የአፋር ፎረም ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ነው

ነሀሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በቤልጂየም ብራሰልስ ጉባኤያቸውን የሚያካሂዱት የለያዩ የአፋር ተወላጆችና ድርጅቶች የተሰባሰቡበትን ዝግጅት የአስተባበሩት አቶ ጋዝ አህመድ ለኢሳት እንደገለጡት ከ፣ ጅቡቲ፣ ከኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ አውሮፓ እና ከሌሎችም አካባቢዎች የተውጣጡ ከ አንድ መቶ አምሳ በላይ ሰዎች ተገኝተው መግለጫ ሰጥተዋል።

የአውሮፓ ፓርላመንት ምክትል ሀላፊና የተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ በርካታ መጽሀፍትን የጻፉት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር ማርካከሲስም ተገኝተው በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ንግግሮችን  አድርገዋል።

አቶ ገዓዝ ጉባኤው የተለያዩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን አንስቶ መወያየቱንም ውሳኔም እንደሚያሳልፍ ታውቋል።

ጉባኤው እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide