በፊንላንድ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ በፊንላንድ አገር በሄሊንስኪ ከተማ የኢሳት ቤተሰቦች እና ከአምስተርዳም የኢሳት ጋዜጠኞች በተገኙበት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያውኑ ስለአገራቸው እና ስለኢሳት አጀንዳዎችን አንስተው ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ኢሳትን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ ከተጋባዥ እንግዶችም ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢሳትን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።