.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ ባንኮች በጠቅላላ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ በመከሰቱ ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ እንደተሳናቸው ተዘገበ

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር፦”የዶላር ያለህ!” በሚል ርዕስ ባጠናቀረው ዘገባ የውጪ ምንዛሬ እጥረቱ ከተከሰተ የሰነበተ ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ግን ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክቷል። ከወራት በፊት በቂ የውጭ ምንዛሪ ያለ መሆኑ ቢገለጽም፣ አሁን በተጨባጭ የሚታየው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል-ብሏል ጋዜጣው። የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የባንኮችን ደጃፍ የሚረግጡ  አስመጪዎች፤ <ሌተር ኦፍ ክሬዲት> ለመክፈት እና ማስመጣት የሚገባቸውን ምርት ለማምጣት ...

Read More »

አዳማ በመጠጥ ውሀ እጥረት እየተሰቃየች ነው

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት በጣለ ከባድ ዝናም ከቆቃ ወደ ናዝሬት  የተዘረጋው ቧንቧ በመወሰዱ የ አዳማ ነዋሪዎች ለ 15 ቀናት በውሀ ጥም መቃጠላቸውን ተናገሩ። በድንገት ውሀ የተቋረጠባቸው የናዝሬት ነዋሪዎች፣ ችግሩ አልፎ አልፎ እንደሚከሰተው ቀላል  መስሏቸው ከዛሬ ነገ ይሠራል በማለት በትዕግስት ቢጠብቁም፣ ችግሩ ተባብሶ 15 ቀናት እንደሞላዋቸው ተናግረዋል::  የከተማው ማዘጋጃ ቤት ነዋሪዎቹ እንዳሉት፤የከተማው ማዘጋጃ ቤት የተፈጠረውን ...

Read More »

በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ድረድር ተጀመረ

(Sept. 10) በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ድረድር እየተካሄደ መሆኑን፤ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጪ ግንባር የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት ገለጡ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደተናገሩት ድርድሩ በናይሮቢ በኬንያ መንግስት አደራዳሪነት ባለፈው ሀሙስና አርብ ተካሄዷል። የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚደራደረው በሶስተኛ አገሮች መሆን እንዳለበት ጠይቆ የነበረ ሲሆን፤ ያንን ቅድመሁኔታ ሳይቀበል የቆየው የኢትዮጵያ ...

Read More »

1900 እስረኞች በምህረት ሊፈቱ ነው

የአትዮጵያ መንግስት ሁለቱን የስዊድን ጋዜጠኞች፤ ማርቲን ሽብዬና ዮሀን ፐርሶንን ጨምሮ፤ ለ1900 እስረኞች ምህረት ማድረጉን የተለያዩ አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። እስረኞቹ የተለቀቁት የኢትዮጵያን አዲሱን አመት በማስመልከት ባስገቡት የይቅርታ ጥያቄ መሰረት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሞታቸው በፊት፤ በተለይም ለሁለቱ የሰውዊድን ዜጎች ምህርት አድርገው ለአዲስ አመት ሊፈቷቸው እንደነበር ባለስልጣናቱ ገልጸው፤ 1900 እስረኞች በዚህ ሳምንት በሚደረግ የምህረት ስነስርአት እንደሚለቀቁ ...

Read More »

ሳውዲ አረቢያ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አገደች

(Sep. 10) የሳኡዲ አረቢያ መንግስት፤ ዜጎቹ ወደኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲገቱ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። በአገሪቱ ውስጥ በሙስሊሞችና በፖሊስ መካከከል በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት፤ ግጭቱ እስኪበርድና አገሪቱ ውስጥ ያለው ውጥረት እስኪረግብ ድረስ፤ የሳኡዲ መንግስት፤ ዜጎቹ ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ እንዳስጠነቀቀ እለታዊው የአረብኛ ጋዜጣ፤ አካዝ ጽፏል። በኢትዮጵያ የሳኡዲአረቢያ አምባሳደር፤ አብዱል በቂ አህመድ አጅላን፤ ከአዲስ አበባ በጻፉት ማስጠንቀቂያ፤ “በረመዳን ወር፤ 7 የሳኡዲ ዜጎች በተለያዩ ስፍራዎች ሲዘዋወሩና የበጎ ...

Read More »

በጄነራል ሳሞራ ዩኑስ የሚመሩ የህወሀት አባላት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ  ሥራ አስፈፃሚ ሾልከው  የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ እና በሥራቸው ያሉ የህወሀት ጀነራሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብቁ የሆነ ሰው ከነሱ መካከል ስላለ በመለስ ቦታ ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጥ  መልዕክት አስተላልፈዋል። ጀነራሎቹ፦“መለስን መተካት የሚችል ብቁ ሰው አለን። ከኛ ፈቃድና ዕውቅና ውጪ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም አይችልም!”ነው ያሉት። የጀነራሎቹ መልዕክትና አቋም መሰማቱን ተከትሎ በኢህአዴግ ...

Read More »

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለ17 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለዩኒቨርስቲ መምህራን ይሰጣል

ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የመንግስት ሰራተኞችን በመጋበዝ፣ ለግንባሩ ያላቸውን ተአማኒነት በይፋ እንዲያረጋገጡ የነደፈው ስትራቴጂ በዩኒቨርስቲ መምህራን ይጀመራል። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በቀጥር 259/2311/04 በቀን 10/12/2004ዓም በላኩት ደብዳቤ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 20 ...

Read More »

የኦጋዴን በህራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ

ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ አነሳሽነት በኢህአዴግ መራሹ መንግስትና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር መካከል እኤአ ከመስከረም 6 እስከ 7፣ 2012 ባሉት ቀናት ውስጥ ድርድር ተካሂዷል። ውይይቱ የተመራው በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በሆኑት አቶ አብዱራህማን ማሀዲ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሀሰን ፈርጌሳ መካከል ነው። ውይይቱን የመሩት ደግሞ የኬንያው የእርሻ ሚኒስትር ...

Read More »

በ አፍሪካ ቀንድ ከ17 ሚሊዮን በላይ ህዝቦች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ

ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም  የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ በአፍሪካ ቀንድ 17 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ ኧስታውቃል። ከፍተኛ እርዳታ ከሚፈልጉት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ይገኙበታል። የአለማቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ በቅርቡ ገልጠዋል። ይህ አሀዝ ከ12 ሚሊዮን በላይ በሴፍቲኔት ...

Read More »

የጋንቤላው ተወላጅ እንግሊዝን ሊከሱ ነው

(Sept. 8) ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሰብአዊ መብቴ ተጥሶብኛል ያሉ አንድ የጋምቤላ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ የእንግሊዝ መንግስትን ሊከሱ እንደሆነ ቢቢሲ ዘገበ። ስማቸው ያልተጠቀሰውና በስደተኝነት በኬንያ የሚገኙት ከሳሽ በጠበቆቻቸው በኩል እንደተናገሩት፤ በጋምቤላ አካባቢ በሚካሄድ የሰፈራ መርሀግብር የተነሳ፤ ከመሬታቸው እንደተፈናቀሉና እንደተደበደቡ፤ እንዲሁም ሴቶች ሲደፈሩ እንደተመለከቱ ተናግረዋል። በጋምቤላ አካባቢ የሚደረገው የሰፈራ መርሀግብር፤ የእንግሊዝ አለምአቀፍ የዴቭሎፕመንት ድርጅት መምሪያ የገንዝብ ድጋፍ እንዳለበት ቢነገርም፤ ይህ መምሪያ ግን ...

Read More »