.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኦብነግ የተኩስ አቁም አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ። የግንባሩ አመራሮችም በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ሃገር ቤት ገብተዋል። እስከዛሬ ድረስ በግንባሩ ስም ተደርጉ ከተባሉ ስምምነቶች በተለየ ይህንን ውሳኔ ግንባሩ በራሱ ድረ ገጽም ይፋ ማድረጉ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ በመቀበል የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/ከእሁድ ነሐሴ 6/2010 ጀምሮ የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉን ነው ያስታወቀው። እሁድ ቀትር ላይ ይፋ ...

Read More »

በሻሸመኔ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድንን ለመቀበል በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔና አካባቢዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉም ታውቋል። ፖሊስ ከተማዋን ለማረጋጋት ...

Read More »

ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቀሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ። በአብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ጥቃትን ሸሽተው የተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል። በምዕራብ ሀረርጌ አሰቦት በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙት የጅቡቲ ተፈናቃዮች ምግብና ውሃ አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በምስራቅ ሀረርጌ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል መፈጸሙን መረጃው ...

Read More »

በተለያዩ የክልል ከተሞች በተቧደኑ ወጣቶች እየተፈጸሙ ያሉ የጎዳና ላይ ፍርዶች በሕዝብ ዘንድ ስጋት እያሳደሩ መምጣታቸው ተገለጸ።

በተለያዩ የክልል ከተሞች በተቧደኑ ወጣቶች እየተፈጸሙ ያሉ የጎዳና ላይ ፍርዶች በሕዝብ ዘንድ ስጋት እያሳደሩ መምጣታቸው ተገለጸ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ) ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በትናንትናው ዕለት ብቻ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ንጹህ ሰው ቦምብ ሊያፈነዳ ነበር በሚል መረጃ በወጣቶች ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ሲሆን፣ ግለሰቡ ቦምብ አስገብቶባታል የተባለች ተሽከርካሪም እንድትቃጠል ተደርጋለች፡፤ ሆኖም የኦሮሚያ ፖሊስ ነገሩን አጣርቶ በሰጠው መግለጫ ...

Read More »

ከሶማሊ ክልል ወደ ሃረር ከተማ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ለከፍተኛ ችግሮች ተጋላጭ ሆነዋል

ከሶማሊ ክልል ወደ ሃረር ከተማ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ለከፍተኛ ችግሮች ተጋላጭ ሆነዋል ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ) ባለፈው ሳምንት በጂጂጋና አዋሳኝ ከተሞች የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋና የተረፉ ለደኅንነታቸው በመስጋት ሕይወታቸን ለማዳን መኖሪያ ቀያቸውን እየተው የሚሰደዱ ዜጎች ቁጥራቸው እያሻቀበ ነው። ከሶማሊ ክልል ከሚሰደዱት ተፈናቃዮች ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር በማስተናገድ ሃረር ከተማ ቀዳሚዋ ሆናለች። በሃረር ሸንኮር ወረዳ የከተማ ...

Read More »

የአፍር ነፃ አውጭ ግንባር መሪ ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ነገ ወደ አገራቸው ይገባሉ

የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር መሪ ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ነገ ወደ አገራቸው ይገባሉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ) በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ ኋላ ላይ በታናሽ ወንድማቸው በሀቢብ አሊ ሚራህ እንዲተኩ መደረጋቸው ይታወቃል። የሱልጣን አሊ ሚራህ ልጆች ሀንፍሬ አሊ ሚራህ እና ሀቢብ አሊ ሚራህ በሽግግር መንግስቱ ወቅት ጉልህ አስተዋጽኦ ቢያደርጉም፤ ከ1987 ...

Read More »

የሶማሌ ልዩ ኃይል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ ዜጎች ቁጥር 42 ደረሰ።ለተፈጸሙ ወንጀሎች የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ ናቸው ተባሉ

የሶማሌ ልዩ ኃይል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ ዜጎች ቁጥር 42 ደረሰ።ለተፈጸሙ ወንጀሎች የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ ናቸው ተባሉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአብዲ ኢሌ ደጋፊ እንደሆኑ የሚታመኑ የሶማሌ ልዩ ኃይል ትናንትከቀትር በኋላ ነው ወባሳለፍነው ሳምንትደ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በመዝለቅ ድንገተኛ ጥቃት የፈጸሙት። የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት ግንቦር (ኦብነግ) ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የተኩስ አቁም ...

Read More »

በተሰጣቸው ግዳጅ የተበሳጩ የናይጀሪያ መከላከያ አባላት በአውሮፕላን ማረፊያ ለረዥም ሰዓታት በመተኮስ ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው።

በተሰጣቸው ግዳጅ የተበሳጩ የናይጀሪያ መከላከያ አባላት በአውሮፕላን ማረፊያ ለረዥም ሰዓታት በመተኮስ ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጸጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የተሰማሩ የናይጀሪያ ወታደሮች በድጋሚ የተሰጣቸውን ግዳጅ በመቃወም ከትናንት እሁድ ጀምሮ ጥይት ወደላይ እየተኮሱ ነው። የሰራዊቱ አባላት ጥይታቸውን ሽቅብ እያርከፈከፉ ያሉት በሰሜናዊቷ የናይጀሪያ ከተማ በማይዱግሪ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። የተቃውሟቸው ምክንያትም ወደ ግንባር በመዝመት ከቦኮሀራም ...

Read More »

የካቢኔ አባላት ሹመት ተሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 4/2010) የአዲስ አበባ ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ሰጠ። ምክር ቤቱ ሹመቱን የሰጠው የካቢኔ አባላትን በመበወዝ መሆኑም ታውቋል። የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሹመቱ ብቃትንና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ መሰረት ያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል። በአዲሱ የካቢኔ ድልድል በቅርቡ የብሔራዊ ቲያትር ስራ አስኪያጅ ሆኖ የተሾመው አርቲስት ነብዩ ባዬ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሆኖ ተሹሟል። በዚህም የብሔራዊ ቲያትር ...

Read More »

በኤፈርት ንብረቴን ተነጠኩ ያሉት ባለሃብት የድርሻቸውን ጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 4/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት በሆነው ኤፈርት ንብረቴን ተነጠኩ ያሉት ባለሃብት ድርሻቸውን ለማስከበር አቤቱታ አቀረቡ። የአዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ጠንሳሽና በኋላም የ60 በመቶ ባለድርሻ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ ጓዴ ሙሉ በሙሉ ድርሻቸው በሕወሃቱ ኤፈርት በመነጠቃቸው መብታቸውን ለማስከበር በእንግሊዝና በአሜሪካ ፍርድ ቤት ያደረጉትን ጥረት ለኢሳት ገልጸዋል። በደርግ ዘመነ መንግስት የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ንግዱ አለም በመግባት ስኬታማ ጉዞ ማድረጋቸውን የተናገሩት ...

Read More »