.የኢሳት አማርኛ ዜና

ህወሀት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ቦታ ሊወስድ መዘጋጀቱ ታወቀ

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የአቶ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መሾም፣ በኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ውስጥ በተለይም በኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ተቀባይነት ማጣቱ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የሀይለማርያም መንግስት ኦህዴድን የሚያስከፋ በተወሰነ መጠን የህወሀትን ተቃውሞ ሊያረግብ የሚችል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ታውቋል። በመንግስት የስልጣን ተዋረድ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀጥሎ የተሻለ ቦታ ተደርጎ የሚታየውን ...

Read More »

የኢትዮጵያ የውጪ ዕዳ 200 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተመለከተ

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያ የገንዘብና የ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው 134 ቢሊዮን ብር የነበረው የ አገሪቱ የውጪ ዕዳ እጅግ በሚያስደነግጥ መልኩ ባለፈው ሰኔ ወር ወደ 200 ቢሊዮን ብር አሻቅቧል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዶክመንንት ከዚህም በተጨማሪ የመንግስት የ አገር ውስጥ ብድርና ዕዳ 60 ቢሊዮን ብር መድረሱን ያመለክታል። ይህ ዕዳ ፤ኢትዮጵያ በቅርቡ  ለባቡር ሀዲድ መስመር ግንባታ ...

Read More »

ቻይና አፍሪካውያን ዲሞክራሲን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት እንደምታግዝ አስታወቀች

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ የሆኑት ሚስተር ሉ ሻየ ይህን የተናገሩት በአፍሪካ እና በቻይና ምሁራን መካከል በኢትዮጵያ በደብረዘይት ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ላይ ነው። ባለስልጣኑ እንዳሉት ቻይና አፍሪካዊያን ዲሞክራሲን ብቻ ሳይሆን፣ የህግ ተቋማትን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ታግዛለች። አገራቸው በመልካም አስተዳዳር ላይ ያላትን ልምድ ለአፍሪካ አገሮች ለማካፈል ዝግጁ መሆኑዋንም ገልጠዋል። ...

Read More »

በጋምቤላ የሚንቀሳቀሰው የናይሎቲክ ህዝቦች ንቅናቄ፤ ሰሞኑን ከኢትዮጲያ መንግስት ወታደሮች ጋር መጋጨቱ ተገለጸ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ፤ የጋምቤላ ምንጮችን በመጥቀስ እንዳመለከተው፤ በቅርቡ በተካሔደው ግጭት አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሲገደል፤ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል። የጋምቤላ መንግስት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፤ በአካባቢው የሚገኙትን ጸረሰላም ሀይሎች አስወግጃለሁ ቢልም፤ በጋምቤላ ያለው አለመረጋጋት መቀጠሉንና፤ ከ5 ወራት በፊት የተሾሙ ባለስልጣናትን በመሻር፤ አንዳዶቹን እያሰሯቸው መሆኑ ተመልክቷል። ከወራት በፊት ልጃቸው በመከላከያ ሰራዊት የተገደለባቸው ...

Read More »

በአርባምንጭ ከተማ ከ200 በላይ ነዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ከተማ ከ200 በላይ ነዋሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና 105 ሞተር ብስክሊቶችንና 8 ባጃጅ ተሽከርካሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ከባለንብረቶቹ ጋር መታሰራቸውን የእስራቱ ሠለባዎቹ ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በአርባምንጭ ከተማ በአፈሳ የታሰሩት ግለሰቦችና ንብረቶቻቸው ለምን እንደታሰሩ እንዳልተገለጸላቸው ያስታወቁት ሰለባዎቹ፤ ከታሰሩት ውስጥ የተደበደቡ መኖራቸውም አመልክተዋል። ተሽከርካሪዎቹ እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ ሥለታሰሩበት ምክንያት የታወቀ ይፋ ነገር ባይኖርም፤ አንድ ባለሥልጣን ...

