፊክ መብራቶች ከአምስት ዓመት እስከ ሁለት ዓመታት ድረስ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው ለትራፊክ አደጋዎች መበራከት ከፍተኛውን ድርሻ መውሰዱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።የፈረስ ጋሪን ቦታ የተኩት ባጆች ለብቻ የሚጓዙበት መንገድ አለመሰራቱም ለመንገዶች መጨናነቅና ለተደጋጋሚ የመኪና አደጋ መከሰት ተጨማሪ ምክንያት ሆነዋል። ከተማዋ በየጊዜው ከንቲባዎችን ቀያይራለች። ከኅዳር 11 ቀን ...
Read More »ኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ዝግጅት መጨረሷ ታወቀ
ግንቦት ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በአካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ሃይሎችን እና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩትን ለመግታት በሚል በሁለቱ አገራት የጋራ ጦር የተቋቋመው ወታደራዊ እዝ፣ ሰፊ የሆነ የኢትዮጵያን ግዛት ለሱዳን ለማስረከብ እንቅስቃሴ ጀምሯል። የጋራ ጥምር ጦሩ በኢትዮጵያ አርሶአደሮች በኩል ሊቀርብ የሚችለውን ማንኛውንም ተቃውሞ ለመጨፍለቅ በዝግጅት ላይ ነው። ሰሞኑን የእርሻ መሬቱን ለማስረከብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ...
Read More »ምስራቅ እዝን ለአመታት የመራውና በከፍተኛ ሙስናና ወንጀል የሚከሰሰው ጄኔራል አብረሃ በሌላ በሙስና በተዘፈቀ አዛዥ ተተካ
ግንቦት ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው በሶማሊ ክልል ለተፈጸመው ከፍተኛ እልቂት ተጠያቂ የሆነውና ከሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር ከፍተኛ የሙስና ትስስር እንዳለው የሚነገርለት ጄ/ል አብረሃ ወይም በቅጽል ስሙ ኳርተር፣ በሌላው በሙስና በተዘፈቀው ጄኔራል ማሹ በየነ መተካቱ ታውቋል። ጄ/ል አብርሃ ከምስራቅ እዝ ሃላፊነት ተነስቶ የመከላከያ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ሆኖ ተሹሟል። ጄ/ል ሳሞራ ...
Read More »