በኦጋዴን በመንግስት ወታደሮችና በኦብነግ መካከል ውጊያ ተቀስቀሷል

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ድርድር መቆረጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢ ውጊያ መቀጠሉን ኦብነግ አስታወቀ::

የኦብነግ የኢትዮጵያ ሀላፊ  አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ጉራት ማድረሳቸውን አመልክቶል::

በሶማሌ ክልል ወደ ደግሀቡር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ኦብነግ በሰነዘረው ጥቃት በርካታ ወታደሮች መገደላቸው ተመልክቶል::

ግድያውን ተከትሎ በአካባቢው ውግያ መቀጠሉንና ውጥረት መስፈኑንም የአካባቢው ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተዋል::

በኬኒያ መንግስት አደራዳሪነት በናይሮቢ በሁለት ዙር በኢትዮጵያ መንግስትና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር መክሸፉን ተከትሎ በቀጠለው በዚህ ውጊያ የተገደሉ ወታደሮችንና የተማረኩ ቁሳቁሶችን ይፋ እንደሚያደርጉ የኦብነግ የኢትዮጵያ ጉዳይ ሀላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ገልጸዋል::