ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ሽሮሜዳ አካባቢ ጋደኛቸውን ለማየት ሲሄዱ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፣ አናኒያ ሶሪና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባል የነበረው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከመንገድ ላይ ተይዘው ታስረዋል። ጋዜጠኛ አናኒና ሶሪ እና ኤሊያስ ገብሩ ገርጂ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣  አቶ ዳንኤል ሺበሺ  የታሰሩበትን አድራሻ ለማወቅ አልተቻለም።