የብር የምንዛሬ ዋጋ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ነው

ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከተከሰተው ህዝባዊ አመጽ በሁዋላ የዶላር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል። በህጋዊ ገበያ በ23  ብር ገደማ የሚመነዘረው ዶላር በጥቁር ገበያ ከ28 ብር በላይ እየተመነዘረ ነው። በርካታ ባለሃብቶች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ብር ወደ ዶላር በመመንዘር ሃብታቸውን ወደ ውጭ ማሸሻቸው፣ ወደ አገሪቱ የሚገባው ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ፣ ዲያስፖራው ወደ አገሩ የሚልከው ገንዘብ በመቀነሱ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አስተዋጽኦ ማድረጉ ይነገራል።

በአገሪቱ የሰፈነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባለሀብቶችን ይበልጥ እያሸሸ እንጅ እያረጋጋ አለመሆኑንም ታዛቢዎች ይናገራሉ።