Amsterdam

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአዲግራት ዩኒቨርስቲ 1ኛ አመት ተማሪ የነበረው ሹሚ ለማ በቀለ ጥር 15 ቀን 2009 ዓም ተገድሎ አስከሬኑ ለቤተሰቦቹ ከተላከ በሁዋላ ጥር 19 ቀን 2009 ዓም ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ተቀብሯል። የሰንዳፋ ድሬ አካባቢ ተወላጅ የሆነው ተማሪ ሹሜ ጥር 15 ቀን ፈተና እንደጨረሰ ለወላጆቹ ስልክ ደውሎ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ ተናግሮ ...

Read More »

ቻዳዊው ሙሳ ፋቂ መሃማትን የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት የ56 ዓመቱ ጎልማሳ ሙሳ ፋቂ መሃማት ኬንያዊቷን ዲፕሎማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሀመድን አሽንፈው የአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል። 38 ድምጽ በማግኘት የአፍሪካ ህብረት ፕሎሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ሙሳ ፋቂ አገራቸውን ቻድ በተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሐመድ፣ ቦትስዋናዊቷ ፔሎኖሚ ቬንሰን ...

Read More »

በፊንላንድ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ በፊንላንድ አገር በሄሊንስኪ ከተማ የኢሳት ቤተሰቦች እና ከአምስተርዳም የኢሳት ጋዜጠኞች በተገኙበት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያውኑ ስለአገራቸው እና ስለኢሳት አጀንዳዎችን አንስተው ተወያይተዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢሳትን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ ከተጋባዥ እንግዶችም ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢሳትን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።

Read More »

በጃዊ ጫካ ውስጥ በርካታ ወታደሮች በረሃብና በውሃ ጥም አለቁ

ጥር ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ሳምንታት በፊት በ12ኛው ክፍለጦር ስር ባለው በፓዊና አሶሳ ሰፍሮ ከሚገኘው የ6ኛ እና 7ኛ ሬጅመንቶች የተውጣጣ አንድ አሳሽ ግብረሃይል በጃዊ በረሃና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው አዲስ ናሽናል ፓርክ ውስጥ የነጻነት ሃይሎች ይገኛሉ በሚል ለአሰሳ ከወጣ በሁዋላ ፣ በአቅጣጫ መጥፋት ምክንያት በውሃና በምግብ እጦት ምክንያት በርካታ ወታደሮች ሲሞቱ ፣ በህይወት ...

Read More »

በኦጋዴን የሚታየውን ረሃብ መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች ሆን ብለው አሳንሰውታል ሲል ኦብነግ አስታወቀ

ጥር ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መግለጫ በኦጋዴን ለሁለት ተከታታይ አመታት የተቛረጠው ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳትን መግደሉንና ህዝቡንም ለአደጋ እንዳጋለጠው ጠቅሷል። አብዛኞቹ የኦጋዴን አካባቢዎች ለከፋ የውሃ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን፣ እንስሳትም የሚመገቡት አጥተዋል። ህዝቡ ችግሩን ለማቋቋም እንዳይችል የንግድ፣ የእርዳታ እና የመገናኛ ብዙሃን አፈና ተጥሎበታል የሚለው መግለጫው፣ በተለይ ልጆች በውጭ አገራት ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በጥልቅ ተሃድሶ ስም በሚካሄዱ ስብሰባዎች የተነሳ ህዝቡ በአገልግሎት እጦት እየተማረረ ነው

ጥር ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ፣ ኦሮምያና ደቡብ ክልሎች “ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል የሚደረጉ ስብሰባዎች የመንግስት ስራ እንዲቆም በመድረጉ ህዝቡ አገልግሎት ማግኘት አልቻለም። በአብዛኛው ቦታዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዘጋታቸው አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን፣ አንዳንድ ተገልጋዮች “ ምንም ለውጥ በማያመጣ ስብሰባ “ እየተንገላቱ መሆኑን ገልጸዋል። በአማራ ክልል በሚካሄደው ስብሰባ፣ ሰራተኞች የአሁኑ ስብሰባ ከአሁን በፊት ከተደረጉት ስብሰባዎች የተለየ ...

Read More »

በአርባምንጭ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተከሰ

ጥር ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በሚኖርባት የአርባምንጭ ከተማ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከተማዋ 50ኛ አመቷን ባከበረችበት ወቅት ህዝቡ ባቀረበው አቤቱታ የከተማዋን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በሚል 86 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ከተካሄድና በርካታ የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ከተቀበሩ በሁዋላ፣ የሚከታተላቸው አካል በመጥፋቱ ስራው መቋረጡን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በከተማው ...

Read More »

ዛምቢያ 147 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች

ጥር ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛንቢያ ገብተዋል ያላቸውን በእስር ላይ የነበሩ 147 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የአገሪቱ የስደተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤት አስታውቋል። ስደተኞቹ እ.ኤ.አ. 2016 ጀምሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ተይዘው በተለያዩ የዛንቢያ እስር ቤቶች ውስጥ በግዞት አሳልፈዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ባለፈው ወር የእስራት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ በዛንቢያ ፕሬዚዳንት ...

Read More »

በጢስ አባይ በነዋሪዎችና ወታደሮች መካከል ግጭት ተቀስቅሷል

ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህር ዳር 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የጢስ አባይ ከተማ የአገዛዙ አመራሮች በየጊዜው በሚያደርጉት ጫና የተማረሩት የከተማዋ ነዋሪዎችና የአካባቢው አርሶ አደሮች ሰሞኑን በተደጋጋሚ በደረሰባቸው እንግልት በመማረር በትላንትናውና በዛሬው እለት በተካሄዱት የእምቢተኝነት ተቃውሞ ግጭቱ ተባብሶ ወደ ጦር መሳሪያ መማዘዝ በመሻገሩ ጉዳት መድረሱን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በአካባቢው ከተንቀሳቀሱ የመንግስት ...

Read More »

አወዛጋቢ በሆነው የሶማሊና ኦሮምያ ክልሎች ድንበር ላይ መከላከያ እንዲሰፍር ተወሰነ

ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በአቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመራው የሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያ አባላት ወደ ኦሮምያ ድንበር በመግባት በርካታ ሰዎችን ከገደሉና ካፈናቀሉ በሁዋላ፣ የሁለቱ ክልል መሪዎች እርስ በርስ እስከመዘላለፍ የደረሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ የፌደራል መንግስት አዳማ ላይ አድርጎት በነበረው ስብሰባ ላይ የሁለቱም ክልሎች ሚሊሺያዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡና በስፍራው የመከላከየጣ ሰራዊት እንዲገባ ውሳኔ አሳልፈዋል። ...

Read More »