Amsterdam

በሶማሊያዋ ኪስማዩ ከተማ 3 የኢትዮጵያ  የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በቦንብ ተገደሉ

ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊዋ የሶማሊያ ወደብ ከተማ ኪሲማዩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ጦር የሆኑት ሶስት የኢትዮጵያ መከላከያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቅዳሜ እለት በቦንብ ፍንዳታ ተገድለዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች  ከኪሲማዩ ከተማ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትከኘው ከማእድን ማውጫዋ ቡሉ ጋዱድ መንደር በወታደራዊ ኮንቮይ መኪና ተጭነው ሲመጡ ጥቃቱ እንደደረሰባቸው የአካባቢው ...

Read More »

13 የሃይማኖት አባቶችና ካህናት በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት 7ትን ተቀላቅለው ህዝብን በማስተባባር ላይ መሆናቸውን ገለጹ ።

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲያገለግሉ የነበሩ 13ቱ አባቶች ወደ በረሃ ለመውረድ የወሰኑት አገዛዙ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ዝም ለማለት ህሊናቸውና ሃይማኖታቸው ስላልፈቀደ መሆኑን ተናግረዋል። ጠመንጃ ይዘን ባንዋጋም ፣ በረሃ ወርደን ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲነሳ እየቀሰቀስነው ነው ያሉት አባቶች፣ በረሃ ውስጥ ከአርበኞች ግንቦት7 አደራጆች ጋር ከተገናኙ በሁዋላ የኢትዮጵያ ወጣት ትግሉን እንዲቀላቀል ...

Read More »

በደቡብ ኢትዮጵያ ግድያውና እስራቱ ቀጥሎአል

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎች፣ በፓርቲ አባላት እና በህዝብ ላይ ወታደራዊ የኃይል እርምጃን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ  ህዳር 5 /2009 ዓ.ም የኦሞ ህዝቦች ዲሞክርሲዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ተጠሪ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የዞኑ ...

Read More »

የብአዴን አባላት በባህርዳር ከተማ ያለአግባብ የታሰሩ ነጋዴዎች እንዲፈቱ በድጋሜ ተጠየቀ፡፡

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዥው መንግስት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የብአዴን አባላትን በየክፍለ ከተማው ሰብስቦ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያና በተከሰቱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሰሞኑን ባነጋገረበት ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የታሰሩት ነጋዴዎችን ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አባላቱ ጠይቀዋል። ጥያቄውን ያቀረቡት የብአዴን አባላት እንደተናገሩት የታሰሩት ነጋዴዎች በአጋጣሚ የንግድ ድርጅታቸውን ከፈተው አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙት ብቻ መሆናቸውን ገልጸው ...

Read More »

ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ሽሮሜዳ አካባቢ ጋደኛቸውን ለማየት ሲሄዱ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፣ አናኒያ ሶሪና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባል የነበረው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከመንገድ ላይ ተይዘው ታስረዋል። ጋዜጠኛ አናኒና ሶሪ እና ኤሊያስ ገብሩ ገርጂ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣  አቶ ዳንኤል ሺበሺ  የታሰሩበትን አድራሻ ለማወቅ አልተቻለም።

Read More »

የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ከህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ጋር በቀብትያ ሁመራ እና አጎራባች ቀበሌዎች  እየተዋጋ ነው

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ እንደገለጹት፣ አባሎቻቸው በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ለወራት ሲደራጁና ሲያደራጁ ከቆዩ በሁዋላ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ ከትናንት ጀምሮ በቃፍታ ሁመራ እና በአከር አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። አደንድን በሚባል አካባቢ ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጦርነት 48 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን የገለጹት አስተባባሪው፣ ከትናንት ...

Read More »

በአባይ ግድብ አካባቢ ያለው የስራ እንቅስቃሴ መዳከሙን ጋዜጠኞች ገለጹ ።

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹ በአባይ ግድብ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ቆሟል የሚል ወሬ በስፋት እየተወራ ነውና ወሬውን አክሽፉ!” ተብለው ለጉብኝት የተላኩት ጋዜጠኞች ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ ባለማየታቸው የሚወራው ትክክል መሆኑን አረጋጋጥው መመለሳቸውን ለኢሳት ገለጹ። ሰሞኑን ወደ አባይ ግድብ የተላከው የ መንግስት ጋዜጠኞች ቡድን ለጉብኝት በቆየበት አንድ ቀን፤ ምንም አይነት ስራ ሲሰራ አለመመልከቱን ገልጿል፡፡ ‹‹ ለአንድም ...

Read More »

በሶማሊያ ክልል በኮሌራ ወረሽኝ 35 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢዎች በኮሌራ በሽታ 35 ሰዎች መሞታቸውንና ድርቁን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አስታወቀ። በድርቁ ምክንያት እንስሳት እየሞቱ ነው። የምግብ እጥረት ተጠቂ የሆኑት የኦጋዴን ነዋሪዎች አፋጣኝ እርዳታ ካላገኙ አደጋው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ለጋሽ የረድኤት ድርጅቶች ለነዋሪዎቹ የሚያደርጉትን ሰብዓዊ እገዛዎች እንዳያሰራጩ ...

Read More »

በኢንተርኔት አፈና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች ።

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዜጎቻቸው ላይ አፈና በማድረግ የመረጃ እቀባ ከሚያደርጉ አገራት ውስጥ ቻይና፣ ሶሪያ እና ኢራንን በመከተል ኢትዮጵያ በዓለም አራተኛ፣ በአፍሪካ ደግሞ በአንደኝኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ፍሪደም ሃውስ አስታውቋል። በኢንተርኔት ስርጭት ሁዋላ ቀር የሆነችው ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጎቿ ላይ በምታደርገው እቀባዎችና አፈናዎች ግን ቀዳሚ ሆናለች ብሎአል። አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በመላው ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር አንድ የኮማንድፖስት አባል ሁለት ወጣቶችንና አንድ ፖሊስ ሲገድል  የወልቃይት ተወላጆችም እየታደኑ ነው ።

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገሪቱን እየመራ ያለው ወታደራዊ እዝ በእንግሊዝኛው ኮማንድ ፖስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጽማቸው ግድያዎችና አፈናዎች እየጨመሩ በመምጣት ላይ ናቸው። በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ በዳባት ከተማ ከአካባቢው አርሶአደሮች ተውጣጥቶ ጉጅሌ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የኮማንድ ፖስት አባል የሆነው ንጋት ምስጋናው ሁለት የወገራ ደሲያ አካባቢ ተወላጆችን ከእስር ቤት በማውጣት በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ሲሆን፣ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው ...

Read More »