Read More »

ከ2 አመት በፊት ከቴሌ የተባረሩ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በቴሌ በሚወጡ ስራዎችን ላይ ተወዳድረው እንዳይቀጠሩ እንደተከለከሉ ተናገሩ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮፕያ ቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የቴሌኮሚኒኬሽን ውል፤ ዜድ ቲ ኢ እና ሁዌይ ለተሰኙ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች እንደሰጠ የታወቀ ሲሆን፤ ከ2 አመት በፊት ከቴሌ የተባረሩ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ደግሞ በችግር ከመሰቃየታቸውም በላይ፤ በቴሌ የሚወጡ ስራዎችን ተወዳድረው እንዳይቀጠሩ እንደተከለከሉ ተናገሩ። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ሩ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በአሜሪካን ኮንግረስ በስለላና የአሜሪካንን ቴክኖሎጂ ሰርቆ ለቻይና በመስጠት ...

Read More »

የኢኮኖሚ እድገቱ በምርታማነትና በኢትዮጵያ ሀብት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ በኩል እንደሆነ ተገለጸ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መንግስት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ለ10ኛ አመት በድርብ ቁጥር ያድጋል ቢልም፤ የኢኮኖሚ እድገቱ በምርታማነትና በኢትዮጵያ ሀብት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ በኩል እንደሆነ ተገለጸ “ዚስ ኢዝ አፈሪካ” የተሰኘው የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት ከሚያድጉት አምስት ኢኮኖሚዎች ውስጥ ነው ቢባልም፤ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት፤ የቴክኖሎጂ ዘርፍና፤ የባንኩ ዘርፍ በጣም  ሁዋላቀርና በአፍሪካ ደረጃ እንኩዋን ...

Read More »

በዛሬው የጁመዓ ጸሎት ሙስሊሞች በዝምታ ተቃውሞአቸውን አካሂደው በሰላም ተበትነዋል

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁመዓ ጸሎት የስግደት መርሀ ግብር ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአዲስ አበባ መርካቶ አንዋር መስጊድ በዝምታ ተቃውሞአቸውን አካሂደው በሰላም ተበትነዋል ዛሬ ከቀኑ 4፡30 ጀምሮ በአንዋር መስጊድ እና በአካባቢው ከፍተና ቁጥር ያላቸው የመንግስት የደህንነት ሀይሎች በአለባበስ ሙስሊም መስለው መቀላቀላቸውን ለዘጋቢአችን የገለጡት አንድ የመስጊድ አስተናጋጅ፣ የፌደራል ፖሊሶች ዝግጁ ሆነው በኡመር ሰመተር ትምህርት ቤት እና በአራተኛ ፖሊስ ...

Read More »

የ 1 ዶላር ምንዛሬ ለማግኘት 1 ብር ከ 25 ሳንቲም ጉቦ መክፈል ግድ ነው ተባለ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከወጋገን ባንክ በስተቀር በአብዛኞቹ የአገሪቱ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ በመጥፋቱ፤  ምንዛሬ ፈላጊዎች  በእያንዳንዷ ዶላር  1 ብር ከ 25 ሳንቲም ጉቦ  እንዲከፍሉ መገደዳቸው  ተዘገበ።   በዚህም መሰረት አንድ ሰው የአንድ መቶ ሺ ዶላር ምንዛሪን ለማግኘት፤  ለምናዛሬ ፈቃጅ አካላቱ እስከ 125 ሺ ብር  ጉቦ መክፈል ግዴታው ሆኗል።   በቅርቡ የተከሰተውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመጠቀም የአንዳንድ ባንክ ...

Read More »

ስዊድናዊያኑ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለእስረኞች ሊለግሱ ነው

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሽብርተኝነትን በመርዳት ክስ ተመስርቶባቸው ላለፈው አንድ ዓመት በ ኢትዮጵያ ከታሰሩ በሁዋላ በቅርቡ በይቅርታ የተለቀቁት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች በሽልማት ያገኙትን 10 ሺህ የስዊድን ክሮነር በቃሊቲ እስር ቤት በዞን ስድስት ውስጥ ላሉ እስረኞች ለማበርከት ወሰኑ። በ እስር ቆይታቸው የኢትዮጵያውያንን አብሮ የመብላት ባህል ማየታቸውን የገለፁት  ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን፤ 10 ሺህ ክሩነሩን የለገሱት፤ የኢትዮጵያ ዓመት ...

Read More »