Amsterdam

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) ግድቡን በዋና ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ስመኛው በቀለ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በቪ 8 መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱን የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ዘይኑ፣ ኢንጂነር ስመኛው ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደነበረ፣ በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ...

Read More »

በሳውላ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ

በሳውላ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጎፋ ወረዳ ሳውላ ከተማ ላይ ዛሬ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፣ በደኢህዴን ባለስልጣናትና እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ለሳምንት የቆዬ ውዝግብ ነበር። ባለፈው ሳምንት ለዶ/ር አብይ የተደረገውን የድጋፍ ስልፍ ተከትሎ ህዝቡ የአካባቢውን ባለስልጣናት መቃወሙ ያስቆጣቸው የወረዳው ባለስልጣናት በወጣቶቹ ላይ ...

Read More »

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) አቶ ተስፋዬ ጌታቸው አሜሪካ ውስጥ ህክምኛ እየተደረገላቸው በነበረበት ወቅት ማረፋቸው ታውቋል። የአማራ ክልል የገበያ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ተስፋዬ፣ በቅርቡ ደግሞ የብአዴን ማእከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመው ነበር። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ...

Read More »

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ።

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን 400 የፓርላማ አባላት ቅንጡ መኪና እንዲገዙ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ዶላር በብድር መልክ መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ።

የደቡብ ሱዳን 400 የፓርላማ አባላት ቅንጡ መኪና እንዲገዙ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ዶላር በብድር መልክ መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) ቢቢሲ እንደዘገበው የሳልቫኪር መንግስት አጠቃላይ ለፓርላማ አባላቱ መኪና መግዣ 16 ሚሊዮን ዶላር ነው ያወጣው። የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ “የፓርላማ አባሎቻችን ሞተር ባይስክል መጠቀም የለባቸውም” በማለት ውሳኔው ትክክል እንደሆነ ለመከላከል ሞክረዋል። የፓርላማ አባላቱ የሳልቫኪር የሥልጣን ...

Read More »

የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ለደረሰባቸው ጥቃት አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸውና ጥያቄያቸውም እንዲመለስላቸው ጠየቁ

የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ለደረሰባቸው ጥቃት አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸውና ጥያቄያቸውም እንዲመለስላቸው ጠየቁ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) የማህበረሰቡ ተወካዮች ለጠ/ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ዘንድሮም ሆነ ከዚህ ቀደም በተነሳው ጥያቄ ምክንያት ለአመታት ለተፈጸመው የሰው እልቂት ለሟች ቤተሰቦች የደም ካሳ እንዲከፈል ጠይቀዋል። “በዘንድሮው እልቂት፣ በተቋማትና ንብረት መውደም መንስኤ የሆኑ ንጹሃንን በማደናገር አሳስተው አሰለፉ፣ ጥፋትና ውድመት ያደረሱ ያደረሱ በየደረጃው ያሉ አካላት ...

Read More »

በሃረር ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ በመምጣቱ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው

በሃረር ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ በመምጣቱ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደገለጸው በአካባቢው የሚታዬው ስርዓት አልበኝነት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በቄሮ ስም የሚነግዱ ወጣቶች ውሃ ወደ ሃረር ከተማ እንዳይገባ ለማድረግ የየረርን ትልቁን የውሃ ቧንቧ በመስበር ውሃ መከልከላቸው ታውቋል። በሃሮማያ አካባቢ ደግሞ ውሃ በቦቴ ወደ ሃረር እንዳይገባ ለማድረግ የመኪኖችን ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በደብረማርቆስና አርባ ምንጭ እስር ቤት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ በወልድያ፣ ፍኖተሰላም፣ ሸዋ ሮቢትና መቀሌ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሷል። በወልድያ እስር ቤት በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 2 ሰዎች ሲሞቱ 3 ሰዎድ ደግሞ ቆስለዋል። በመቀሌ እስር ቤት በተነሳው ቃጠሎም ...

Read More »

የማምረቻ እንዱስትሪዎች በዶላር እጥረት ለቅሶ ላይ ነን ሲሉ ባለሀብቶች ተናገሩ

የማምረቻ እንዱስትሪዎች በዶላር እጥረት ለቅሶ ላይ ነን ሲሉ ባለሀብቶች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኢትዮጵያ የማምረቻ እንዱስትሪ ባለሀብቶች ከአዲሱ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ከአቶ ይናገር ደሴ ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ያለውን የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠቱ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣባቸው ነው። የሲዲኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት 800 ሰራተኞችን ቢያስተዳድሩም፣ ወደ አምራች እንዱስትሪ የገቡበትን ...

Read More »

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጂድ ውስጥ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጂድ ውስጥ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በትናንትናው እለት በደሴ ከተማ ሸዋ በር በመባል በሚጠራው መስጂድ ውስጥ ድምጽ አልባ የስለት መሳሪዎችን ይዘው በመግባት መስኪዱ ውስጥ የነበሩ ምእመናን ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በመስጅዱ ሃይማኖታዊ ፀሎት በማድረግ ላይ እያሉ ቁርአን እናስቀራለን በሚሉና አናስቀራም በሚሉ መሃከል አለመግባባት መፈጠሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በወቅቱ በተከሠተው ...

Read More »