Amsterdam

በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የተጣለውን ቅጣት በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ ደጋፊዎችና አጋሮቻቸው ተቃውሟቸውን አሰሙ፤ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ታመው ሆስፒታል ገቡ

በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የተጣለውን ቅጣት በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ ደጋፊዎችና አጋሮቻቸው ተቃውሟቸውን አሰሙ፤ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ታመው ሆስፒታል ገቡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵይያ በእግር ኳስ ሜዳዎች ከከስፖርት መርህ ውጪ ስርዓት አልበኝነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተሳፋ መጥቷል። በዚህም የብዙ ሰላማዊ ዜጎች ህይወትና ንብረት ለመውደም ምክንያት ሆኗል። ችግሩን ከመሰርቱ እንዲፈታ ወቅታዊ የሕግ እርምጃዎች መውሰድ የነበረበት ...

Read More »

ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለሕክምና ወደ ስላሴ ክሊኒክ በመኪና እየተጓዘ እያለ በድንገተኛ አደጋ ራሱን ስቶ ሕይወቱ አልፏል። ድምጻዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር። በሻሸመኔና ሃዋሳ ከተማ አማካኝ ላይ በምትገኘው በጥቁር ውሃ ከተማ በ1971 ዓ.ም የተወለደውና በሻሸመኔ ከተማ ያደገው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለቤተሰቦቹ 2ኛ ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ሶስት ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል

በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ሶስት ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) በሞያሌ ከተማ ሰላማዊ ዜጎች በሚበዙበት በከተማዋ መናሃሪያ አካባቢ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት እስካሁን ሶስት ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በጥቃቱ ከመቶ በላይ ሰላማዊ ዜጎች በደረሰባቸው ጉዳት ቆስለው ወደ ከተማዋ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መሃከል ህጻናት፣ሴቶችና አዛውንቶች ...

Read More »

በቡሌ ሆራ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ

በቡሌ ሆራ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሁለት ቀናት በፊት በጉጂ እና ጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ቆስለው በከተማው በሚገኝ ሆስፒታል የተጠለሉ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ያበሳጫቸው የሆስፒታሉ ሰራተኞች፣ በቁስለኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ ከኢትዮጵያ ባህል የወጣና ሰብአዊ መብትንም የሚጥስ በመሆኑ ገለልተኛ አካላት አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ...

Read More »

በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ለሰዓታት ተስተጓጉለው ውለዋል።

በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ለሰዓታት ተስተጓጉለው ውለዋል። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) የቢቢሲው የአዲስ አበባ ወኪል ኢማኑኤል ኢንጉዛ ከሥፍራው እንደዘገበው የአየር መንገዱ የአየር ትራፊክ ሠራተኞች ዛሬ ማለዳ ላይ አድማ በመምታታቸው የኬንያው ኬ ኪው ወደ ናይሮቢ የሚያደርገውን ጉዞ ጨምሮ የበርካታ አየር መንገዶች በረራ ለሰዓታት ተስተጓጉሏል። የአየር ትራፊክ ሠራተኞቹ መሣሪያዎቻቸውን በማውረድ ማደማቸውን ያወሳው የቢቢሲው ዘጋቢ፣ የአመጻቸው ምክንያት ...

Read More »

የዳባት ወረዳ ነዋሪዎች ወልቃይትና ሴቲት ሁመራ እንደሚመለስላቸው ጠየቁ

የዳባት ወረዳ ነዋሪዎች ወልቃይትና ሴቲት ሁመራ እንደሚመለስላቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ዳባት ከአመታት በፊት የነበራትን ሰባት ወረዳዎች በማጣት በሰሜን የነበሩትን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ክልል እና ወደ ሰሜን ጎንደር ተከፋፍሎ በመሰጠቱ፤ ዛሬ ያላት የህዝብ ብዛት ተመናምኗል፡፡ ይህም ለልማት የሚመደብላትን ገንዘብ አነስተኛ እንዲሆን አድርጓል፡፡ እነዚህ ችግሮች ባለመነሳታቸው ከተማዋ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣ ባለችበት መቆየቷ በየጊዜው በወረዳዋ ለሚከሰተው ችግር ...

Read More »

40 ሚሊዮን ብር የወጣበት የጣናን ደለል ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ በዝገት ሲበላ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተባለ

40 ሚሊዮን ብር የወጣበት የጣናን ደለል ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ በዝገት ሲበላ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተባለ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢሳት ትናንት ሰኞ አንድ የመንግስት ባለስልጣንን ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የጣና ደለልን ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ መቀመጡን ገልጾ ነበር። ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ባለስልጣኑ የሰጡት መረጃ የተዛባ ነው። ማሽኑ ...

Read More »

በጉጅና በጌዲዮ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ትናንት ምሽት ብቻ በቡሌ ሆራ ከተማ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

በጉጅና በጌዲዮ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ትናንት ምሽት ብቻ በቡሌ ሆራ ከተማ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) የተለያዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ሰሞኑን በሁለቱ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ትናንት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች በጩቤ ተገድለዋል። በአካባቢው ብቻ እስካሁን የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ20 ይበልጣል። ከ15 በላይ መኪኖች ስደተኞችን ይዘው በከተማው አስተዳደር ተጠልለው የቆዩ ቢሆንም፣ ...

Read More »

በኮሬ እና በጉጂ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው

በኮሬ እና በጉጂ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከሃምሌ 2009 ዓም ጀምሮ በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት አንዴ ከፍ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ እንዳዲስ በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው። ሰሞኑን በተነሳው ግጭት ከሁለቱም ወገን 5 ሰዎች ሲገደሉ 11 ሰዎች ...

Read More »

መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ

መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳቡን በድፍረት በመግለጽ የሚታወቀው መምህር ስዩም ተሾመ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፎ አገዛዙን ተቃውሟል በሚል ለወር ያክል ጊዜ ከታሰረ በሁዋላ ዛሬ ከእስር ቤት ተለቋል። በተመሳሳይ መንገድ የታሰረው የኦሮምያ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደዓም እንዲሁ ከእስር ተለቋል። ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ ...

Read More »