አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ካለ ሕግ ማሰርን፣ በግዳጅ ማፈናቀልና ሰቆቃን ማስቆም አልቻሉም ሲል ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ኢስት አፍሪካ አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ በህወሃት ኢህአዴግ በሚመራው ወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ወ/ሮ አያንቱ ሰኢድ የተባለች የድስት ወር ነፍሰጡር ሴት በምእራብ ሃረርጌ ዞን በቆቦ ከተማ መገደሏን ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ኢስት አፍሪካ ይኮንናል። የአያንቱ እህት በቪኦኤ ሬዲዮ ላይ ...
Read More »Amsterdam
የጣናን ደለል ለማውጣት ታስቦ የተገዛው ማሽን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም
የጣናን ደለል ለማውጣት ታስቦ የተገዛው ማሽን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወደ ጣና ሐይቅ በየዓመቱ የሚገባውን ከሰላሳ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ አፈር ለማስወገድ ታስቦ ከሶስት ዓመት በፊት በሃያ ሚሊዮን ብር የተገዛው የደለል ማውጫ ማሽን ካለ አገልግሎት መቀመጡ ታወቀ፡፡ ወደ ሐይቁ የሚገባውን ግዙፍ ደለል ለማውጣት ታስቦ በ2007 ዓ.ም የተገዛው የደለል ማውጫ ማሽን ያለአገልግሎት በጐርጐራ ወደብ መቀመጡን ...
Read More »በምዕራብ ጉጂ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው
በምዕራብ ጉጂ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በጉጂና በጌዲዮ ማህበረሰብ መካከል የተነዛውን ወሬ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን በርካታ ዜጎች ሳይገደሉ አልቀረም። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጌዲዮ ዞን፣ ቡሌ ሆራና ሌሎችም አካባባቢዎች እየተሰደዱ ነው። የግጭቱ መንስኤ በውል ባይታወቅም ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች እንደሚሉት በጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ውስጥ ...
Read More »በርካታ የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል ተኝተዋል
በርካታ የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል ተኝተዋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ተማሪዎች በመኝታ ክፋል በማምራት ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ በመፈጸማቸው በርካታ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሃረማያ ሆስፒታል ተኝተዋል። ተማሪዎቹ የታሰሩ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ወታደሮች “ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ መሰላችሁ?” በማለት ወደ ክፍላቸው እየገቡ እንደቀጠቀጡዋቸው ወኪላችን ገልጿል። ...
Read More »ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ከበዓለ-ሲመታቸው ጀምሮ ያሰሙት ንግግር ለአገራችን ፖለቲካዊ መረጋጋት ተስፋ ሰጪዎች ቢሆንም ሁሉንአቀፍ ለውጥ ለማምጣት አፋኝ ሕጎችን በማንሳት ተግባራዊ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ተናገሩ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ከተመረጡበት ጊዜ ...
Read More »በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ
በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ ...
Read More »የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው
የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) ነባሮቹ የኢህአዴግ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት አለው ብለው እንደማያምኑ እየተናገሩ ነው። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት ነባር ከሆኑት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ስዩም መስፍንና ሌሎችም በድርጅቱ ውስጥ የቆዩ ...
Read More »የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ
የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲ ረመጥ ወረዳ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት “የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ትግራይ ቅርንጫፍ” የካቲት 2 ቀን 2010 ዓም አዲስ ክስ እንደቀረበባቸው አመልክተዋል። “ከወንጀል ሕግ አልፎ በሽብርተኝነት ተከሰው የነበሩ ሰዎች ክሳቸው በተቋረጠበት ሁኔታ በእኛ ላይ አዲስ ክስ መመስረቱ የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ...
Read More »የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ያጸደቁት ኤች አር 128 በመባል የሚጠራው ህግ ሉአላዊነትን የሚጥስ ነው በማለት አገዛዙ ተቃውሞውን ገለጸ
የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ያጸደቁት ኤች አር 128 በመባል የሚጠራው ህግ ሉአላዊነትን የሚጥስ ነው በማለት አገዛዙ ተቃውሞውን ገለጸ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ ስብአዊ መብት እንዲከበር ለማስገደድ ያጸደው ህግ በርካታ ለነጻነታቸው የሚታገሉ ዜጎችን ያስደሰተ ቢሆንም፣ በአገዛዙ በኩል ግን በበጎ መልኩ አልታዬም። ይህ በርካታ አስገዳጅ አንቀጾችን የያዘው ህግ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተፈጸሙት ግድያዎችና አፈናዎች በተመድ ገልለተኛ ...
Read More »በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።
በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በአፋር ክልል ኩናባ ወረዳ ዋህደስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱዳ በተባለ ተራራ ትናንት ማክሰኞ በትግራይ ታጣቂ ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከትግራይ ሚሊሻዎች በኩል ሁለት መሞታቸውን የዓይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ አካባቢ በሚሊሻዎቹና በአርብቶ አደሮቹ መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲቀሰቀሱ ቆይተዋል። ...
Read More »