በጋምቤላ የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞችና ባለስልጣናት ተባረሩ

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የጋምቤላ ክልል ምክርቤት ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞችን ጨምሮ ባላስልጣናትን እንዳባረረ ገለጠ::

የአኞዋክ ሬዲዮ ሪፖርተር አጉዋ ጊሎ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደገለጠው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛና ምክትላቸው እንዲሁም የጤና ቢሮ ሀላፊና የደህንነት ሰራተኛ አቶ  ኦቻላ ከስልጣንና ከሀላፊነታቸው ከተባረሩት ውስጥ ይገኙበታል::

የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የተባረሩት በጋምቤላ ከሚገኙ ታጣቂ ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩ ባለስልጣናትን ማስረጃ ስላላገኙባቸውና0 በነጻ ስለለቀቋቸው መሆኑን ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ ገልጧል::

በጋምቤላ የገዥው ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ተከፍሎ ከፍተኛ ሽኩቻ መግባቱን የገለጸው አጉዋ ጊሎ፤ ከስራ አስፈጻሚ ለማባረር የተፈለጉ ሰዎችን ማባረር ስላልተቻለ በክልሉ መረጋጋት የለም፤ የመንግስት ስራም ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል ብሏል::