Amsterdam

በቡሌ ሆራ እስር ቤቶች ሞልተው ተጨማሪ እስር ቤቶች እየተከፈቱ ነው

ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ከተማ ከተለያዩ ቀበሌዎች እየተያዙ የሚታሰሩ አርሶአደሮች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ በቅርቡ ከተከፈቱት ሁለት እስር ቤቶች በተጨማሪ ሌሎች እስር ቤቶች መከፈታቸውንና እነሱም መሙላታቸውን ተናግረዋል። ልጆቻቸውን የሚያጠቡ እናቶች፣ ወጣቶች፣ አዋቂዎችና በእድሜ የገፉ አዛውንት ሳይቀር መታሰራቸውን የሚገልጹት እነዚሁ ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ሰአት አቅሙ ያላቸው ሰዎች አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን፣ አቅሙ የሌላቸው ግን ...

Read More »

የብር የምንዛሬ ዋጋ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ነው

ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከተከሰተው ህዝባዊ አመጽ በሁዋላ የዶላር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል። በህጋዊ ገበያ በ23  ብር ገደማ የሚመነዘረው ዶላር በጥቁር ገበያ ከ28 ብር በላይ እየተመነዘረ ነው። በርካታ ባለሃብቶች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ብር ወደ ዶላር በመመንዘር ሃብታቸውን ወደ ውጭ ማሸሻቸው፣ ወደ አገሪቱ የሚገባው ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ፣ ዲያስፖራው ወደ አገሩ የሚልከው ገንዘብ በመቀነሱ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ...

Read More »

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጀውን የስራ ዕድል ባለስልጣናት ያደራጇቸው ቤተሰቦች እና ስራቸውን የለቀቁ መሃንዲሶች እየተጠቀሙበት ነው ተባለ፡፡

ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በተለያዩ የክልል ቢሮዎችና የዞን መምሪያዎች በግንባታ ስራ ላይ ተቀጥረው የሚገኙ  መሃንዲሶች ስራቸውን በመልቀቅ ላይ ያሉት በቅርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ  ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የስራ ዕድል አማራጮችን ለማስፋፋትና ለማበረታታት በሚል የተዘጋጀውን መመሪያ ቁጥር 27/2009 ተንተርሶ ነው፡፡ መመሪያው ከተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ የሌላቸውን  ወጣቶች ወደ ስራ ለማስገባትና የስራ ዕድል አማራጮችን ለመፍጠር የሚል  ቢሆንም፤ ወጣቶችን ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎችን ለማጥቃት አዲስ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በዞኑ የተለያዩ ግንባሮች በተደረጉ ውጊያዎች ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰበት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ዛሬ ረዕቡ ማለዳ ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ወልቃይት አሰማርቷል። አዲሱ እንቅስቃሴ የጸረ ሽምቅ አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘ መታሰራቸውን ተከትሎ የታቀደ ሲሆን፣ ቀደም ብለው የተደረጉት ተመሳሳይ ዘመቻዎች ሳይሳኩ ቀርተው ነበር። ለውጤት መጥፋቱ ተጠያቄ የተደረጉት ኮማንደር ዋኘው ሲሆኑ፣ የአሁኑን ...

Read More »

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ዝውውር ላይ አፈና መፈጸሟን የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አስታወቀ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ  አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ተከትሎ  በሕገወጥ መንገድ ድረገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎትን በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም መዝጋቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። ሕዝባዊ ተቃውሞው ከተነሳበት እ.ኤ.አ. ኖቨምበር 2015 ጀምሮ ማኅበራዊ ድረገጾችን፣ የግል የዜና አውታር ድረገጾችን በመዝጋት ሕገወጥ የሆነ የመብት ጥሰቶች መፈጸሙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። አስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ...

Read More »

ባለቤትነቱ የሸህ መሀመድ አል አሙዲ የሆነው የሀዋሳው ሚሊኒየም ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ከተዘጋ ሳምንት አለፈው።

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፋብሪካው ሰራተኞች እንደተናገሩት መንግስት ፋብሪካውን በመዝጋቱ ሳቢያ ከ450 በላይ የሆኑ ስራትኞች በስጋት ተውጠው ይገኛሉ። መንግስት የሸህ አልአሙዲ ንብረት የሆነውን ይህን ፋብሪካ የዘጋው የጥራት ደረጃውን አልጠበቀም በሚል ነው። የፋብሪካውን መዘጋት ተከትሎ ፔፕሲ ኢንተርናሽናል ወደ ስፍራው በመምጣት ባደረገው ምርመራ ፋብሪካው ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ ማረጋገጫ ቢሰጥም መንግስት እንዳይከፈት አዟል ተብሎ ከሳምንት በላይ ታሽጎ ይገኛል። ቀደም ...

Read More »

የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ቦታ አናውቅም አሉ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ህብረት መንግስት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ቦታ እንዲያሳውቅ መጠየቁን የዘገበው አሶሺየትድ ፕሬስ፣ የኢትዮጰያ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር  የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ግዛቸው መንግስቴ  ጋዜጠኛ ተመስገን ያለበትን ቦታ እንደማያውቁ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥቅምት 2014 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ህብረቱ  ዛሬ እንዳለው  ከሁለት ኣመት እስር ...

Read More »

የትምህርት ጥራቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መሄዱ ተነገረ፡፡

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በሚካሄደው የመማር ማስተማር ሂደት የትምህርት ጥራቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መምጣቱን ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ በክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በሚካሄዱ የመምህራን ቅጥር ከአስረኛ ወደ አስራ አንደኛ ክፍል መሸጋገር ያልቻሉ ተማሪዎችን ያካተተ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎች፣ የሚቀጠሩት ረዳት መምህራን ምንም ዓይነት ስልጠና ሳይሰጣቸው ወደ ሙያው ገብተው እንዲሰሩ በመደረጋቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን የገደሉ ሶስት ዘራፊዎች ተያዙ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካዋ ሞዶርኩል መንደር በሱቅ ውስጥ በስራቸው ላይ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን ገድለው በመዝረፍ ያመለጡት ሶስት ወንጀለኞች ሰኞ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቦሎሴንቴ ፍሪ ስቴትስ ፖሊስ አስታውቋል።ሟቾቹ ኢትዮጵያዊያን የ27 እና 31 ዓመት ወጣቶች ሲሆኑ ዘራፊዎቹ ንብረቶቻቸውን ዘርፈው ከአካባቢው መሰወራቸውንም ፖሊስ ገልጿል። ተጠርጣሪ ወንጀሎኞቹ በሕዝብ ትብብር መያዛቸውን እና እድሜያቸውም የ27፣32 እና 33 ዓመት ...

Read More »

የሰሜን ጎንደር ዞን የጸረ ሽምቅ አዛዥ መታሰራቸውን ተከትሎ እየደረገ ባለው ግምገማ አባላቱ ለሁለት ተከፍለዋል

ታኅሣሥስ ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰሜን ጎንደር ዞን የጸረ ሽምቅ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘ፣ በነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ታማኝ ወታደሮች መካከል የሚደረገውን ውጊያ ተከትሎ ፣ በገዢው ፓርቲ በኩል ለደረሰው ሽንፈት ተጠያቂ ናቸው በሚል ከታሰሩ በሁዋላ ፣ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ አመራሮች እየተገመገሙ ሲሆን፣ አመራሮች ለሁለት ተከፍለዋል። አንደኛው ወገን የኮማንደሩን መታሰር አጥበቆ እየተቃወመ ሲሆን፣ የህወሃት ድጋፍ አላቸው ...

Read More »