በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን የገደሉ ሶስት ዘራፊዎች ተያዙ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካዋ ሞዶርኩል መንደር በሱቅ ውስጥ በስራቸው ላይ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን ገድለው በመዝረፍ ያመለጡት ሶስት ወንጀለኞች ሰኞ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቦሎሴንቴ ፍሪ ስቴትስ ፖሊስ አስታውቋል።ሟቾቹ ኢትዮጵያዊያን የ27 እና 31 ዓመት ወጣቶች ሲሆኑ ዘራፊዎቹ ንብረቶቻቸውን ዘርፈው ከአካባቢው መሰወራቸውንም ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪ ወንጀሎኞቹ በሕዝብ ትብብር መያዛቸውን እና እድሜያቸውም የ27፣32 እና 33 ዓመት የሆናቸው ወጣቶች መሆናቸውን የፖሊስ አዛዡ ሌቴናንት ጄኔራል ቦት ስሜት ስዌይና መናገራቸው ታይምስ ላይቭስ ዘግቧል።