ቻዳዊው ሙሳ ፋቂ መሃማትን የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት የ56 ዓመቱ ጎልማሳ ሙሳ ፋቂ መሃማት ኬንያዊቷን ዲፕሎማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሀመድን አሽንፈው የአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል። 38 ድምጽ በማግኘት የአፍሪካ ህብረት ፕሎሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ሙሳ ፋቂ አገራቸውን ቻድ በተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሐመድ፣ ቦትስዋናዊቷ ፔሎኖሚ ቬንሰን ሞታይ፣ የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጋፒቶ ምባ ሞኩይ እና ሴኔጋላዊው ዶ/ር አብዱላዪ ባዚልይ እጩ ተፎካካሪ ሆነው ቀርበዋል።
ደቡብ አፍሪካዊቷ ዶ/ር ኒኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ የአፍሪካ ህብረትን ላለፉት አራት ዓመታት የመሩ ሲሆን እስከ ሰኔ ወር ድረስ በሃላፊነታቸው ይቆያሉ። በምእራብ ሳህራ ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ከአፍሪካ ሕብረት ከሰላሳ ዓመታት በላይ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት እስከ አፍሪካ ኅብረት ራሷን አግላ የቆየችው ሞሮኮ ”ትመለስ? ወይስ አትመለስ?” በሚለው ላይ ድምጽ ይሰጣል። 54 አባል አገራት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በሕብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።