ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን መርጃ እንዲውል በአውስትራሊያ ከተሞች ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከ 115 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ። የሜልቦርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ቡድን ባደረገለት ግብዣ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ባለፈው ኦገስት 12 ቀን አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁ አርቲስት፤ በአምስት የአውስትራሊያ ከተሞች ማለትም በሜልቦርን፣ በሲድኒ፣ በአድላይድ፣ በብሪዝበንና በፐርዝ እንዲሁም በኒውዝላንድ-ኦክላንድ ባካሄዳቸው ደማቅ ዝግጅቶች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ዘመቻ መጠቀሙ እንዳሳፈራቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ
ነሀሴ ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ፌደራሊስ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የበላይ ጠባቂና የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ዲክታተር ነበሩ ብለዋል:: የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ኢስነምግባራዊ እና የሚዘገንን ነው በማለት መላውን የኢህአዴግ አመራሮች ወቅሰዋል :: ኢህአዴግ ህዝቡን አልቅሱ ብሎ አለማስገደዱን ይልቁንም በራሱ ፈቃድ ፈንቅሎ እንደወጣ ይናገራል ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ ታፈነዋል አለ
ነሀሴ ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ በሀገሪቱ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የሰብዓዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ መታፈናቸውን ቀጥለዋል ሲል አንድነት ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ። አንድነት ፓርቲ ፦”የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ መታገድ፤አምባገነናዊው ስርዓት አፈናውን አጠናክሮና አባብሶ መቀጠሉን የሚያሳይ ድርጊት ነው” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤የ አቶ መለስን ሞት ተከትሎ በሀገሪቱ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የሰብዓዊ፣የዲሞክራሲያዊና ሀሳብን ...
Read More »ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስን ለመተካት እየታገሉ ነው
ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸውን በሞት ካጡ በኃላ በእሳቸው እግር ተተክተው የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ ተቆናጥጦ ወደ ኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት ለመሳብ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ መክረማቸውን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ በኢህአዴግ 36 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ብቸኛ ሴት ሆነው በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም ከፍተኛውን የፓርቲ ሥልጣን በባለቤታቸው በአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ ድጋፍ ማግኘት የቻሉት ወ/ሮ አዜብ ...
Read More »በጀርመን የሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማህበር ካህናት አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ጠየቁ
ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ነሀሴ 26 ቀን 2004 ዓም በጀርመን አገር ፍራንከፈርት ከተማ ባወጣው መገልጫ ላይ ” እስካሁን ቤተ ክርስቲአኑዋን ለሁለት የከፈለው ጉዳይ በእግዚአብሄር ፈቃድ አንደኛው አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ስለዚህ አሁን በህይወት ያሉት ቀድሞም ያለአግባብ በመንግስት ሀይል ከስልጣናቸው እንዲወገዱ የተደረጉት አባት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ሊመለሱ ይገባል። ማህበሩ ያለፈው ስህተት እንዳይደገም ...
Read More »አቶ ሀይለማርያም ግልገል ጊቤ ሦስት በታሰበው ጊዜ አይጠናቀቅም አሉ
ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቀጣዮቹ ዓመታት የሀይል እጥረት ያጋጥማል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ ከአንድ ዓመት በሁዋላ ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ ሀይል ማመንጫ ግንባታ በተባለው ጊዜ እንደማይጠናቀቅ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ። በመስከረም 2006 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግንባታ በወቅቱ እንደማይጠናቀቅ በመረጋገጡ፣ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ አዲስ ...
Read More »የአቶ መለስን ዜና እረፍት ሲሰሙ አላዘኑም ወይም አላግጠዋል የተባሉ ወደ ሰንዳፋና ሸዋ ሮቢት እስርቤቶች ተላኩ
ነሀሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት በርካታ አስገራሚ ነገሮችን እያሳየ በመጠናቀቅ ላይ ነው። እሁድ እለት አብያተ ቤተክርስቲያናት ለአቶ መለስ ልዩ የጸሎት ስነስርአት እንዲያዘጋጁ መታዘዙ በተሰማ ማግስት፣ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ አላግጣችሁዋል ወይም በደንብ አላዘናችሁም የተባሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ በርካታ ወጣቶች በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ (ማዕከላዊ)፣ ሰንዳፋ እና ...
Read More »የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እንዳይታተም ታገደ
ነሀሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሀሙስ እለት ተጨማሪ ልዩ ህትመታቸውን በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት ለማሳተም የ18 እሺ ጋዜጣ ዋጋ ለመክፈል የሄዱት የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አዘጋጆች በማተሚያ ቤቱ ሁለተኛ ለእናንተ ጋዜጣ ህትመት በእኛ ማተሚያ ቤት አይታተምም ብለው እንደከለከሉዋቸው ታውቋል። የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች የማተሚያ ቤቱን ሀላፊዎች ያነጋገሩ ሲሆን፣ ፣ እናንተ የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ሞት ...
Read More »የአፋር ፎረም ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ነው
ነሀሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በቤልጂየም ብራሰልስ ጉባኤያቸውን የሚያካሂዱት የለያዩ የአፋር ተወላጆችና ድርጅቶች የተሰባሰቡበትን ዝግጅት የአስተባበሩት አቶ ጋዝ አህመድ ለኢሳት እንደገለጡት ከ፣ ጅቡቲ፣ ከኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ አውሮፓ እና ከሌሎችም አካባቢዎች የተውጣጡ ከ አንድ መቶ አምሳ በላይ ሰዎች ተገኝተው መግለጫ ሰጥተዋል። የአውሮፓ ፓርላመንት ምክትል ሀላፊና የተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ በርካታ መጽሀፍትን የጻፉት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር ...
Read More »የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ ፍቅሩን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲለውጥ ጥረት እንዲያደርጉ ታዘዙ::
ነሀሴ ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ያለው አቶ መለስ ዜናዊን ልዩ ሰው አድርጎ የመሳል እንቅስቃሴ ድርጅቱን ስጋት ላይ እየጣለው በመምጣቱ ካድሬዎች የፕሮጋንዳ ስራቸውን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲያዞሩ ታዘዋል። ኢህአዴግ በመጀመሪያ በአቶ መለስ ዜናዊ የግለሰብ ስብእና አስታኮ ስልጣኑን ለማደላደል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቀይሶ የነበረ ቢሆንም፣ የፕሮፓጋንዳው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን እየቀየረ መምጣቱ ድርጅቱን ስጋት ላይ ጥሎታል። አቶ መለስ ...
Read More »