በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ በተነሳው ተቃውሞ 5 ሰዎች ተገደሉ ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት ሰሞኑን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው።

በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ በተነሳው ተቃውሞ 5 ሰዎች ተገደሉ
ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት ሰሞኑን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶች በሰንገጢ ቀበሌ 280 ሄክታር መሬት ይዞ የሚገኘውን ኢንቨስተር መሬት በመውረር < እኛ መሬት አጥተን ለአንድ ግለሰብ ይህን ያክል መሬት ሊሰጥ አይገባም” በማለታቸው ተቃውሞው መቀስቀሱ ታውቋል። በተርጫ ከመንገድ ስራ ድርጅት ጋር በተያያዘ የክልሉ የመገናኛ ብዙሃን ባቀረበው የተሳሳተ ዘገባ ሳቢያ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መውደማቸው ይታወቃል።