(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) በቀብሪዳህር መከላከያ ሰራዊት ግቢ የተጠለሉ ዜጎች የሰራዊቱ ቀለብ እየተመናመነ በመምጣቱ ለከፍተኛ ችግር መጋለጠቸውን ገለጹ። ላለፉት ስድስት ቀናት ሰራዊቱ ቀለቡን እያካፈላቸው መቆየቱን ተፈናቅዮች ገልጸዋል። ከ5ሺህ በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ቤት ንብረታቸው ተዘርፏል። ህይወታቸውን ለማትረፍ በአቅራቢያው በሚገኝ መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ተሸሽገው ይገኛሉ። በሌላ በኩል በጂጂጋ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም የምግብና የውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ችግሩ እየከፋ መምጣቱን ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የጅግጅጋ ነዋሪዎች በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙና የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ጥረት ቢጀምሩም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ተናገሩ
የጅግጅጋ ነዋሪዎች በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙና የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ጥረት ቢጀምሩም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኢሳት በስልክ ያነጋገራቸው የሶማሊ ክልል ተወላጆች በክልላቸው በተፈጠረው ድርጊት በእጅጉ እንዳሳዘናቸውና ድርጊቱም በጥቂት የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተፈጸመ እንጅ የከተማዋን ነዋሪዎች እንደማይመለከት ገልጸዋል። ጥቃት የተፈጸመባቸውን ወገኖች ቤታቸው አስጠልለው ያዳኑት አቶ ሽኔ፣ አቶ አብደ ኢሌ ቤተክርስቲያናትን ጨምሮ መቃጠል ያላበቸውን ...
Read More »በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ በተነሳው ተቃውሞ 5 ሰዎች ተገደሉ ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት ሰሞኑን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው።
በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ በተነሳው ተቃውሞ 5 ሰዎች ተገደሉ ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት ሰሞኑን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶች በሰንገጢ ቀበሌ 280 ሄክታር መሬት ይዞ የሚገኘውን ኢንቨስተር መሬት በመውረር < እኛ መሬት አጥተን ለአንድ ግለሰብ ይህን ያክል መሬት ሊሰጥ አይገባም” በማለታቸው ተቃውሞው መቀስቀሱ ታውቋል። በተርጫ ከመንገድ ስራ ድርጅት ጋር በተያያዘ የክልሉ የመገናኛ ...
Read More »አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ ካቢኔያቸውን ሊያዋቅሩ ነው
አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ ካቢኔያቸውን ሊያዋቅሩ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነሃሴ 4 ቀን 2010 ዓም አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ አዲስ ካቢኔ ሊዋቅሩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። 17 በሚሆኑ የቢሮ ሃላፊነት ቦታዎች የካቢኔ አባላት በቀጥታ እንደሚሾሙ ሲጠበቅ፣ ከተማዋን እንደፈለጉ ሲመሩ የነበሩት የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ በደቡብ ክልል የድርጅት ሃላፊው ...
Read More »በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ያለው የዘር መድልኦ ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ፡፡
በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ያለው የዘር መድልኦ ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ፡፡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቅርቡ የኢሳት ቴሌቪዥን “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ አመራሮች ዘንድ የሚሰራውን የተጠናከረ የሙስና አሰራር አጋልጠዋል” በማለት የተጠረጠሩ የሌላ ብሄር ተወላጅ የድርጅቱን ሰራተኞች ከኃላፊነት በማውረድ አሰራሩን ሚስጥራዊ ለማድረግ ይበልጥ እየሰራ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል፡፡ የኢሳት ቴሌቪዥን ዜና ከተሰማ በኋላ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ...
Read More »የሞጆ ዋየርና ኬብል ፋብሪካ በዘራፊዎች ምክንያት ሊዘጋ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 2/2010) በሜቴክ ስር ይተዳደር የነበረው የሞጆ ዋየርና ኬብል ፋብሪካ በዘረፋ ምክንያት መስራት ባለመቻሉ ሊዘጋ ነው ሲሉ ሰራተኞች ስጋታቸውን ለኢሳት ተናገሩ ። ፋብሪካው ከውጭ የሚገባለት ጥሬ እቃ ባለመኖሩም ከእንቅስቃሴ ውጪ እንዲሆን መደረጉንም ጠቁመዋል። በፋብሪካው ውስጥ ያሉት በርካታ ምርቶችና ጥሬ እቃዎችም እየተባላሹ መሆኑን ተናግረዋል። ይህንን ችግር የተናገሩ ሰራተኞችም ከደሞዝ ቅጣት ጀምሮ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ ኮንቴነር ለቀናት እንደሚታሰሩም አጋልጠዋል። ...
Read More »የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ባለስልጣን ፍርድ ቤት ቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 2/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 16 ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ሒደቱን በማቀነባበር የተጠረጠሩት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ባለስልጣን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ባለስልጣኑ ፍንዳታውን በውጭና በሃገር ውስጥ ካሉ ሃይሎች ጋር በማቀነባበርና የጥቃቱን አድራሾች በማስተባበርም ተጠያቂ መሆናቸው ተመልክቷል። ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ትዕይንተ ሕዝብ ላይ በተሰነዘረው የቦምብ ጥቃት ...
Read More »ኦብነግ ሁሉም ወገኖች ከግጭት ራሳቸውን እንዲያርቁ ጥሪ አቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 2/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/ ሁሉም ወገኖች ከግጭት ራሳቸውን እንዲያርቁና ሰላማዊ መፍትሄ ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ አቀረበ። ኦብነግ በጂጂጋ ባለፉት አራት ቀናት የተፈጸመውን ግድያና የቤተክርስቲያናት ቃጠሎ አውግዟል። ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል። መከላከያ ሰራዊቱ በመግባቱ የሶማሌ ተወላጆች ላይ አደጋ ተደቅኗል ያለው ኦብነግ የአብዲ ዒሌ ከስልጣን መወገድ ቢዘገይም ወሳኝ ርምጃ ነው ሲል ገልጿል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ መንግስት ...
Read More »በጅጅጋ ዜጎች በምግብና ውሃ እጦት እየተሰቃዩ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 2/2010) በጂጂጋ በቤተክርስቲያን የተጠለሉ ዜጎች በምግብና ውሃ እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለጸ። ምግብ ጭነው ወደ ጂጂጋ ሲያመሩ የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ በመታገታቸው ችግሩ የከፋ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአስቸኳይ የምግብና ውሃ አቅርቦት ካልተደረገ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ከጂጂጋ ውጭ በአንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋት እንዳለ ለማወቅ ተችሏል። በደገሃቡር የመከላከያ ሰራዊት ባለመግባቱ ስጋት እንዳደረባቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ጂጂጋ ከባለፉት ...
Read More »በጅግጅጋና በሌሎችም የሶማሊ ክልሎች የሚገኙ ዜጎች አሁንም የድረሱንል ጥሪ እያሰሙ ነው
በጅግጅጋና በሌሎችም የሶማሊ ክልሎች የሚገኙ ዜጎች አሁንም የድረሱንል ጥሪ እያሰሙ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጅግጅጋ በሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ፣ በደገሃቡር በፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም በቀብሪደሃር በመከላከያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አሁንም የድረሱን ጥሪ እያሰሙ ነው። በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ቢናገሩም፣ የምግብና የውሃ ችግር አሁንም ከፍተኛ ችግር ሆኖባቸዋል። በደጋሃቡር ደግሞ የመከላከያ ሰራዊት ባለመግባቱ የክልሉ ልዩ ...
Read More »