.የኢሳት አማርኛ ዜና

በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች በባንዲራ ቀን በአል ላይ የአቶ መለስን ፎቶ ግራፍ ይዘው እንዲወጡ ታዘዙ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ትእዛዝ መሰረት በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች የፈታችን ሰኞ በሚደረገው የባንዲራ ቀን በአል ላይ ጥቁር ሪባን በማሰርና የታላቁን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ከፍ አድርጎ በመያዝ በአሉን እንዲያከብሩ ትእዛዝ አስተላልፎአል። በመጪው ጥቅምት 19 የሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት ቃል ኪዳናችንን በማደስ የምናከብረው ነው ሲሉ ...

Read More »

ወጣቱ ትውልድ በአንድነት ለሀገር እድገት እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሡ ትውልድ ተቻችሎና ተከባብሮ ለሃገሩ በአንድነት እንዲቆምና እንዲሠራ አንጋፋው ኢትዮጲያዊ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ጠሪ አቀረቡ። በሐገር ቤትና በውጭ ሐገር የሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶችን ለመሸምገል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ዶር አክሊሉ ሐብቴ አብራርተዋል።በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የዛሬው አዲስ አበባ ፕሬዝዳንት የነበሩት በኋላም በሚንስትርነት እንዲሁም በአለም ባንክና በዩኒሴፍ ...

Read More »

የሙስሊም አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ዛሬ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው ያለ አንዳች ውሳኔ ለሰኞ ቀጠሮው መዛወሩ ተገለጠ።ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ እንደዘገቡት የአመራሮቹ የፍርድ ሂደት ቀድሞ የሚታየው በአራዳ ፍርድ ቤት የነበረ ቢሆንም ዛሬ የቀረቡት ግን በልደታ ፍ/ቤት ነው ። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት በተከሰሱበት የሽብርተኝነት ወንጀል ለብይን ቀጠሮ የተሰጣቸው ...

Read More »

በአባቶች መሀከል የሚካሄደው እርቅ በቀጣዩ ወር ይቀጥላል ተባለ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የተጀመረው የቀዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ባጸደቃቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይቱን ቅጥሏል።የእርቁ ሂደት በቀጣዩ ወር እንዲቀጥለም ወስኗል።ሰኞ ዕለት የተጀመረው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከቀረጻቸው አጀንዳዎች የፓትሪያሊክ መርጫ ህግ ማውጣት አንዱ መሆኑ ተመልክቷል፤ደጀሰላም እንደዘገበው ከፍተኛ የገንዘብ ብክለት የተመዘገበባቸው የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሰራ አስኪያጅ ንብረእድ ኤልያስ አብርሃ ከሃላፊነታቸው የመነሳታቸው ጉዳይ እያበቃለት ...

Read More »

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ በገርባ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኦነግ “የህወሀት ሽብር ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የሚደረገውን  ትግል አይገታውም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለአለፉት 11 ወራት መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ መቆየታቸውን አስታውሷል። ሙስሊሞች ያቀረቡት ጥያቄ፣ የይስሙላው ህገመንግስት እንኳን የሚፈቅደው ነው የሚለው ኦነግ፣ ሰሞኑን በገርባ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ግድያ ፣ ሌላው የህወሀት ጭካኔ  ማሳያ ነው ብሎአል። አዲሱ የይስሙላ ጠቅላይ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ሽልመቷን ተቀበለች

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ተከሳ በቃሊቲ እስር ቤት የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የ2012 የ ዓለማቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፍውንዴሽን ሽልማትን ተቀበለች።   የኢትዮፎረሙ ዳዊት ከበደ እንደዘገበው  የጋዜጠኛ ርዕዮትን ሽልማት ኒዮርክ በተካሄደው ዝግጅት ላይ ተገኝቶ  የተቀበለው የፀሀይ አሳታሚ ድርጅት ባለቤት ጋዘተጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ነው። ——————– ሽልማቱን ለመቀበል ቀደም ሲል የታጨው ጓደኛዋ ስለሺ ሃጎስ ቢሆንም፤ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ...

Read More »

ጤና ጥበቃ ከታራሚዎች 62 በመቶዎቹ በአዕምሮ ጭንቀት በሽታ የሚሰቃዩ ናቸው አለ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን ብሔራዊ የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂን ይፋ ባደረገበት ወቅት በለቀቀው መረጃ፤ በአዲስ አበባ፣ በቃሊቲና በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ከሚገኙት ታራሚዎች መካከል 61 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት በከፍተኛ የአዕምሮ ጭንቀት የተጠቁ መሆናቸውን ያመለክታል። ታራሚዎቹን ለአዕምሮ ጭንቀት ከሚዳርጓቸው ምክንያቶች መካከል በጠባብ ክፍል ውስጥ መታፈግ፣ በግዳጅ ለብቻ እንዲገለሉ ማድረግ ፣ብዙም እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ በቀጣይ ህይወት ...

Read More »

ካታርና ኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ሊጀምሩ ነው

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት አመታት የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ካታር ግንኙነታቸውን እንደገና ለመጀመር ማቀዳቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከአራት አመታት በፊት ካታር በኢትዮጵያ ውስጥ አፍራሽ ስራዎችን እየሰራች ነው በሚል የዲፐሎማሲ ግንኙነቷን መቋረጧ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ካታር በሱማሊያ የእስልምና አክራሪ ሀይሎችን ትደግፋለች የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ስታቀርብ ቆይታለች። የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከአምናዋ ሻምፒዮን ዛምቢያ ጋር ተመደበች

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ጥር በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የ29ኛው እግር ኳስ ዋንጫ የምድብ ድልድል ወጥቷል፤ ኢትዮጵያ በምድብ ሶስት፤ ከአምናዋ ቻምፒዮን ዛምቢያ፤ ቡርኪናፋሶና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላለች። ዛሬ፤ ረቡእ ጥቅምት 14 ቀን በደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ደርባን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማና የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት፤ ኢሳ አያቱ በተገኙበት ስነስርአት በወጣው እጣ፤ ኢትዮጵያ ከሶስቱ አገሮች ጋር ተደልድላለች። ደቡብ አፍሪካ በምድብ ...

Read More »

በኦጋዴን በመንግስት ወታደሮችና በኦብነግ መካከል ውጊያ ተቀስቀሷል

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ድርድር መቆረጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢ ውጊያ መቀጠሉን ኦብነግ አስታወቀ:: የኦብነግ የኢትዮጵያ ሀላፊ  አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ጉራት ማድረሳቸውን አመልክቶል:: በሶማሌ ክልል ወደ ደግሀቡር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ኦብነግ በሰነዘረው ጥቃት በርካታ ወታደሮች መገደላቸው ተመልክቶል:: ግድያውን ተከትሎ በአካባቢው ...

Read More »